The Secret ምስጢሩወለላዬ ከስዊድን
"The Secret" በሚል ርዕስ አውስትራሊያዊቷ ሮዳ ቢየርን ጽፋው፣ ጋሻው አባተ "ምስጢሩ" በማለት ወደ አማርኛ የመለሰውን መጽሐፍ በአድናቆት አነበብኩ። ምስጢሩ ... "ወዳንተ የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር ወደ ሕይወትህ የምትጎትተው አንተው ነህ" ይለናል። አዎን! በእርግጥ ብዙዎች ምስክርነት ሰጥተውበታል። ይህም በመጽሐፉ ላይ ተካቶ ይገኛል። መጽሐፉ በአስራ አንድ ርዕሶች የተከፋፈለ ነው። ከዛ ውስጥ የመጀመሪያውን ዕርስ ማጠቃለያ ፍሬ ሀሳብ፤ በግጥም ስሠራው እንዲህ እንሶና ጭምቅ ብሎ ወጣልኝ። ለወገኖቼ ባካፍልስ ብዬ አሰብኩ፤ ወደናንተም ላኩት። ሁለተኛው ርዕስና ሌሎቹም ይቀጥላሉ።

 

የተከሰተው ሚስጢር
ሕይወት ለመለወጥ፤ የተገኘው ሚስጢር፤
ስበት እንደሆነ፤ አውቀህ ሕጉን ተማር።
የፈለከው ነገር፤ ወደ ዓለም ተልኮ
የልብህን ምኞት፤ ያመጣዋል ማርኮ።
ከ'ንግዲህ ሕይወትህን፤ ካሻህ ለመለወጥ
መስመሩን አስተካክል፤ ፍሪኮንሲ ምረጥ።
አንተው ነህ ለራስህ፤ ኃይል ማሰራጫ
ጎትተህ አቅራቢ፤ የሕይወትህን ምርጫ።
ስለዚህ ከዓለም፤ ሁሉን እንድታገኝ
በስበት ተማምነህ፤ ደህና ነገር ተመኝ።
አሁን ለምነግርህ፤ ለዚህ ለምስጢሩ
የመረጃው ብዛት፤ በርካታ ነው ቁጥሩ።


መልዕክትና አስተያየት ካለዎት
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!