ወታደር ”በአማራ ማንነቴ ተጠቃሁ” ሲል ያናድዳል፤ ያበሳጫልም፤ ወታድርነቱ የት ገብቶ ነው?

አርሶ አደር ተገፋሁ ብሎ መሬት ቢጭር ያሳዝናል። መገፋቱም ያበሳጫል። ወታደር በአማራ ማንነቴ ተጠቃሁ ሲል ግን አያምርም!

ሸንቁጥ አየለ

በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ሰሞኑን የተለቀቀውን እና ወታደሮች በአማራ ማንነታቸው ጥቃት ደረሰባቸው የሚለውን መረጃ እያነበብኩ በጣም ገረመኝ። መገረምም ብቻ ሳይሆን ብዙ ጥያቄዎችም በሕሊናዬ ተመላለሱብኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በጎ ጅማሪዎችና ቀጣዩ ፈተና

Dr. Abiy Ahmed

በቀለ ደገፋ

ዶ/ር ዐቢይ ጠ/ሚ ሆኖ ከተመረጠ በኋላ በበጎ የሚነሱና አንዳንዴም በዚህ ፍጥነት ይሆናሉ ተብሎ የማይጠበቁ ነገሮችን አድርጓል፤ የለማና የገዱ ከእሱ ያልተናነስ አስተዋፆ ሳይዘነጋ። ከእነዚህም ውስጥ ጎልተው የሚወጡት ስለኢትዮጵያዊነት መናገር እንደ ወንጀል መቆጠሩ ቀርቶ ሊኮራበት የሚገባና ብዙ ዋጋ የተከፈለበት መሆኑን ማሳየቱ፤ በኦሮሞ ወገኖቻችን ዘንድ የነበረውን አንዳንድ ጥርጣሬ አስውግዶ ኦሮሞ ከሌላው ሕዝብ እኩል መሥዋዕትነት ከፍሎ ባቆያት አገር ውስጥ ሆኖ የፍትሕና የእኩልነት ጥያቄውን ማስመለስ እንደሚችል ማሳየቱ፤ በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ለእስርና ለእንግልት የተዳረጉ ወገኖቻችንን ከእስር እንዲፈቱ ማድረግ፤ ለዚህም አንዳርጋቸው ፅጌን ከመፍታት የበለጠ ምንም ዐይነት ማስረጃ አያስፈልግም። አንዳርጋቸው ምንም እንኳን ምርጥ የፍትሕና የእኩልነት ታጋይ ቢሆንም፤ ከመረጠው የትግል መንገድ አንጻር እንዲፈታ መደረጉ በቀላሉ ሊታይ አይገባውም። ለለውጥ ያለውን ቁርጠኝነት ያመላክታል። ቂመኞቹ አሁንም ከአገር አንጋግተው ሊያባርሩት ሲያሴሩ ዶ/ር ዐቢይ በክብር ቤተመንግሥት ጠርቶ በማናገሩ ያልተደመመ ያለ አይመስለኝም። የታሰሩትን ከመፍታት በተጨማሪ በተፈበረከ የአሸባሪነት ክስ ለስደት የተዳረጉ ምርጥ ኢትዮጵያዊያንን ክስ ማንሳትና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡ ሌላው ወሳኝ እርምጃ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጥብቅ ማሳሰቢያ ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ - እኔም በሀገሬ ያገባኛል!

 Abiy Ahmed and Lemma Megersa

ምሕረት ዘገዬ

መረጃ አይናቅም። መረጃ ሁሉ በግርድፉ እንደ እውነት አይወሰድም። መረጃዎች እንደየምንጫቸው ሰውን/ተቋምን ለማሳሳት፣ ለማደናገር፣ ለማስፈራራት፣ ለማስጠንቀቅ፣ ለማሳወቅ፣ ወዘተ ... ይለቀቃሉ። ጥንቃቄ ማድረግ የሚያሻው መረጃ ተጠቃሚው ወገን ነው።

ጠ/ሚ ዐቢይ ሥራው የተቃና ይሆን ዘንድ፣ እኛም ዜጎች የሚታየንን ባሉን ማስንተፈሻዎች እንጠቁማለን፤ ሰሚ ካገኘን እሰዬው። ሰሚ ባናገኝ ቢያንስ ከኅሊና ወቀሳ እንድናለን። የሚነገሩ ሁሉ እውነት ሊሆኑ እንደማይችሉ ሁሉ፤ የሚነገሩ ሁሉ ሐሰት ሊሆኑም አይችሉም። የአንድ መሪም ሆነ ጉዳዩ የሚመለከተው ወገን ዋና ኃላፊነት እውነቱን ከውሸቱ አበጥሮ የመለየት ትልቅ ተግባር ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሲናሪዎቹን (ቢሆኖችን) መደርደሩ ፍኖተ ካርታን በጋራ መንደፉን ይተካልን?

ዐቢይ አሕመድ

ዩሱፍ ያሲን (ኦስሎ ኖርዌይ)

በዛሬይቷ ኢትዮጵያችን ተስፋም፣ ስጋትም፣ ሰፍኗል። ጎን ለጎን እርግጥ ተስፋ መሰነቁ ሚዛን እየደፋ መምጣቱ አይካድም። መዳረሻችን በውል ባለመታወቁ ጉዟችንን በጥርጣሬ ዓይን የሚመለከቱ ወገኖች በዚያኑ መጠን እንዳሉ መቀበል የግድ ይላል። ደስ በሚያሰኙ ቸር ወሬዎች እየተንበሸበሽን ነን። ባንጻሩ ተስፋን የሚያደበዝዙ ዜናዎች ያንገላቱናል፣ ያላጉናል ብንል ማጋነን አይሆንብንም። There is Good news ብለው በኋላ There is bad news በማለት አሜሪካኖቹ እንደሚጠርቁት መሆኑ ነው። በየቱ እንጀምር? ከነጸሎቱ «ቸር ወሬ ያሰማን!» ስለሆነ ወጉ፤ ደግ ደጉን ላስቀድም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ESFNA - የሕወሓት የሰሜን አሜሪካ ቅርንጫፍ

የሰሜን አሜሪካ ስፖርት እና ባህል ፌስቲቫል (ESFNA) አመራሮች

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

አንድን ሰው ወይም ድርጅት መፈረጅ ቀላል ነው። ፍረጃ ደግሞ እንደተመልካቹ ነው። አሁን በአጭሩ የምናገረው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች የስፖርት ፌዴሬሽን ስለሚባለው የቦሌ ሞልቃቆች - የፈረንሣይ ልዕልቶች ስብስብ ነው። የካሣ ዳምጤ ልጅ (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ) መሸፋፈን አያውቅም። ከአንጀቴ የወጣ ብሶቴን በጥሞና አድምጡ። ለዚያውስ ይህን ጽሑፍ የሚያወጣልኝ ድረገጽ ሳገኝ አይደል? ዓለም የምትንሰፈሰፈው ላለው ነው፤ ድሃን የምትጸየፍ ዓለም የኔን ብሶት ለማድመጥ ጊዜም የላት። የሚያስተናግደኝ አንድ እንኳን ባገኝ ዕድለኛ ነኝ። በውነት በጣም ተናድጃለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማይታመን እውነት! (ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ የተላከ ጠቃሚ ደብዳቤ!!)

Andargache Tsge and PM Dr. Abyi Ahmed

ብሥራት ደረሰ (ከአዲስ አበባ)

የትናንትናዋ ዕለት እጅግ ታሪካዊት ናት። ይህችን የመሰለች ታሪካዊት ቀን ትመጣለች ብሎ የጠበቀ ወይ ያሰበ ካለ በርግጥም ነቢይ መሆን አለበት። ቀኒቱ ለዘላለም ልትዘከር ይገባታል። በአንድ በኩል የወያኔን አገዛዝ የሚነቅፍ በሌላ በኩል አንዳርጋቸው ፅጌን በአንድ ወይ በሌላ ምክንያት የሚፈራም ሆነ የሚጠላ ግንቦት 21/2010 ዓ.ም.ን ቢያስባት በኢትዮጵያ መፃዒ ዕድል ላይ ጭላንጭል ብርሃን መፈንጠቁንና በእግረ መንገድም ፍትህ-ወዳድ መሆኑን ይጠቁማል። “ከመረቁ አውጡልኝ ከሥጋው ጦመኛ ነኝ” ማለት አይገባም። የአንዳርጋቸው መለቀቅ ካላንዳች ቅድመ ሁኔታ ሁላችንንም ሊያስደስት የሚገባ ያልተጠበቀ ክስተት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፈ የግል ደብዳቤ (ትርጉም ከንግሊዘኛ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም.
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

“እንደማንኛውም ተራ ደቡብ አፍሪካዊ ዜጋ ዕለት በዕለት የምናከናውናቸው ተግባራት የሰው ልጆች በፍትህ ላይ ያላቸውን እምነት እና በእራስ የመተማመን መንፈስ በማጠናከር ለሁሉም ሕዝብ የተመቸ እና አንጸባራቂ ሕይወት ለማስገኘት እንዲቻል ይህች ቆንጆ የሆነች ሀገር በፍጹም በፍጹም እንደገና አንዱ በሌላው የማትጨቆን እና የዓለም ሁሉ ውራጅ እንዳትሆን ጠንክረን መስራት አለብን።” ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ እ.ኤ.አ በ1994 ካደረጉት የመክፈቻ ንግግር የተወሰደ

ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣

ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሾምዎ ልባዊ የሆነ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክቴን ይቀበሉኝ። የኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ አባል በኢትዮጵያ በጣም ከፍተኛውን የስልጣን እርካብ ተቆናጥጦ በማየቴ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአማራ ክልል ኦሮሞኛ መሰጠት የለበትም የሚሉ፤ በስሜት ሳይሆን በመረጃ ይከራከሩን

ግርማ ካሳ

በቅርቡ እኔም ያለሁበት የምሁራንና አክቲቪስቶች ስብስብ ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአማራ ክልል ከአማርኛ ከእንግሊዘኛ በተጨማሪ ሦስተኛ ቋንቋ እንዲሰጥና ሦስተኛው ቋንቋም አሮምኛ ከሆነ በላቲን ሳይሆን በግዕዝ ፊደል እንዲጻፍ የሚጠይቅ፣ ከአባሪ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ደብዳቤ ጽፏል። ደብዳቤው የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የተከበሩ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ይፋዊ ድጋፍ ያገኝ ሲሆን፣ ከሁሉም ማዕዘናት ኢትዮጵያዊያን አዎንታዊ ምላሽ እየሰጡበት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወያኔን ግድያ ለማስቆም የአንድ ሲቪል ኢትዮጵያዊን ሕይወት በአንድ ሲቪል ወያኔ መበቀል የግድ ያስፈልጋል

ዘመቻ ራስ አድን

የወያኔን የሰላማዊ ኢትዮጵያውያንን የግድያ ዘመቻ ለማስቆም የምንችልበት ያለን አማራጭ ይህ ብቻ ነው። ወያኔ የወጠነው በግድያ፣ በእስራትና በማሰቃየት የኢትዮጵያን ሕዝብ የለውጥ ፍላጎት ለመግደል ነው። በወያኔዎች ስሌት ለውጥ፣ ሪፎርም፣ ፍትሕ ወይም እኩልነት ማለት ከመቶ ፐርሰንት ወደ አምስት ፐርሰንት መውረድ ማለት ነው። ይህንን እውነታ ወያኔዎች በውይይትና በጸጋ ይቀበላሉ ብሎ መድከም ሠይጣናዊ የሆኑትን ወያኔዎች ስለሰላም ማሰብ ይችላሉ ብሎ መገመት ሊሆን ይችላል። አንድ አፈጣጠሩም ሆነ አስተዳደጉ ሠይጣናዊ የሆነ ድርጅት በምን ተዓምር ቢሆን ነው በቅፅበት ወደ ሰላማዊነት በቀላሉ ሊቀየር የሚችለው። ስለዚህ በተባበረ ሕዝብ፣ በተቀናጀና በዕውቀት በሚመራ ትግል፣ አስገዳጅና ጨካን ያለ ኃይል በሚጠቀም የትግል ስልት ሕወሓት ካልተንበረከከ በስተቀር ወያኔዎችን በውይይትና በተበታተነ ሕዝባዊ አመጽ ብቻ ግድያቸውን ሊያቆሙ አይችሉም። ወያኔ በውይይት አይለወጥም ወይም አይሻሻልም። የወያኔን ግድያ ካላስቆምን በሰላማዊ ትግሉ ድል ለመጎናፀፍ መስዋዕትነቱ የበዛ፣ ጊዜውም የረዘመ ሊሆን ይችላል። ወያኔዎች በመግደልና በማሰር ሕዝባዊ ትግሉን መደፍጠጥ እንደሚገባና እንደሚችሉ በመቀሌ ስብሰባቸው ውሳኔ ያሳለፉበት ጉዳይ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!