Ehadegen Eksesalehu  by Alemayehu Gelagayeደራሲ፤ ዓለማየሁ ገላጋይ
ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ

መንደርደሪያ
ሰቀቀን ጭንቀታቸውን እንደ ተጋቦ የሚያጋቡ፤ ግፍና በደሉን ጠኔና ጣዕሩን እንደ ሾተል አሹለው፤ ከልብ የሚቸክሉ ከአእምሮ ጓዳ የሚቀብሩ፤ አዝነው የሚያሳዝኑ፤ ተቃጥለው የሚያሳርሩ...ፍትህ ተሟጋች፤ ነፃነት ተፋራጅ፤ ጧፍ ነዳጅ...ደራሲያን፤ ቀመረ ቃላት ጠቢባን...ቢኖሩም...የብዕር ትሩፋታቸው ጨለማን ተጋፍቶ ጨለማን ተዋግቶ የወጣው - 'ኢምንቱ' ነው። እነርሱም ቢሆኑ ታዲያ፤ በጨለማ እንደሚተኮስ ርችት ወጋጋናቸው አድማስ ካድመስ የሚያሳይ ብርሃን ሆኗልና፤ እሰየው!!

 

ከዳፍንት ጨለማው እየቀለጡ ከበሩ፤ እየበሩ ከቀለጡ...ደራሲያኑ አንዱ፤ ኢህአዴግን ከሳሹ ኢህአዴግን ተሟጋቹ ዓለማየሁ ገላጋይ ነው፤ የሠላማዊ ትግሉ ብዕረተኛ አርበኛ። (የሠላማዊ ትግል ብዕረተኛ፤ ከተነሳ አርበኛ፤ ይጠቅሷል አብነት - እስክንድር ነጋን፤ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን፤ ርዕዮት አለሙን፤ ተመስገን ደሳለኝን እና...በርካቶችን) ... (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ ይህንን ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ