“እርካብና መንበር”ን አየኋት፤ ኢትዮጵያ እርምሽን አውጪ!

እርካብና መንበር

ገ/ክርስቶስ ዓባይ

“እርካብና መንበር” በ'ዲራአዝ' የብዕር ስም የተጻፈች እጥር ምጥን ያለች መጽሐፍ ናት። መጽሐፏ እጅግ በሠፊው የተወራላት በመሆኗ በእጄ እንደገባች በጥንቃቄ እና በጥሞና ማንበቤን ቀጠልሁ። ጸሐፊው ያላቸውን ራዕይና የሞራል ጥንካሬ በሚገባ አይቼበታለሁ። ከልብ በመነጨ ስሜትና ጉጉትም እንደተጻፈ ለመገንዘብ ችያለሁ። ምናልባት ጸሐፊው የአስተዳደርን ጥበብ ለማወቅ፤ አንድም በተወሰነ ርዕስ ላይ በአተኮረ ጥናት መጻሕፍትን ሲበረብሩ፤ አልያም ስለአመራር የተለያዩ ሥልጠናዎችን የመካፈል ዕድል ያጋጠማቸው እንደነበር መገመት አይከብድም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊነት፤ ሰው የመኾን ሕይወትን የሚያቀነቅነውን የ‘ምሥራቃዊት ኮከብ’ ፖለቲካዊ ልቦለድ ድርሰትን በጨረፍታ

ምሥራቃዊት ኮከብ
ኒቆዲሞስ

እንደ መንደርደሪያ

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት/የኢኮኖሚክስ ምሩቅ፣ የዓለም ሰላምና ዕርቅ ግብረ ሠናይ ድ/ት የሥራ ባልደረባና የኢኮኖሚክስ መምህር የሆነው ወጣቱ ጸጋዘአብ ለምለም ተስፋይ በ2010 ዓ.ም. ባሳተመውና በ336 ገጾች በተቀነበበው በ‹ምሥራቃዊት ኮከብ› ፖለቲካዊ ድርሰት ላይ በጥቂቱ የግሌ ምልከታና አስተያየት የተካተተበት የወፍ በረር ዳሰሳ ለማድረግ ወደድኹ። በቅድሚያ ግን በመጽሐፉ የፊት ሽፋን ገጽ ላይ በተካተቱት ሥዕላት ላይ ጥቂት ሐሳቦችን በማንሳት ልንደርደር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ስውሩና ያልታወቀው ታሪክ”

The Hidden and Untold History of the Jewish People and Ethiopians by Fikre Tolossa

የመጽሐፍ ርዕስ፦ ስውሩና ያልተነገረው የአይሁዳውያን እና የኢትዮጵያውያን ታሪክ

ደራሲ፦ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ

አሳታሚ፦ ንባዳን ኃ.የተ.የግል ማኅበር (Nebadan plc)

የገጽ ብዛት፦ 234 (ከአባሪዎችና ምስሎች ጋር)

ዳሰሳ አቅራቢ፦ ሚኪያስ ጥ.

ሰውዬው በትምህርቱና በሥነ-ጽሁፉ ዓለም ከከረሙ፣ ዘመን አልፏቸዋል። ኢትዮጵያ እያሉ ካሳተሟት፣ “ወለላ” ከተሰኘች የአጫጭር ልቦለዶች መድበል አንስቶ እስከዛሬ እስከጻፏቸው ታሪክ-ቀመስና ልቦለዳዊ ሥራዎቻቸው ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን አትርፈዋል። በአሁኑ ሰዓት በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሊንኮልን (university of Lincoln) በመምህርነት እየሠሩ ይገኛሉ፤ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኅቡእ ጣት (ዘ ሀይድ)፣ አዲስ መጽሐፍ

ሸንቁጥ አየለ

ኅቡእ ጣት (ዘ ሀይድ)
ኅቡእ ጣት (ዘ ሀይድ)፣ የሸንቁጥ አየለ አዲስ መጽሐፍ

ኅቡእ ጣት (ዘ ሀይድ) የተሰኘውን አዲሱ መጽሐፌ፤ በኢትዮጵጵያውያን፣ ኤርትራውያን እና ግብጻውያን፤ ብሎም በተጓዳኝ ያሉ አገራትን ፖለቲካዊ ስነልቦናዊ ጭብጥ፣ የፖለቲካ ኢኮኖሚያዊ ስሌት፣ አገራዊ ራዕይ፤ እንዲሁም አጠቃላይ የፖለቲካ ቀመራዊ ውል ሊፈትሽ ይባትታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ድር ያደራበት ብዕርዎትን ከሰገባው ባያወጡት ይሻል ነበር!”

“... መሃል ፒያሳ ላይ መርከብ እንዲያንሳፍፍልዎ ነበር እንዴ የፈለጉት? ወይስ አይሮፕላን አኮብኩቦ እንዲያሳርፍልዎ?”

መዝገቡ ሊበን ከሜነሶታ

Yetekolefebet qulf

አልታዬ የተባሉ ጸሃፊ በቅርቡ “... ለረጅም ዓመታተ የጣሉትን ብዕር ድር ካደራበት ሰገባው ...” መዝዘው “የተቆለፈበት ቁልፍ” በቃላት ቁልፍ ተቆላልፏል!” በሚል ርዕስ አስነብበውናል። ዶ/ር በፍቃዱ በቀለ በ“የተቆለፈበት ቁልፍ” መጽሐፍ ላይ በጻፉት ግምገማ ላይ ተነስተው ትችታቸውን ያስነበቡን አልታዬ፣ ከስነ-ጽሁፋዊ ትችታቸው በፊት ያስቀደሙት፣ ዶ/ር በፍቃዱ፣ በ‘የተቆለፈበት ቁልፍ’ መፅሐፍ ላይ ያቀረቡት ጽሁፍ“...የወዳጅነት ፍቅር፣ አክብሮትና ስሜታቸውን ነው ... ወይስ በእውነት ምክንያታዊ ትችታቸውን?!...” በሚል፣ ምናልባትም “speculation” (ተጨባጭ ማስረጃ የሌለው “ቲዎሪ”) ነው። እንኳንስ አይደለም “ወዳጅ”፤ አባት እና ልጅ ቢሆኑስ አልታዬን ምን አገባዎት? ልጅ የአባቱን፣ አባት የልጁን ስነ-ጽሁፍ ስራ ቢተች ምን ችግር አለው? ትኩረትዎን ለምን ሃሳቡ እና ጽሁፉ ላይ አላደረጉም? ወዳጅነታቸውንስ መጥቀስ ለምን አስፈለገ? “speculation” ካልሆነ ደግሞ የዶ/ር በቀለን እና የደራሲውን ወዳጅነት አልታዬ ያውቃሉ? ምናልባትም ጽሁፉ ከእውነተኛ ስነ-ጽሁፋዊ ትችት ይልቅ “character assassination”/ሃሳብን ሳይሆን ግለሰብን ማጥቃት (ad hominem) አያስመስልብዎትም?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"የተቆለፈበት ቁልፍ" በቃላት ቁልፍ ተቆላልፏል

አልታዬ ገብረመድህን

Yetekolefebet qulf

ለረጀም ዓመታተ የጣልኩትን ብዕር ድር ካደራበት ሰገባው እንድመዝ አስገደደኝ - (Ethiomedia) ድረ-ገፅ ላይ ከወራት በፊት በዶክተር ፍቃዱ በቀለ በተባሉ ግለሰብ በ"የተቆለፈበት ቁልፍ" መጽሐፉ ላይ የቀረበ አንድ ፅሑፍ።

"ሃያሲው" በዘመናችን አቻ ያላገኙለት (ወደር የሌለው) መጽሐፉ መሆኑን ነው የገለፁልን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ