ጦርነቱ የአፍሪካውያን ሳይሆን የአሜሪካና የአውሮፓ ጦርነት ነው!

ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

ሻለቃ ዳዊት በቅርቡ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ስለሚካሄደው ጦርነትና ስለኢኮኖሚ ዕድገት ለሰጠው ሐተታ መልስ

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

መግቢያ

ሻለቃ ዳዊት ብቻ ሳይሆን እንደሱ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸው ምሁራን በተለያየ ወቅት የዓለም አቀፍንም ሆነ የአገራችንን ፖለቲካ በሚመለከት በጽሑፍ መልክ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። በአቀራረባቸውም አንዳንድ የዋህ ኢትዮጵያውያንን ቀልብ የሳቡና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውን ናቸው እስከማለት አድርሷቸዋል። ይሁንና አንባቢው እነዚህ ምሁራን የሚሰጡትን አስተያየትና ሐተታ ለመረዳት የፍልስፍናቸውን፣ የቲዎሪዎቻቸውንና የሳይንሳቸውን መሰረት ይጠይቅ አይጠይቅ እንደሆን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። አብዛኛውን ጊዜ አንዳንድ ጽሑፎች በጥሩ የእንግሊዘኛም ሆነ የአማርኛ ቋንቋ ተጠናቅረው በሚቀርቡበት ጊዜ አንባቢው የይዘታቸውንና የሐተታዎችን የኢንፎርሜሼን ምንጭ ሳይመረምር ዝም ብሎ በመቀበል ትክክል ናቸው ብሎ ይደመድማል። እንደምከታተለው ከሆነ አብዛኛዎቹ አንባቢዎች እንደዚህ ዐይነቱን የሻለቃ ዳዊትን የመሳሰሉ ጽሑፎች ውስጣዊ ይዘት ለመመርመርና በተመሳሳይ አርዕስት ላይ ከሚጽፉ፣ ይሁንና ደግሞ በተለየ መልክ ከሚያቀርቡ ሰዎች ጋር የማወዳደር ጊዜና ገት ስለሌላቸው ከአንድ ወገን ብቻ የሚመጣውን ኢንፎርሜሽን አንብበው ትክክል ነው ብለው በመቀበል አላስፈላጊ ድምደማ ላይ ይደርሳሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፖለቲካውን ምስቅልቅል ተረድተህ ጽንፈኛ፣ ቁርጠኛ ብሎም ጦረኛ እስክትሆን፤ አገርና ሕዝብ ከቶም አይኖርህም

ዐፄ ቴዎድሮስ

ሸንቁጥ አየለ

የፖለቲካው ምስቅልቅል

አሁን ያለው የፖለቲካ ምስቅልቅል እውነትና ገጽታው ምን ይመስላል?የጠላት አቋሙስ ምን ይመስላል? ወያኔ ምን እየሰራች ነው? አጠቃላይ የፖለቲካው ትርምስምሱ እንዴት ይገለጻል ብለህ እራስህን ጠይቅ። ከአንድ እስከ አስር ያሉትን ነጥቦች አንድ በአንድ በስፋት እያብራራህ ከእውነተኛ የትግል አጋሮችህ ጋር ብቻ እጅግ ጥልቅ ውይይት አድርግባቸው። እዚህ በደምሳሳው የተሰጡትን ነጥቦች በምሳሌ እያሰፋፋህ የፖለቲካውን ምስቅልቅል መጀመሪያ አጥብቀህ ተረዳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለአህመዲን ሕክምና ስጡት፣ ፍቱትም! (የማለዳ ወግ)

Ustaz Ahmedin Jebel

* ፍትሕ ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል!

* በግፍ አስሮም ሕክምና መንፈግ ለምን?

* ሐሳብን የደፈረው ጀግና ...!

ነቢዩ ሲራክ

የወንድም ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን በእስር ላይ ሕክምና መነፈጉን ከተለያዩ ምንጮች ለማረጋገጥ ችያለሁ። በእስር ላይ ያሉ ወገኖችን በሕገ መንግሥትና በዓለም አቀፍ ሕግ የተደነገገ እየተጣሰባቸው ነው። በሕግ ስር ባለው ኡስታዝ አህመዲንና በብዙ ታሳሪዎች መንግሥት የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸመባቸው ተደጋግሞ ተመልክተናል። ዛሬ አደባባይ በአህመዲን ያየነውም ይህንኑ ነው። በኡስታዝ አህመዲን ሰውነት ላይ የሚታየውን ጉዳትና መጎሳቆል ስመለከት የተሰማኝ ስሜት ደስ አይልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦቦ ለማን ያናገራቸው እምነት ወይንስ ስሜት

Lemma Megersa

ይገረም አለሙ

የኦሮምያ ክልል ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ ባህር ዳር ተገኝተው ከተናገሩት መካከል ”ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” የሚለው አስደማሚ ቃል የሚገኝበትን ክፍል በጨረፍታ የሰማሁት ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛው ክፍል ነው። ሰምቼ ሳልጨርስ ስሜቴ ተለዋወጠ፣ ለራሴም ልረዳው ባልቻልኩ ሁኔታ የለቅሶ ስሜትም ተሰማኝ። በዚህ ስሜት ውስጥ ሆኜ ፈጥነው ወደ አዕምሮዬ የመጡት አይታክቴው አባት ምሁር ፕ/ር መስፍን ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ወያኔም ማታለል፣ እኛም መታለል ችሎታችን ነው!"

ወያኔ

ፊልጶስ

አሁን … አሁን ”'ከልሂቃኑ እስከ ኢ-ልሂቃኑ” ድረስ፤ ቀድም ብሎ ሙሶሎኒያዊያንና ሂትለራዊያን፤ ካለፉት ሃምሳ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ሻዕቢያዊያንና ወያኔያዊያን፤ እንዲሁም ኦነጋዊያን ከባንዳ አያቶቻቸውና አባቶቻቸው የተቀበሉትን የፈጠራና የጥላቻ ታሪክ ስላወሩትና የሥልጣን ኮርቻውን ስለተፈናጠጡት፤ የሚናገሩትና የሚጽፉት ሁሉ እንደ እውነት ተቆጥሮ፤ “በኢትዮጵያ ሕዝብ መኻል ጥላቻና በደል አለ!” መባሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለኦሕዴድና ብአዴን፤ ኢትዮጵያዊነቱም፣ አንድነቱም ከመፈክር እንዲያልፍ

አቶ ለማ መገርሳ

ያሬድ ኃይለማርያም

የመጠፋፋት ዜና በሰማንበት ማግስትና ዘረኝነት ነግሦ አንዱ ኢትዮጵያዊ ሌላውን በማንነቱ ብቻ ሲያገል፣ ሲገል፣ ሲያፈናቅልና ሲያዋርድ እያየን ባለንበት በዚህ ክፉ ወቅት፤ ከወደ ባህር ዳር ከተማ የተሰማው ዜና፤ ኦሕዴድና በብአዴን ያሳዩት የአንድነት ስሜትና ኢትዮጵያዊነትን የማስቀደም መንፈስ ይበል የሚያሰኝ ነው። ይሁንና እነዚህ ድርጅቶች ከዳንኪራና ከሆይ ሆታ ባለፈ አገሪቱ የተጋፈጠችውን አስፈሪና ውስብስብ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተወሰኑ እርምጃዎችን ወደፊት መራመድ ካልቻሉ፤ የዛሬው ንግግራቸው ከባዶ ፕሮፓጋንዳነት የዘለለ ሊሆን አይችልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ንጉሠ ነገሥት የሌላቸው የኢትዮጵያ ንገሦች

Bekele Gerba

ይገረም አለሙ

“አይተዳደርም ሁለት ኮርማ አንድ ቤት

አንዱ ተሸንፎ ካላለ አቤት አቤት” ውርሰ ቃል

በዘመነ መሳፍንትም በሉት በፊውዳሉ፣ በአጼውም ይሁን በወታደራዊው ወይንም በተጋዳላዮቹ በየትኛውም የኢትዮጵያ የመንግሥትነት ዘመን አንድም በሕገ ሥርዓቱ አለያም በጉልበቱ የነገሠ ንጉሠሠ ነገሥት ነበር። በመሆኑም በየአካባቢው ራሱን የሚያነግሠውም ሆነ በንጉሠ ነገሥቱ የሚሾመው ንጉሥ እንዳሻው አይሆንም። ሥልጣኑ ገደብ ኀላፊነቱ ልክ አለው። ጡንቻው ሕሊናውን አደንዝዞት፣ አለያም ከማን አንሼ እብሪት ተጠናውቶት ራሴ ንጉሥ ነኝ የምን ለንጉሥ ማደር ነው ብሎ ያሻውን ለመሥራት ቢሞክር፣ ትዕዛዝ አልቀበል አላከብር ማለት ቢዳዳው በንጉሠ ነገሥቱ ትዕዛዝና ውሳኔ አንድም በሕግ እንዲያም ካለ በጉልበት አቅሙን እንዲያውቅ ልኩን እንዲረዳ ይደረጋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኛ ሰው በሄግ ችሎት

Eshetu Alemu

ክንፉ አሰፋ (ዘ ሄግ)

ለ25 ዓመታት በኔዘርላንድ ውስጥ ሲኖር ሰብአዊነት ማለት ምን እንደሆነ በደንብ የተረዳ ይመስላል። ምዕራባውያን ለሰብአዊ ፍጡር የሚሰጡትን ዋጋ ሳይገነዘብ አልቀረም። አምላክ በአምሳሉ የፈጠረው የሰው ልጅ ሕይወት ቀርቶ ለእንሰሶች ሕይወት የሚሰጠውን ክብር ሌት ተቀን እያየ የአመለካከት ለውጥ አያደርግም ብሎ ለመናገር ይከብዳል። እዚህ ሰብአዊ ፍጡርን በፖለቲካ አመለካከቱ መግደል ከቶውንም አይታሰብም። መግደል አይደለም የሰው ልጅ ላይ እጁን የሚያነሳ፣ ጸያፍ ስድብ ከአንደበቱ የሚያወጣ እንኳ ባለሥልጣን ቢኖር ዋጋ ይከፍላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራ ሕዝብ ሞቱ ሲዘገብ እንዴት ሆኖ ነው ወንጀል የሚሆነው? ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋውን እንደማሳያ

Muluken Tesfaw

ሸንቁጥ አየለ

ጥቅል ሃሳብ

የሞተው ወገን መከፋት ሲገባው ሞትህ በመነገሩ ለምን ትንፍሽ ትላለህ ብሎ ሰውን መውቀስ አስደማሚ ነው። ገዳይ እና አስገዳይን መውቀስ እና መገሰጽ ቢቻልም ተባብሮ ለፍርድ ማቅረብ ሲገባ ለምን የሞተው ሰው ተገደለ ብለህ ትናገራለህ ብሎ ስለፍትሕ የሚጮህን ሰው መክሰስ አስደናቂ ብቻ ሳይሆን፤ በዓለም ላይ የመጨረሻው የግፍ ግፍ ነው። አማራ ሕዝብ ላይ ከሚደረገው የግድያ ወንጀል የበለጠው ግፍ ለምን የአማራ ሕዝብ ሞት ተዘገበ ብሎ በድፍረት መናገር ነው።

ሰሞኑን ከማስተውላቸው አስገራሚ ነገሮች የአማራ ሕዝብ በየቦታው ሲታረድ ለምን ታረደ፣ ተገደለ እያላችሁ ትዘግባላችሁ የሚል ነው። በተለይም ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ጊዜውን ሰጥቶ የአማራን ሕዝብ በየቦታው መታረድ እና መገደል እየዘገበ ሰነበተ። እናም ዘይገርም የሚባለው ነገር የሚከተለው ታዲያ ይሄኔ ነው። የአማራ ሕዝብ ሞቱ መዘገቡ ዘረኝነት ነው፣ የኢትዮጵያን አንድነት ለማናጋት ነው የሚል ትችት በብዛት ይደመጣሉ። የአንድ ሕዝብ መገደል፣ መታረድ እና መሰደድ አለመዘገቡ ለአገር አንድነት ፍቱን መድኃኒት እንዴት ሊሆን እንደሚችል ደጋግሜ ባስበውም ጠብ የሚል ምክንያት አላገኘሁም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተደራዳሪ ወይንስ ተባባሪ

አጋዚ ጦር

ይገረም አለሙ

የተረገምንበት ጊዜና ምክንያቱ
አልታወቅ ብሎ ከጠዋት ከጥንቱ
ከትውልድ ትውልድ እየተሻገረ
ይላላል ያልነው ብሶ እየከረረ
ችግር በሽታችን ዘመን አስቆጠረ፤
ከእውነተኛው ታጋይ - የአስመሳዩ ቁጥር እጅግ ስለላቀ፣
ግድያ ፍጅቱ ከአደባባይ አልፎ እስር ቤት ዘለቀ።

2010 ከባተ ገና ሁለተኛ ወሩን ያልጨረሰ ቢሆንም፤ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ ያየን የሰማናቸው ነገሮች ፖለቲከኛ ነኝ ለለውጥ እየታገልኩ ነው የሚሉትን ቀርቶ ማናቸውንም ሰው የሆነ ፍጡር ሁሉ እንቅልፍ የማያስተኛ ነበር። በምሥራቁ የአገራችን ክፍል የተፈጸመውን ሰምተን ከንፈር መጠን አጀኢብም ብለን ሳናበቃ (የእኛ ተቃውሞም ሆነ ቁጣ ከዚህ አይዘልም) ኢሉባቡር ላይ ሌላ ፍጅት ሌላ አልቂት ተፈጸመ። ይህኛውን ገና በወጉ አዝነንበት አይደለም አውርተንበት ሳንጨርስ ከትናንት በስቲያ አምቦ ላይ ሌላ የግፍ ግድያ ተፈጸመ። በእኔ አረዳድ የአንቦው ሁለት መሰረታዊ ልዩ ገጽታዎች ተንጸባርቀውበታል። የመጀመሪያው የወያኔ ቅኝ ገዢነት የተረጋገጠበት ሁለተኛው የኦሕዴድ ሰዎች ትእግስት በሉት ሎሌነት ወደ ጫፍ እየደረሰ መሆኑ መታየቱ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!