ኤርሚያስ ለገሰ፦ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

በቅድሚያ መጽሓፉን ጊዜ ሰጥተህ በማንበብ አስደማሚ ምልከታ በመስጠትህ ከልብ አመሰግናለሁ ። የተጻፈበትም አንዱ አላማ ይህ ስለሆነ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በእይታህ ላይ እነዚህ ጉድለት ይታይባቸዋል ብለህ ያነሳኸው እና የወደፊት ግምቶችህ ላይ የተወሰነ አስተያየት ለመስጠት የሚጋብዙ ስለሆነ ትንሽ ማለት ፈለኩ። በዚህ አጋጣሚ ሌሎች በመጵሀፉ ይዘት ላይ ዝርዝር ግምገማ ላደረጉ ሰዎች ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ለእያንዳንዱ አስተያየት መስጠት ከጊዜ አኳያ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ የማልዘልቅበትን መንገድ ልጀምረው አልፈለኩም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኮብላዩ ሚኒስትር ወጎች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ተመስገን ደሳለኝ

በዚህ ተጠየቅ ጨርፈን የምንመለከተው በኮሙኑዮኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረውና ዛሬ በስደት የሚገኘው የአቶ ኤርሚያስ ለገሰን “የመለስ ትሩፋቶች፣ ባለቤት አልባ ከተማ” የተሰኘው መጽሐፍን ነው። የመድብሉ ጻሐፊ ኤርሚያስን በግል አላውቀውም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት አቶ በረከት ስምዖን እርሱን እና ሽመልስ ከማልን ምክትሎቹ አድርጐ በሚኒስቴር ዲኤታ ማዕረግ መሾሙን በግዮን ሆቴል ለጋዜጠኞች ይፋ ባደረገበት ዝግጅት ላይ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከመፃፍ በፊት ራስን መገምገም

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

"እኛና አብዮቱ" በሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስስሜነህ ታምራት (ስዊድን)
የቀድሞው ባለሥልጣን ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ "እኛና አብዮቱ" በሚል ርዕስ አንድ መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል። ይህንኑ መጽሐፍ መነሻ አድርገው፤ ወይም የቆየ የፖለቲካ መስመር ልዩነት አነሳስቷቸው ይሁን ብቻ አቶ ሰለሞን ገ/የስ በኢትዮ-ሚዲያ ድረ-ገጽ ላይ "የመጽሐፍ ግምገማ" በሚል ርዕስ የጻፉትን አንብቤ እንደጨረስኩ ሁለት ሀሳቦች መጡብኝ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፍኖተ ሕይወት - የመጽሐፍ ቅኝት

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ደራሲ - ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም ቅኝት - መስፍን ማሞ ተሰማ
መንደርደሪያ
ሥነ ፅሁፍ የሀገር ታሪክ ባህልና የህብረተሰብ ህይወት ... በቃላት ደርዝ ተደርዘው ላለውና ለሚመጣው ትውልድ የሥነ ፅሁፍ ጠቢባን የሚያበረክቱት ቅርስ ነው። ጥበብ ነው ሥነ ፅሁፍ፤ የሀቅ መልህቅ። ጥበብን ያላሸተ፤ እውነትንና ፍትህን ያላማጠ፤ ያልወለደ ሥነ ፅሁፍ - ምን ቢኳኳል ቃል በቃል፤ ምን ቢቀማጠል፤ ቢያማልል - እንኳንና ዘመን ከዘመን ተሻግሮ፤ ትውልድን በትውልድ አጥፎ 'ዘለዓለማዊ ህልው' ሊያገኝ ቀርቶ - እንደ ጠዋት ጤዛ አረጋገፉ፤ ፋታም አይሰጥ አሟሟቱ። እንዲህ ያሉ - በየዘመኑ የመከኑ ብዕራት፤ በየዘመኑ ነበሩ፤ ዛሬም አሉ፤ ነገም ይኖራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሥልጣኔ ሞት - ከድርሰት ሞት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ሐዲስ ዓለማየሁ Haddis Alemayehuዳንኤል ክብረት
የዛሬ 600 ዓመት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተባለ ኢትዮጵያዊ ደራሲ "አርጋኖን" የተሰኘ መጽሐፍ ይደርሳል። ይህንን መጽሐፍ የተመለከቱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትም እጅግ ያደንቁና ለንጉሡ ለዐፄ ዳዊት ያቀርባሉ። ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም መጽሐፉን ተመልክተው በማድነቅ በወርቅ ቀለም እንዲጻፍ አዘዙ። አባ ጊዮርጊስንም ሸለሙ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!