የሰው አገርን በመውረር ምን ይገኛል? (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

መስፍን ወልደማርያም (ፕ/ር)

በዛሬው ጊዜ ዓለም አቀፍ ሕጎች፣ በተለያዩ የአካባቢ ማኅበሮችና በተባበሩት የዓለም መንግሥታት ማኅበር ታትመውና ታውጀው፣ ተሰብከው፣ ብዙ ዲስኩሮችም በታላላቅ ሰዎች በተደጋጋሚ ተደርጎባቸዋል። ከብዙ ዓመታት በፊት ቻይና ቲቤትን ስትውጥ፣ ለጥቂት ጊዜ ተወራና ተረስታ፤ እኛም ካልረሳነው ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ስትወር እንዲሁ ነበር፤ ዛሬ እኛም ወግ ደርሶን ከወራሪዎች ጋር መሰለፋችን በሰፊው እየተወራ ነው። አሁን ደግሞ የአውሮፓ ሕብረት “ቲቤት የቻይና አካል ነች” ብሎ ዐወጀ ይባላል። እንግዲህ ወረራ በይርጋ ይጸድቃል ማለት ነው፤ ጉልበተኞች ጨክነው ዘመናትን ካስቆጠሩ፣ ወረራው በይርጋ እንደሚጸናላቸው አዲስ ትምህርት እየተገኘ ነው። አሜሪካ በኢራቅ ስድስተኛ ዓመቱን እያስቆጠረ ነው፤ ስንት ዓመት ይቀረዋል? ሆኖም የአሜሪካ መንግሥት ከህዝብ ፈቃድ ውጭ ጉልበት የለውምና ወረራው በአሜሪካ ህዝብ ትዕዛዝ የሚያበቃበት ጊዜ ያለ ጥርጥር ይመጣል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጎንደር የሱዳኖችን ጥቃት በተመለከተ (ግርማ ካሣ)

Atsé Yohanesግርማ ካሣ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

(ሚያዝያ 24 ቀን 2000 ዓ.ም. May 2, 2008)

“ዐፄ ዮሐንስ ይዋሻሉ

መጠጥ አልጠጣም ይላሉ

ሲጠጡ አየናቸው በርግጥ

እራስ የሚያዞር መጠጥ”

 

ይህ ለዐፄ ዮሐንስ አራተኛ የተገጠመ ቅኔ ነበር። ሰሙ፣ ዐፄ ዮሐንስ መጠጥ አልጠጣም እያሉ የሚያሰክር መጠጥ ሲጠጡ እንደሚታዩ የሚገልጽ ሲሆን፤ የቅኔው ዋና መልዕክት - ወርቁ ግን የእኝህን ታላቅ ኢትዮጵያዊ የደም መስዋዕትነት ያሳያል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"የሞራል እኩልነት ጥያቄዎችና የአመለካከት ችግራቸው" ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቅዳሜ ሚያዝያ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. (አፕሪል 19 ቀን 2008 እ.ኤ.አ.) በቶሮንቶ ከተማ ካናዳ ከኢትዮጵያውያኖች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ "የሞራል እኩልነት ጥያቄዎችና የአመለካከት ችግራቸው፤ ምን ያህሉ ከተግባር ለመራቅ የሚደረግ እራስን የመሸንገያ መሣሪያ ነው?" በሚል ርዕስ ንግግር አድርገዋል። ሙሉ ንግግሩን በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ። (Read on PDF)


አፍሪካና ምርጫ (ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም)

Prof. Mesfin Woldemariamመስፍን ወልደማርያም (ፕ/ር) - ሚያዝያ 2000

ምርጫ የነፃ ሕዝቦች መግለጫ ነው፤ ነፃ ሕዝቦች የአገራቸውንና የመንግሥታቸው ባለቤቶች ናቸው፤ ስለዚህም ምርጫ የአገራቸውና የመንግሥታቸው ባለቤትነታቸውን የሚያረጋግጡበት ዘዴ ነው። በአንፃሩ ደግሞ ነፃ ላልሆኑ ሕዝቦች ምርጫ ለሕዝቡ ፋይዳ የሌለውና የገዢዎቹን ጅራፍ ለመጎንጎኛ የሚያገለግል እጅ መንሻ ነው፤ በአፍሪካ ምርጫ የሚባለው የሁለተኛው ዓይነት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፍትህ ማሽቆልቆል ጉዞ በኢትዮጵያ (ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም)

ከዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማሪያም

1. መነሻው

አንድ ማኅበረሰብ እንደ ማኅበረሰብነቱ እንዲቀጥል ከተፈለገ በረቀቀ መልኩም ይሁን በግርድፉ የህዝብ መስተጋብሮችን የሚያስተናግዱ፣ የሥራ ኃላፊነትንና ድርሻን የሚያደላድሉ፣ መሠረታዊ ፍላጎቶችን የሚያሟሉ ሕጎች መኖር የግድ ይላል። በመሆኑም እንደ አንዳንድ ጥንታዊ የዳበረ ኅብረተሰብ ኢትዮጵያዊያን ያለ ሕግ የኖሩበት ጊዜ የለም ማለት ይቻላል። ከዚያም አልፎ ዛሬ ሕጎቻቸው ዳብረው፣ ፍትሕ ሰፍኖባቸው፣ ህዝቡ መብቱ ተከብሮለት፣ ነፃነቱ ተጠብቆለት የምናያቸው ብዙዎቹ የዓለም መንግሥታት ባልተፈጠሩበት ዘመን በኢትዮጵያ በጽሑፍ የሰፈሩ የህዝቡን መስተጋብር የሚያስተናግዱ፣ የነገሥታቱና የባላባቱ ሥልጣን ስፋትና ወርድ ዳር ድንበሩን የሚከልሉ፣ በዳይን የሚወቅሱ፣ ተበዳይን የሚክሱ ሕግጋት ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እኛ እና ፌሽት (ያሬድ ክንፈ)

ያሬድ ክንፈ ከስዊድን (ሀገር ቤት ላለ ወዳጅ የተጣፈ) ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

Teddi on stage in Stockholmጌትዬ! ከነመላው ቤተሰብህ መልካም የገና በዓል ይሆንልህ ዘንድ ከልቤ እመኛለሁ!

 

እዚህ ስዊድን ውስጥ የኢትዮጵያን ገና ምክንያት በማድረግ ቅዳሜ ታህሳስ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. (ዲሴምበር 29 ቀን 2007 ዓ.ም.) ፌሽታ ተደርጎ ነበር። ዋና ከተማዋ ስቶክሆልም ውስጥ ሊልሆልመን እተባለው ክፍለከተማ በኢድሮትስሐለን አዳራሽ ውስጥ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ (ለእሁድ አጥቢያ) 10 ሰዓት ድረስ ነበር ዝግጅቱ። መድረኩን ተቆጣጥሮት የነበረው ተወዳጁ ቴዲ አፍሮ (ቴድሮስ ካሣሁን) ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዳንኤልና ነፃነት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

Prof. Mesfin Woldemariamከፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም - መጋቢት 2000

በጥቅምት 1998 ዓ.ም. ላይ የሚያዝያ 1997 ዓ.ም. የህዝብ ስብሰባ እና ተከታትሎ የመጣው ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ ለነፃነት ያለውን ቁርጠኛ ፍላጎት አሳየ፤ ተደላድለው የነበሩ ወንበሮችን አነቃነቀ፤ በትምክህት አብጠው የነበሩትን ሁሉ ልባቸውን በፍርሃት አርበደበደው፤ ከታች መሰረት፣ ከጎን ምሰሶ፣ ከላይ ጣሪያ የሌላቸው መሆናቸውን ያለጥርጥር እንዲገነዘቡ አደረጋቸው፤ ጭካኔ ከፍርሃት ተለወደ። የፍርሃት ልጅ ያስከተለው መዘዝ ወዳጅንና ጠላትን የመለየት ችሎታችንም እስከመንሳት ደረሰ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከመናቆር መነጋገር ይበጃል (ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም)

ከዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 5 ቀን 2000 ዓ.ም. March 14,2008) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29፣ ግለሰቦችም ሆኑ ፕሬስ ወይንም ሌሎች መገናኛ ብዙኀን ሃሳባቸውን በነፃ የመግለጽ ተፈጥሮአዊ መብት ያረጋግጥላቸዋል። የአሜሪካ ሕገ መንግሥት እነዚህን መብቶች ከማረጋገጥ አልፎ እንዲያውም ኮንግሬስ ይህንን መብት ለመገደብ ሕግ ሊያወጣ እንደማይችል ይደነግጋል። ይህ የንግግርና የጽሁፍ ነፃነት ይህን ያህል ዋጋ የሚሰጠው ያለ ፕሬስ ነፃነት ዲሞክራሲና የተመጣጠነ ክብር ያለው ኑሮ ለመኖር የሚያስችል ልማት ፈጽሞ የማይታሰብ በመሆኑ ነው። የፕሬስ ነፃነት መዳበር ወይንም መቀጨጭ አንድ አገር በሥልጣኔ ምን ያህል ወደፊት እንደመጠቀ ወይንም ምን ያህል ወደ ኋላ እንደቀረ የሚጠቁም ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...