የግንቦት ሰባት ሌላ የተሳካ ስብሰባ በዳላስ ተካሄደ፡ ሁለት መቶ ሀምሳ ሰው ተጠመቀ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ልጅ ተክሌ

መስከረም 25 መሆኑ ነው? እኛ ተናጋሪዎቹ እኛ እንግዶቹ ወደ ውስጥ ስንገባ፡ የዳላስ ክራውን ፕላዛ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከግማሽ በላይ ሞልቷል። ስብሰባው ከተጠራበት ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በላይ ዘግይተን መጀመር ግን አልፈለግንም። ዶ/ር ብርሀኑ መሀል ቁጭ አለ። አቶ ዘነበ ሀይለማሪያም ገነሜ በስተግራ፡ ልጅ ተክሌ ደግሞ በስተቀኝ ተቀመጠ። የመድረኩ መሪና ሰብሳቢው አቶ አበበ እንግዶቹን አስተዋወቀ። ስብሰባው ተጀመረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለውድ ብርቱካን! (ኩችዬ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ይድረስ ለውድ ብርቱካን!

ቃሊቲ እስር ቤት - አዲስ አበባ

June 7 2009

ኩችዬ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. / www.kuchiye.blogspot.com

 

“ታውቅ ይሆን?” እያልኩ አወጣና አወርዳለሁ። “የስንቱን ህሊና እንደነካች ታውቀው ይሆን?” እላለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ህዝባዊ ተነሳሽነት ብዙ ሥራ ይቀረዋል” አቶ አክሉ ግርግሬ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ያሬድ ክንፈ ከስዊድን

በዕለተ ቅዳሜ ኅዳር 6 ቀን 2001 ዓ.ም. ከምኖርባት ከተማ 200 ኪሎ ሜትር ርቃ ወደምትገኘው የስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ያቀናሁት በመኺና ነበር። በዕለቱ የጉዞዬ ዋና ዓላማ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እና አቶ አክሉ ግርግሬ (የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ አባልና የዕቅድና የስትራቴጂ ኃላፊ) ከኢትዮጵያውያን ጋር ከቀኑ በ7 ሰዓት ሊያደርጉ ያቀዱትን ውይይት መሳተፍ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቅዱሳን ቦታ ላይ - ርኩሳን አይኖሩበትም! (ገሞራው)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ገሞራው - ዘስዊድን

ጦማር ቁጥር 2 (የመጀመሪያው ቁጥር ተከታይ)

ግባዊ ዓላማው እኔን ከምወዳት ሀገሬ ምድር ነቅሎ ለማስወጣት በሆነ ዕቅድ የትውልድ ቦታዬን ዘራቸው ለሆነ ሰው መስጠታቸውን ባለፈው መቅድማዊ መልዕክቴ ላይ መግለጼን ታስታውሱልኛላችሁ። የተፈፀመብኝ በደል እጅግ ቅጥ ያጣ መሆኑን ያነበበው ወገን ሁሉ እንደተረዳልኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”የቅዱሳንን ዐጽመ-ርስት፤ ርኩሣን አይወስዱትም!” (ከገሞራው)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

(የማስጠንቀቂያ ጦማር፣ ቁጥር ፩)

ገሞራው - ዘስዊድን

ለማላከብርዎ ቀማተኛ ...

በዚህ ቀዳማዊ ደብዳቤዬ ላይ ብዙኃን ቁምነገሮችን ለማስፈር፣ እምብዛም አያመቸኝም። ሊመቸኝ ካልቻለበት ወይም ከማይችልበት ምክንያቶች ውስጥ ዓይነተኛውና ተቀዳሚው ስለርስዎ ስለቀማኛው ማንነት በዝርዝር ለማወቅ ባለመቻሌ ነው። ስለቤተሰብዎ መሠረት፣ ስለሶሻል ዕርከናዊ ደረጃዎ፣ ስለትምህርት ጣራዎ፣ ስለሥራ ክፍልዎ፣ ስለኑሮ ባህርይዎ፣ ... በዝርዝር ባውቅ ኖሮ፣ በሰፊው አሟልቼ እጅግ በሚያመረቃ አቀራረብ፣ በጽፍኩልዎ ነበር። የእርስዎን ገበናዊ ራዕይ በመላምት ጅምላዊ ትኩረት ሳይ ግን አንድ ነጥብ ፍንትው ብሎ በግልጽና በጉልህ ታይቶኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግንቦት 7 ንቅናቄ በስዊድን (ያሬድ ክንፈ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ህዝባዊ ውይይቱ ምን ይመስል ነበር?

ያሬድ ክንፈ ከስዊድን

ሠላምና ጤናውን ከነቤተሰብህ ያበዛልህ ዘንድ የዘወትር ምኞቴ ነው። ለእመቤትህና ለልጃችሁ የከበረ ሠላምታዬን አቅርብልኝ። ዛሬ የማወጋህ “ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ” የተሰኘውና በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው አዲስ ንቅናቄ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ከተማ ከህዝብ ጋር ያደረገውን ውይይት ነው። ውይይቱ ቅዳሜ ሰኔ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. እንደሚካሄድ ስላወቅሁ ከስቶክሆልም 220 ኪሎ ሜትር ርቄ ከምኖርበት ሳንድቪከን ከተማ ወደዚያው አመራሁ። ንቅናቄውን በመወከል ዶ/ር ብርሃኑ እና አቶ ቸኮል ጌታሁን ነበር የተገኙት። አቶ ቸኮል የቀድሞው ቅንጅት የላዕላይ ምክር ቤት አባል የነበረ ሲሆን፣ አሁን በስዊድን ስደተኛ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...