በ”ምርኮኛ” መጽሐፍ ላይ የግል አስተያየት

ነሲቡ ስብሐት (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

በአንድ ብዕር ሁለት መጽሐፍ። የዚያን ትውልድ ተጋድሎና የዘመኑን መቅሰፍት። በአንድ በኩል በወጣትነት ዘመኑ ያ ትውልድ ለሀገሩ አንድነት፣ ለሰው ልጆች መብትና ለዴሞክራሲ ያደረገውን ተጋድሎና የከፈለውን መስዋዕትነት፤ በሌላ በኩል የዛሬው ወጣቶች ደግሞ በኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ የተጠቁትን ወገኖች በግብረ ሰናይ ድርጅቶች አማካይነት የሚያደርጉትን እንክብካቤና ሕይወት አርዝም ጥረት።

 

ቆንጂት ብርሃን ”ለልጆች የሚደርስ አደራ” አስነብባናለች። አደራዋን ሳትበላ የገባቸውን ቃል ተወጥታለች። ቃል ኪዳኗን አክብራለች። የፍርዬን አደራ ለህዝብ አበርክታለች። ሕይወት ዘርታበታለች። እነዚያ ብርቅዬዎች ከመቃብር በላይ ከፍ ብለው እንዲታዩ አድርጋለች። ዛሬም ታሪካቸው ተናፋቂና ሕያው እንደሆነ አስነብባ በበኩሌ አስለቅሳኛለች። ”ምነው የረሳነውን ታስታውሽናለሽ? ለምን ቁስላችንን ትቀሰቅሻለሽ? ምናለ ብትተይን?! ...” ያሏትን ሁሉ ሳትሰለችና ተስፋ ሳትቆርጥ ትዕግስትን ተላብሳ ተወጥታዋለች። በአንጻሩም ”ምን እንርዳሽ? በርቺ! ይህን አስተካክይ ...” እያሉ ለብዕሯ ቀለም የሆኑትን እያመሰገነች ባካፈለችን ውርስ ያትውልድ ይመርቅሽ፣ ይህ ትውልድ ያክብርሽ እላለሁ! ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!