ለአህመዲን ሕክምና ስጡት፣ ፍቱትም! (የማለዳ ወግ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Ustaz Ahmedin Jebel

* ፍትሕ ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል!

* በግፍ አስሮም ሕክምና መንፈግ ለምን?

* ሐሳብን የደፈረው ጀግና ...!

ነቢዩ ሲራክ

የወንድም ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን በእስር ላይ ሕክምና መነፈጉን ከተለያዩ ምንጮች ለማረጋገጥ ችያለሁ። በእስር ላይ ያሉ ወገኖችን በሕገ መንግሥትና በዓለም አቀፍ ሕግ የተደነገገ እየተጣሰባቸው ነው። በሕግ ስር ባለው ኡስታዝ አህመዲንና በብዙ ታሳሪዎች መንግሥት የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸመባቸው ተደጋግሞ ተመልክተናል። ዛሬ አደባባይ በአህመዲን ያየነውም ይህንኑ ነው። በኡስታዝ አህመዲን ሰውነት ላይ የሚታየውን ጉዳትና መጎሳቆል ስመለከት የተሰማኝ ስሜት ደስ አይልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ኢትዮጵያ ኬኛ፣ ጣና ኬኛ!" ድንቅ መንፈስ! (የማለዳ ወግ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ነቢዩ ሲራክ

* "ጣና ኬኛ!" መልዕክቱ ከእንቦጭ አረሙ በላይ ነው
* የመለያየትና የመፈራረስን አደጋ ያከሸፈ መንፈስ

ከኦሮሚያ "ጣና ኬኛ!" እያለ የተመመው ወጣት ክፉውን የእንቦጭን ዐረም ነቃቅሎ እንደማያስወግድ ግልጽ ነው። ጥቂት ወጣቶች ተሸክመውት ጎጃም የገቡት ዋናው መልዕክት የኢትዮጵያዊነት፣ የአብሮነትና የ"አንድ ነን" እንጂ፤ የእንቦጭ ተራ ዐረም አልነበረም። ኢትዮጵያን የመታደግ የታመቀ ታላቅ መንፈስ ያለው መልዕክት ነበር። ዛሬ ያየሁት ፍቅር፣ ዛሬ ያየሁት የአብሮነት፣ የሕብረትና የአንድነት መንፈስ ከሰፊው የጣና እንቦጭ ዐረም በላይ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ክፉው ስደት የማያሳይ የማያሰማኝ የለም! (የማለዳ ወግ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ነቢዩ ሲራክ

★ ውሃ የበላው ጎልማሳና እኔ ... ያኔ :(

ውሃ የበላው ጎልማሳ
ውሃ የበላው ጎልማሳና እኔ ... ያኔ

የማወጋችሁ ዛሬ ስለሌለ፣ ትናንት ስለነበረ አንድ ጎልማሳ ወንድም ነው ... ተንከራታች እግሬ የማያደርሰኝ ቦታ የለም፣ ክፉው ስደት የማያሳይ የማያሰማኝ የለም። እኔና ከዚህ በታች የማወጋችሁ ጎልማሳ ወንድም ከሁለት ወር በፊት የሳውዲን የውጡ ምህረት አዋጅ ተከትሎ መልዕክት ልኮልኝ ግንኙነነት ተጀመረ ... ብዙ ሳይቆይ ለዓመታት ይሰራበት ወደ ነበረው የአሲር ግዛት ለኩባንያ ስራ ሳመራ በፊስቡክ የጻፍኩትን መረጃ ተመልክቶ በአካል ሊያገኘኝ እንደሚፈልግ ጠየቀኝ ... ፍቃደኝነቴን ገለጽኩለት ... ደስታው ገልጾልኝ በክልሉ ለስራ ጉዳይ ስተላለፍ ተገናኘን። ለሰዓታት ባንደ ተቀምጠን የሆድ የሆዱን ዘርግፎ እንደ ትልቅ ወንድም አምኖ አጫወተኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የበላችው ያስገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታል

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ምሕረት ዘገዬ

Tana High School, Bahirdar, 2010 [Credit: Chora, Inc.]
ጣና ከፍተኛ ኹለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ባህር ዳር (ፎቶ፣ Chora, Inc.)

በዚህ ዘመን ተማሪዎች “አጤሬራ” የሚሉት ፈሊጥ አላቸው። አጤሬራ ማለት አንድ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ፈተና ክፍል ወይም አዳራሽ ሲገባ ደብቆ ይዞት የሚገባው በአጭር በአጭሩ የተጻፈ ማስታወሻ ማለት ነው። ዘመኑ የኩረጃና የማጭበርበር ነው። ኮራጅና ከማስታወሻ ገልባጭ ተማሪ “እየተመረቀ” አገር ምድሩን እየሞላው ነው። ለማንኛውም ከተማሪዎች ለየት የሚለው የኔ አጤሬራ ከዚህ በታች ይቀጥላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለሚመለከታችሁ ባለሥልጣናት (የማለዳ ወግ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ነቢዩ ሲራክ

* ለአንባሳደር አሚንና ለአንባሳደር ውብሸት ባላችሁበት

* ቅጅ፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት
አንባሳደር አሚን፣ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁና አንባሳደር ውብሸት

መረጃን ማቀበሌ ወንጀል ሆኖ "የነቢዩ ሲራክ ልጆች ከሚማሩበት የጅዳ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት እንዲታገዱ" የሚለው የካድሬዎች ሀሳብ ያን ሰሞን ቀርቦ እንደነበር በድጋሜ በማረጋገጤ አዝኘ ነበር ያደርኩት። ... ስለ እውነት ለመናገር፣ ስለ እውነት እየተገፉ መኖር ግድ ይላል ብዬ የሚሰራው ባይደንቀኝም በዘመነ ኦሪት እንኳ ባልታዬ ህግ ልጆች በአባታቸው "ወንጀል" ስማቸው ሲጠራ መስማት ልቤን በሀዘን ሰብሮት አድሯል። እናም ሁሉንም ለመርሳት ልጆቸን እረፍት ወደ ማይሰማ ወደ ማይናገረው ቀይ ባህር ይዣቸው ዘና ልበል ብዬ ማልጀ ስነሳ ሌላ አሳዛኝ መረጃ ደረሰኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዘፈንና የሙዚቃ ኮታችን እንኳን አይጠበቅልንም?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ምሕረት ዘገዬ (ከአዲስ አበባ)

Ginbot 20
የግምቦት 20 የሙዚቃ ምርጫ። (ምስል ቅንብር፣ ኢዛ)

ይህ በዓል የማን እንደሆነ አሁን ገና በደምብ ገባኝ! “ኢሕአዲግ” የሚባለው የሕወሓት መሀል-አገራዊ የሠርክ መጠሪያም የለየለት ቅጥፈት መሆኑን በዛሬዋ አጋጣሚ ይበልጥ ተገነዘብኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!