በጅዳ ሽሜሲ በር ላይ ወድቃለች የተባለችው እኅት ጉዳይ! - የማለዳ ወግ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

በጠና የታመመችነቢዩ ሲራክ

* በሳውዲ ለተቸገሩት ተወካዮቻችን በቀዳሚነት ሊደርሱልን ይገባል
* ከኢንባሲና ከቆንስላ ውጭ አማራጭ የለም
* የቆንስሉ ሹማምንትና ሠራተኞች ለፈጣሪ ብላችሁ እርዷት፣ ተለመኑን!

ከትናንት ጅዳ ውስጥ በጠና ታማ እሷና ልጇ አደጋ ላይ አሉ ስለተባለችው እኅት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ደርሶኛል። መረጃውን በዝርዝር ያገኘሁት ከሊያ ሾው ነበር፣ ታመመች የተባለችውን እኅት በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ እንደደረሰኝ ወደ ጅዳ ቆንስል ደውዬ ለማጣራት ሞክሬ ነበር! በጅዳ ቆንስላ መረጃ ለማግኘት ከባድ እየሆነ መጥቷል፣ አንዳንዶች ኃላፊዎች ከዚህ ቀደም በማቀርባቸው ተጨባጭ ሂሶች አኩርፈው መረጃ ላለመስጠት ስልካቸውን ይዘጉብኛል፣ አንዳንዶች ደግሞ መረጃም ሆነ ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ አይደሉም! እጅ አዙር በሆነ መንገድ የጅዳ ቆንስል መረጃው እንዳልደረሰው ተነግሮኛል!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የልብ ስፔሻሊስት በወህኒ ቤት ለማጣት ተቃርባለች

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

Dr. Fikru Maru

እንደ ፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር በ1975 ፍቅሩ ማሩ እናት አገራቸውን ለቀው በስዊድን የስደተኝነትን ሕይወት መምራት ጀምረዋል። በስዊድን ቆይታቸው በልብ ሕክምና ስፔሻላይዝድ በማድረግ ዶክትሬታቸውን የሠሩት ፍቅሩ፣ ረዘም ላሉ ዓመታት በስደተኝነት በተቀበለቻቸውና ባስተማረቻቸው ስዊድን በሚገኘው ኹዲክስቫል ሆስፒታል (Hudiksvall) በሞያቸው ሲያገለግሉና በአገሪቱ ዮኒቨርሲቲዎች ሲያስተምሩ ቆይተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"እውነትን እንጂ ውሸትን አናስተናግድም" [የማለዳ ወግ]

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Mesfin Bezu of TG television* የምርጫው ትዝታዬ ... * የጅብ ችኩል ...

ነቢዩ ሲራክ

መቼም ይህ የአሜሪካ ምርጫ ከቅስቀሳው እስከ ትራንፕ ምርጫ ትዝታው ብዙ ነው። በመጨረሻው ቀንና በምርጫው ውጤት ቀን የሆንነው ግን በጣም ያጓጓና ልዩ ትዝታ ይዞ ያለፈ አጋጣሚ ነበር። ለብዙዎቻችን ... የማልረሳውን የእኔን ትዝታ ከትዝብት ጋር ላጋራችሁ ...

"እውነትን እንጂ ውሸትን አናስተናግድም!" የሚል መርኅን ይዘው ከሚንቀሳቀሱት የቲጂ ቲቪ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መስፍን በዙ "HILLARY WINS!" "ሂላሪ አሸነፈች!" የሚል አንድ አስገራሚ ሰበር መረጃ ከሌሊት 3:34 a.m. ተሰራጭቶ ደረሰኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድ ጉድ ልንገራችሁ!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

አንድ ጉድ ልንገራችሁ!

ያለፈው እኁድ የዱሮው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ኢሰመጉ (ዛሬ በግድ ስምን ለውጦ ሰመጉ የተባለው) የሃያ አምስተኛ ዓመት በዓሉን ለማክበርና በዚያው እርዳታ ለመሰብሰብ በደሳለኝ ሆቴል የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ ነበር፤ ኢትዮጵያውያንም የውጭ ሀገር ሰዎችም ነበሩ፤ ፕሮግራሙ ሲካሄድ ቆይቶ አንድ ሰዓት ያህል ሲቀረው ፖሊሶች መጥተው ፕሮግራሙ እንዲቋረጥ አዘዙ፤ ተቋረጠና ወደየቤታችን ሄድን! ስብሰባው የተደረገው አስፈላጊው ፈቃድ ሁሉ በጽሑፍ ከተገኘ በኋላ ነበር፤ ምናልባት ፈቃጆቹና ከልካዮቹ አይተዋወቁም ይሆናል!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ዓይናችን እያየ አትፈርስም!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Jawar Mohammedአቤ ቶኩቻው

ይቺ ሚጢጢ የአቋም መግለጫ ናት ብላችሁ አስቡ ... አንዳንድ ዕድሜ የተጫጫናቸው ስደት እና አሰልቺ ትግል የሀገራቸውን እና የህዝባቸውን ተጨባጭ ሁኔታ ያስረሳቸው ... ግለሰቦች እና ድርጅቶች ኢትዮጵያን አፍርሰን እኛ እንቆማለን ሲሉ እየሰማን ነው ... (እስቲ ማሉልን! ... በሳቅ ነው የምታፈርሷት!? ወይስ በመረጃ ልትቆፍሯት ነው!? ... !?)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጀግና ልጅ ልደቱ በኀዘንና በመከራ ይከበራል (የማለዳ ወግ)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ነቢዩ ሲራክHabtamu Ayalew with his daughter. ሀብታሙ አያሌው ከልጁ ከህፃን ኤማንዳ ሀብታሙ ጋር

* እንኳንም ተወለድሽ ህፃን ኤማንዳ ሀብታሙ

ዛሬ የወጣቱ አባዎራ ሀብታሙ የአብራክ ክፋይ ህጻን ኤማንዳ ሀብታሙ 4ኛው ዓመት የልደት ቀን መሆኑን ስሰማ ከልብ የመነጨ መልካም ምኞቴን ለመግለጽ፣ ብሎም በሕግ ሽፋን በአባቷ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በማውገዝ እንደ ዜጋ ማለት የምለውን ማለት ፈለግኩ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!