አረጋዊ በርሀ (ዘሔግ)

በቅርቡ “መለስ ዜናዊ እና የህወሓት የትግል ጉዞ” በሚል ርዕስ፣ ፀሐፊ ኢያሱ መንገሻ (ኮ/ል) ተብሎ፣ ባለ 313 ገፆች አንድ መጽሐፍ መጋቢት 2002 ዓ.ም. አዲስ አበባ ታትሞ ወጥቶ፤ ከጫፍ እስከ ጫፍ አነበብኩላቸው። መጽሐፉ አቶ መለስን ልዩ የታሪክ ካባ ለማልበስ ሲባል ብዙ የተደከመበት የፈጠራ ቅንብር መሆኑ ገና ከሽፋኑና ከመቅድሙ ያስታውቃል። ለዚሁም በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ከባህል ሚኒስትሩ ጋር በመሆን በሸራተን ሆቴል ደግሰው ነሐሴ 22 ቀን 2002 ዓ.ም. መርቀውለታል። ፀሐፊው ኮ/ል ኢያሱ መንገሻ ይባል እንጂ፤ በዚህ የፈጠራ ቅንብር የአቶ መለስ እጅ በእጅጉ እንዳለበት ብዙ ጠቋሚ ነጥቦች በዚህ መጽሐፍ ይገኛሉ።

 

ለመለስ ቅርበት አለኝ የሚለው ኮ/ል ኢያሱ፣ ቅርበቱ እዚህ ላይ እንዴት እንደተጠቀመበት ባይገልጽም ቅንብሩ ራሱ ይመሰክርለታል። ከዚህ አልፎም አንዳንድ የቅርብ ታዛቢዎች ‘መለስ ራሱ የፃፈው ድርሰት ነው’ ሲሉ ይደመጣሉ። ትዝብቱ ልክ ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም የአቶ መለስ የሙጉት ዘይቤ በመጽሐፉ በስፋት ከመታየቱ ባሻገር ሰውየው ድምፁን እየቀለባበሰ “ፓል-ቶክ” ውስጥም ጭምር ገብቶ አራዳዊ ክርክሩን በመርጨት የሚታወቅ ነውና።

 

እንግዲህ ቀጥሎ በዚህ መጽሐፍ ላይ ያለኝን አጠቃላይ ትዝብት ሳቀርብ፣ ትችቱ አቶ መለስን እና ”ፀሐፊው” ኮ/ል ኢያሱን የሚመለከት ሆኖ፤ ድርሰቱ ዋና ዓላማ አድርጎ በያዘው ‘የመለስ ጉዞ በህወሓት’ እና እኔም በቀጥታ በማውቃቸው አቶ መለስን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ብቻ ያተኩራል። በዚህ መልክ የመጽሐፉ አጠቃላይ ገፅታ ለመገንዘብ የሚከብድ አይሆንም። (ሙሉውን ጽሑፍ አስነብበኝ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ