የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሐፍና የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ተክለብርሃን ገብረሚካኤል

"የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ" ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ”የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ” በሚል ርዕስ በሐምሌ ወር 2008 ዓ.ም. አሳትመው ያወጡት መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ምርምርና ጥናት አዲስ ፈር ቀዳጅ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ውጪ (ከማዳጋስካር፣ ከኢስያ ክፍሎች) ወደ ኢትዮጵያ ፈልሶ የገባ ሲባል የኖረውን አፈ ታሪክ አሳማኝ ናቸው በሚባሉ ማስረጃዎች አስደግፈው ከእውነቱ የራቀ መሆኑን አሳይተዋል። ሁለተኛ አማራ የገዥ መደብ ተብሎ በአማራ ሥርወ መንግሥት ኦሮሞን ጨምሮ ሌሎች የባህል ገጽታዎቹን በኃይል ጭኖባቸዋል የሚለው ውግዘት ምንም ታሪካዊ መሠረት እንደሌለውና እንዲያውም፣ በአግአዚ/ሰሎሞናዊና በዛጉዌ ሥርወ መንግሥታት በንጉሠ ነገሥትና ደረጃ አማሮች የበላይነት ይዘው እንደማያውቁና ይልቁንም በዚህ የሥልጣን ደረጃ አብዛኞቹ ኦሮሞዎች እንደነበሩ አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በዘመነ መሳፍንት በባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴነቱ በኢትዮጵያ ሥልጣን ይቀራመቱ የነበሩት አማሮች ሳይሆኑ፣ በተለይ የየጁ ኦሮሞዎች መሆናቸውን ቁልጭ አድርገው ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ አመልክተዋል። ሦስተኛ አማሮች የዘር ምድባቸው ሴማዊ (ሴሜቲክ) ሳይሆን እንደ ኦሮሞ ኩሻዊ መሆኑን፣ ሁለቱም ጎሳዎች (ጎሳ በቋንቋ መወሰኑን አመልክተዋል) የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጥንታዊ አባት ከሆነው ኩሻዊው ኢትዮጵያ ልጅ ከደሽት (ከደሴት) የመጡ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ጂኦግራፊያዊ ወይም መልክዓ ምድራዊ ምንጫቸው ዛሬ ጐጃም እየተባለ የሚጠራው አካባቢ መሆኑን አመልክተዋል። እነዚህ ሁሉ አዳዲስ ታሪካዊ ግኝቶች ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አነጋጋሪው የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሐፍ ምጥን ዳሰሳ (ክፍል አንድ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

መንግሥቱ አበበ

- የኦሮሞና የአማራ ህዝብ በደምና ስጋ ብቻ ሳይሆን በባህል፣ በኅሊናና በመንፈስ ዳቅሏል፤ ተዋህዷል
· አንዳንዶች፤ “አፄ ምኒልክ ጡት ቆረጡ፤ 5 ሚሊዮን ኦሮሞ ገደሉ” እያሉ የሚነዙት የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ነው
· አማራውን እወክላለሁ ብሎ ያወጀ ንጉሠ ነገሥትስ ይኖር ይሆን?

"የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ" ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ

ነዋሪነታቸው በአሜሪካ የሆነው ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ፤ በቅርቡ የኦሮሞ የአማራና የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛና ትክክለኛ የዘር ምንጭ ምን እንደሆነ ከ5ሺ ዓመታት በላይ ወደኋላ ተጉዘው፣ ማስረጃ አስደግፈው፣ ምንጭ ጠቅሰው፣ እስካሁን ድረስ የምናውቀውን የኢትዮጵያን ታሪክ የሚሽር፣ አዲስ የኢትዮጵያ ታሪክ በዝርዝርና በጠራ አቀራረብ የሚገልጽ ድንቅ መጽሐፍ አቅርበዋል። እስካሁን የነበረውን ታሪክ ከስር መሰረቱ ገለባብጦ፣ በአዲስ ታሪክ የሚተካ መጽሐፍ አግኝቼና አንብቤ አላውቅም፤ስለዚህም በጉጉት ነው ያነበብኩት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዶ/ር መረራ የቡዳ ፖለቲካ እና መቀበል ያቃተው መራራ እውነት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ግርማ ሠይፉ ማሩ

“የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” ዶ/ር መረራ ጉዲና Dr. Merera Gudinas new bookዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” በሚል አዲስ መጽሐፍ አስነብቦናል። በአንድ ጋዜጣ ላይ የዶክተር መረራ ከዩኒቨርሲቲ መሰናበት ያመጣው አንድ በጎ ጎን መሆኑን አንብቤያሁ። እኔም በዚህ እስማማለሁ። ብዙ የሀገራችን ፖለቲካኞች ጋዜጠኛ መቅረፀ ድምፅ ይዞ በሚጠይቃቸው ጥያቄ መልስ ከመስጠት የዘለለ ብዕርና ወረቀት አገናኝተው የሚያምኑበትን የፖለቲካ መስመር እና በግላቸው ያላቸውን ምልከታ ማካፈል ይቸግራቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኤርምያስ ለገሠና በዲ/ን ዳንኤል ክብረት በኩል እኛን ማዋራት አሰኘኝ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Daniel Kibret and Ermias Legesseይሄይስ አእምሮ (ከአዲስ አበባ)

ይህ ኢትዮጵያዊነት በስንት ረገድ ቁጭት ውስጥ እየከተተን እንደሆነ እናንተም አስቡት። በእጅጉ የሚገርም ሁኔታ ውስጥ እየከተተን ነው ያለ። በዚህች ሌሊት ሰባት ሰዓት ገደማ ያነበብኩት ጽሑፍ እንኳን ክፉኛ ዕንቅልፍ ነስቶኝ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ላይ ከሚጥመው መኝታየ ተነስቼ ይሄውና መዶግዶግ ያዝኩ - ለነገሩ ሳለ ወያኔ ምን የሚጥም መኝታ አለና!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የተቆለፈበት ቁልፍ” (መጽሐፍ ግምገማ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Yetekolefebet qulfኩችዬ

ርዕስ፤ የተቆለፈበት ቁልፍ (439 ገጽ)
ደራሲ፤ ምሕረት ደበበ ገ/ጻዲቅ (ዶ/ር)
ሮሆቦት አታሚዎች፤ አዲስ አበባ፤ መጋቢት 2005

አገር ቤቱ ዳያስፖራ፤ ዳያስፖራው ደግሞ አገር ቤት እየሆነ በመጣበት በዚህ ህልሙም፤ ቅዠቱም፤ ባህሉም፤ ኑሮውም ተወራራሽ በሆነበት ዘመን የሥነ ጥበብ ሰዎች አስጎምዥ የትረካ አውድማ እንደተቸሩ ካወቅኹ ሰንብቻለሁ።

የምሕረት ደበበ ልቦለድ ታሪክ ስድሰት ሺህ ማይል አራርቋቸው በሚኖሩ ያበሻ ሕበረተሰቦች ሁለንተናዊ ባሕርይና ዕጣ-ፈንታ ላይ የተመሠረተ ነው። የደራሲው አንድ እግር አሜሪካ፤ ሌላኛው እግር ደግሞ ኢትዮጵያ መሆን የሁለቱንም ሕብረተሰቦች ውጫዊና ሥነ-ዓዕምሮዋዊ ባሕርይ፤ እንዲሁም የየቤቱን ውሎና ከራሞ በቅርብ ለማስተዋል ዕድል እንደሰጠው ከትርካዎቹ ማስተዋል ይቻላል። ሁለቱም ሕብረተቦች ውስጥ እየተከሰተ ያለው ፈጣንና አንዳንዴም አስፈሪ የሆነ ማኅበራዊ ለውጥ የብዙ ደራሲያንን እንዲሁም በየሙያ ዘርፉ ያሉ ጠቢባንን የሰላ አዕምሮና ብዕር የሚጋብዝ ነውና እንደ ምሕረት ደበበ ያሉ ብዕር ሲያነሱ ደስ ይላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!