ካሣሁን ዓለሙ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

፩. ምክንያተ ጽሕፈት

ይስማዕከ ወርቁ በቅርብ ጊዜ ባሳተመው ‹ተከርቸም› በሚለው 6ኛ መጽሐፉ ‹እልፍ (፼) ዐሥር ሺህን ሳይኾን አንድ ሺህን ይወክላል› የሚል መከራከሪያ አቅርቧል። እኔም በመጽሐፉ ያቀረበውን የእልፍ(፼) ቁጥር አስተያየት ከተመለከትኩ በኋላ መስተካከል ያለበት ጉዳይ መስሎ ስለተሰማኝ ይህንን ጽሑፍ በተወሰነ ደረጃ ሞነጫጭሬ አስቀምጨው ነበር፤ በዕንቁ መጽሔት ተጠይቆ የሰጠውን መልስ ከተመለከትኩ በኋላ ግን መከራከሪያ ነጥቦችን ማቅረብ አስፈላጊ መስሎ ታየኝ።

 

 

ምክንያቱም በእኔ ዕይታ የይሰማዕከ የ‹እልፍ አንድ ሺህ ነው› ውሳኔያዊ መጣጥፍና አጠቃቀም ሁለት አንድምታዎች አሰምቶኛል። አንድኛ ከዚህ በፊት የታተሙት የሊቃውንት መጻሕፍት የግዕዝ ቁጥር አጠቃቀም ስህተት መኾን ይጠቁማል። ይህ አንድምታም ‹የሀገራችን ሊቃውንት የግዕዝ ቁጥር ዕውቀት የላቸውም› የሚል ትርጓሜንም ያመጣል። ይህንን ደግሞ ‹እነዚህ ሕዝቦች እስከ ሺህ ድረስ አልቆጠሩም እንደ?› ያስብለናል እና ‹ቀና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ› የሚሉት የይስማዕከ አገላለጾቹ ምስክር ናቸው። ስጋቱ ቢገባኝም ‹ከኛ በላይ ያወቀ ቡዳ ነው› ዓይነት አቀራረቡ ግን አስተዋይነት ያለው አልመሰለኝም። ስለዚህ ጥረቱ መልካም ቢኾንም ያላስተዋላቸው ነጥቦች ስላሉ እንዲያጤናቸው እና ሌሎችም ትክክል መስሏቸው የቁጥር አጠቃቀማችን እንዳያዛቡ በሚል አመለካከት ይህንን አስተያየት አቀረብኩ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!