የሽምግልናው ነገር (ተመስገን ዘነበ )

ተመስገን ዘነበ

በተናገረበት ተጽፎ በተናገረበት ወይንም በቴሌቭዥንም ሆነ በመድረክ በታየበት ወቅት ነገሬ ተብሎ ትኩረት ያልተሰጠው ድርጊት አንድ ቀን ዐብይ ጉዳይ ሆኖ ብቅ ይልና የመነጋገሪያ አጀንዳ ይሆናል። የቅንጅት አመራሮች “በሀገር ባህልና ወግ መሠረት” በይቅርታ በተፈቱበት ዕለትም ሆነ በሐምሌ 13 ቀን 1999 ዓ.ም. ሰሞን የተሰጡ መግለጫዎችን፣ የተደረጉ ቃለ ምልልሶችን፣ የተነገሩ የተነበቡ ጉዳዩችን ትኩረት ሰጥቶ ከታሳሪዎች መፈታት በላይም አጉልቶ ያጤናቸው አልነበረም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቫንኩቨር ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ውዝግብ በፍርድ ቤት መሰማቱን ቀጥሏል (ዘገዬ በቀለ)

በላይ፣ ሰብለና፣ ኤርሚያስ ከተከሳሽ ወገን ምስክርነታቸውን ሰጡ፤ ታሪኩም ጀምሯል

ዘገዬ በቀለ - ከቫንኩቨር

ሲጀምር፤ ሲንደረደር

“ቄሱ ሥራቸውን ባግባቡ አልተወጡም፣ በጎሣና በዘር ይከፋፍሉን ነበር። ስብከቱን ትተው ፖለቲካ ያስተምሩን ነበር” ደግሞ ደጋግሞ ይሄንን ነው ያለው ሦስተኛው የዕለቱ ምስክር። ያም ብቻ አይደለም። “እኔ ፍጹም ሥልጣን አለኝ፣ የቤተክርስቲያኗም መሪ እኔ ነኝ፣ ያለኔም ፈቃድ ስብሰባም ውይይትም ሊደረግ አይገባም አሉን። ...” ዝርዝሩ ብዙ ነው። አቶ በላይ ከበደ ገለቱ ይባላል። መልከ መልካምና ረጅም ቁመናው ያማረ፣ ሆን ብሎ ያሳስታል ተብሎ የማይገመት የቤተሰብ ሰው፣ የልጆች አባት፣ በሙያው አካውንታንት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሠለጠነ ማኅበረሰብ ከሚጠይቀው የበዛም ያነሰም አንጠይቅም (ፕ/ር አለማየሁ)

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ፕሬዝዳንት ኦባማ በቅርቡ ለቱርክ ሕግ አውጭዎች አንድ ታሪካዊ ንግግር አድርገውላቸዋል፤ ነገር ግን ይህ ንግግራቸው ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለውና እስከ አሁን ይፋ ስላልተደረገው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ጠቃሚ ፍንጭ የሰጠ ነው። ኦባማ ለዓለም ሠላም እየወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ለአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ በጣም አስፈላጊውን ጤንነት ብቻም ሳይሆን የሚመልሰው አሜሪካ ከተቀረው ዓለም ጋር ለሚኖራት መጪ ግንኙነቶች ድጋፍ የሚሰጥ አዲስ ምሰሶ የሚያቆም ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስህተቶችን ለማረም የተፈፀሙ ስህተቶች (ርዕዮት ዓለሙ)

ርዕዮት ዓለሙ

ማንኛውም ግለሰብ፣ ተቋም፣ ድርጅት ወይም መንግሥት በተለይ ከደረሱበት ችግሮች በመነሳት እንደስህተት የሚያስቀምጣቸው ድርጊቶችና አመለካከቶች ይኖሩታል። ግለሰቡ ወይም ድርጅቱ ስህተቶቹን በትክክል መፈተሽ ካልቻለ በእውነተኛ ስህተቶቹ ፋንታ ስህተት ያልሆኑትን እንደ ስህተት ሊወስዳቸው ይችላል። ይህም እውነተኛውን ስህተት በማረም ፋንታ ሌሎች ስህተቶች የሆኑ “የስህተት ማረሚያ እርምጃዎችን” እንዲወስድ በማድረግ ለተደጋጋሚ ስህተት ይዳርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ሕገመንግሥታዊነት፣ ዲሞክራሲና የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እስር” ስየ አብርሃ

የወ/ት ብርቱካንን እስር ምክንያት በማድረግ ዕሁድ መጋቢት 20 ቀን 2001 ዓ.ም. (ማርች 29 ቀን 2009) በአዲስ አበባ ኢምፔሪያል ሆቴል ”ቃሌ” በሚል ስያሜ በተካሄደው ሲምፖዚየምና የሻማ ማብራት ዝግጅት ላይ አቶ ስየ አብርሃ ”ሕገመንግሥታዊነት፣ ዲሞክራሲና የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እስር” በሚል ርዕስ ጽሑፍ አቅርበዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማስታወሻ (ፕ/ር መስፍን)

ለአንድነት ምክር ቤት አባሎች

ፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያም (የካቲት 20 ቀን 2001 ዓ.ም.)

ቅንጅትን ያፈረሰው የጥቂት ሰዎች ግለኛና አምባገነናዊ አሰራር በሌላ መልክ በአንድነት ውስጥ ሲከሰት

መግቢያ

አንድ መሰረታዊ ጥያቄ የሚያከራክር ሆኖ አላገኘሁትም፤ያነጋገርኳቸው የአንድነት አባላት ሁሉ ከመድረክ ጋር መቀራረብ፣ መወያየትና መመካከር አስፈላጊ መሆኑን ያምናሉ። ትልቁና ዋናው ጥያቄ በአንድነትና በመድረክ መካከል የሚፈጠረው ግንኙነት መዋቅራዊ ነው? ወይስ ተግባራዊ? (structural or functional?) የሚለው ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እኩል ስናለቅስ፡ እናታችን የሞተችብንም እናታቸው ገበያ የሄደችባቸውም

የሪፖርተር ዘገባ፤ ባትወዱትም ስሙት

የማነ ናግሽ የሪፖርተሩ ዘጋቢ የማነ ናግሽ፤ የካቲት 11 ቀን 2001 .. ህወሓት የተመሰረተበትን 34 ዓመት  አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ከህወሀት ተወካይ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ተገኝቶ እንዲህ ሲል ዘገበ። በነገራችን ላይ፡ የማነ የሚለውን ስም ስሰማ ድንግጥ እላለሁ። ስመ ሞክሼውን፡ የቀድሞ ወዳጄን ሌላኛውን የማነን ትዝ ስለሚያሰኘኝ ይሆናል። ስለሌላኛው የማነ ሌላ ጊዜ እነግራችኋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብርቱ ካህናችን ካለሽበት ቀድሺ፤ ካለንበት እንሳላለን

ጉዞ ወደ ቃሊቲ፤ በመድረክ “መድረቅ”

አባኪያ - ከሀገረ ካናዳ

የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ ያነበብኩት፡ የአምባሳደር ዘውዴ ረታ መጽሐፍ “የኤርትራ ጉዳይ” ላይ ከቶም የማይዘነጋኝ አንድ ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ ወይንም ወልደዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ ይመስሉኛል ያን ጊዜ በአውሮፓ ሆኖ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ለሚከራከረው አክሊሉ ሀብተወልድ የተናገሩት አረፍተ ነገር አለ። “አንተ ከዚያ በርታ እኔ ከዚህ እበረታልሀለሁ” አይነት ነገር። በዚህ ሰዓት ብርቱካን ያንን የምትችል መሰለኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦ ለኦባማ ነበር፤ የኦባማን ተወጣነው፤ አሁን ኦ ለኦባንግ!!

 የኢትዮጵያዊው ኦባማ ውልደት!!

አፍቃሬ - ኦባንግና ልጅ ተክሌ ከካናዳ

የ2009 ቋንቋችን “ኦባንግ በዲ.ሲ. ለኢትዮጵያ ያሰልፈናል” ቢሆንስ። ኦባንግ ጥቁሩ አይደለም። ኦባንግ አኝዋኩ አይደለም። ኦባንግ ወጣቱ አይደለም። ኦባንግ የኢትዮጵያዊያንን ሁሉ ቁስላትና ህማማት ሊሸከም የተዘጋጀው ኦባንግ ሜቶ። ዋናው ጠላት፣ ዋናው ጅብ ኢህአዴግ ስጋችንን እየበላን፤ እርስ በርስ የምንሻኮትባትን ሳይሆን፤ ቅድሚያ ለጋራ ጠላት የምንሰጥባትን የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ ያነገበውን ኦባንግን ልንከተለው ይገባል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...