ደራሲ - ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም ቅኝት - መስፍን ማሞ ተሰማ
መንደርደሪያ
ሥነ ፅሁፍ የሀገር ታሪክ ባህልና የህብረተሰብ ህይወት ... በቃላት ደርዝ ተደርዘው ላለውና ለሚመጣው ትውልድ የሥነ ፅሁፍ ጠቢባን የሚያበረክቱት ቅርስ ነው። ጥበብ ነው ሥነ ፅሁፍ፤ የሀቅ መልህቅ። ጥበብን ያላሸተ፤ እውነትንና ፍትህን ያላማጠ፤ ያልወለደ ሥነ ፅሁፍ - ምን ቢኳኳል ቃል በቃል፤ ምን ቢቀማጠል፤ ቢያማልል - እንኳንና ዘመን ከዘመን ተሻግሮ፤ ትውልድን በትውልድ አጥፎ 'ዘለዓለማዊ ህልው' ሊያገኝ ቀርቶ - እንደ ጠዋት ጤዛ አረጋገፉ፤ ፋታም አይሰጥ አሟሟቱ። እንዲህ ያሉ - በየዘመኑ የመከኑ ብዕራት፤ በየዘመኑ ነበሩ፤ ዛሬም አሉ፤ ነገም ይኖራሉ።

 

ታዲያ ለመንደርደሪያ፤ የመካነ ብዕራትን ህይወተ ጎዳና፤ ብናነሳሳም ቅሉ፤ የቅኝታችን ሰበቅ ግና - ወዲህ ነው ውሉ። በኢትዮጵያ የሥነ ፅሁፍ ታሪክ ግዙፍ አሻራ ካኖሩት አንጋፋ ፀሀፍት አንዱ፤ ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም ይገኛሉ። ሥራዎቻቸው ሕያው ናቸው። ያልመከኑ፤ የማይመክኑ። ደራሲ ናቸው። ተርጓሚ ናቸው። ሀያሲ ናቸው። እንዲህ ይላሉ፤ ... (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!