የኢትዮጵያውያን ሽግግር - በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር

Ethiopian Transitions: At Home and Abroad (by Kebede Haile) / የኢትዮጵያውያን ሽግግር - በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር (ከበደ ኃይሌ)አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ

የመጽሐፉ ርዕስ፡- Ethiopian Transitions: At Home and Abroad (የኢትዮጵያውያን ሽግግር - በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር)

ፀሐፊ፡- ከበደ ኃይሌ

ቋንቋ፡- እንግሊዝኛ እና አማርኛ

ዋጋ፡- 32.99 የአሜሪካ ዶላር (ጠንካራ ሽፋን)

የገጽ ብዛት፡- 286

አሳታሚ፡- ኦልራይት ፐብሊሺንግ

ገበያ ላይ የዋለው፡- መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም. / ኦገስት 24 ቀን 2015 (እ.ኤ.አ.)

ደራሲና ፀሐፊ ከበደ ኃይሌ በቅርቡ እንግሊዝኛ እና በአማርኛ ቋንቋ የጻፉት “Ethiopian Transitions: At Home and Abroad” (የኢትዮጵያውያን ሽግግር - በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር) የተሰኘው መጽሐፍ በቅርቡ በገበያ ላይ መዋሉን ለኢትዮጵያ ዛሬ በላኩት ኢ-ሜይል ገለጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኤርምያስ ለገሠና በዲ/ን ዳንኤል ክብረት በኩል እኛን ማዋራት አሰኘኝ

Daniel Kibret and Ermias Legesseይሄይስ አእምሮ (ከአዲስ አበባ)

ይህ ኢትዮጵያዊነት በስንት ረገድ ቁጭት ውስጥ እየከተተን እንደሆነ እናንተም አስቡት። በእጅጉ የሚገርም ሁኔታ ውስጥ እየከተተን ነው ያለ። በዚህች ሌሊት ሰባት ሰዓት ገደማ ያነበብኩት ጽሑፍ እንኳን ክፉኛ ዕንቅልፍ ነስቶኝ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ላይ ከሚጥመው መኝታየ ተነስቼ ይሄውና መዶግዶግ ያዝኩ - ለነገሩ ሳለ ወያኔ ምን የሚጥም መኝታ አለና!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የተቆለፈበት ቁልፍ” (መጽሐፍ ግምገማ)

Yetekolefebet qulfኩችዬ

ርዕስ፤ የተቆለፈበት ቁልፍ (439 ገጽ)
ደራሲ፤ ምሕረት ደበበ ገ/ጻዲቅ (ዶ/ር)
ሮሆቦት አታሚዎች፤ አዲስ አበባ፤ መጋቢት 2005

አገር ቤቱ ዳያስፖራ፤ ዳያስፖራው ደግሞ አገር ቤት እየሆነ በመጣበት በዚህ ህልሙም፤ ቅዠቱም፤ ባህሉም፤ ኑሮውም ተወራራሽ በሆነበት ዘመን የሥነ ጥበብ ሰዎች አስጎምዥ የትረካ አውድማ እንደተቸሩ ካወቅኹ ሰንብቻለሁ።

የምሕረት ደበበ ልቦለድ ታሪክ ስድሰት ሺህ ማይል አራርቋቸው በሚኖሩ ያበሻ ሕበረተሰቦች ሁለንተናዊ ባሕርይና ዕጣ-ፈንታ ላይ የተመሠረተ ነው። የደራሲው አንድ እግር አሜሪካ፤ ሌላኛው እግር ደግሞ ኢትዮጵያ መሆን የሁለቱንም ሕብረተሰቦች ውጫዊና ሥነ-ዓዕምሮዋዊ ባሕርይ፤ እንዲሁም የየቤቱን ውሎና ከራሞ በቅርብ ለማስተዋል ዕድል እንደሰጠው ከትርካዎቹ ማስተዋል ይቻላል። ሁለቱም ሕብረተቦች ውስጥ እየተከሰተ ያለው ፈጣንና አንዳንዴም አስፈሪ የሆነ ማኅበራዊ ለውጥ የብዙ ደራሲያንን እንዲሁም በየሙያ ዘርፉ ያሉ ጠቢባንን የሰላ አዕምሮና ብዕር የሚጋብዝ ነውና እንደ ምሕረት ደበበ ያሉ ብዕር ሲያነሱ ደስ ይላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኤርሚያስ ለገሰ፦ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

በቅድሚያ መጽሓፉን ጊዜ ሰጥተህ በማንበብ አስደማሚ ምልከታ በመስጠትህ ከልብ አመሰግናለሁ ። የተጻፈበትም አንዱ አላማ ይህ ስለሆነ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በእይታህ ላይ እነዚህ ጉድለት ይታይባቸዋል ብለህ ያነሳኸው እና የወደፊት ግምቶችህ ላይ የተወሰነ አስተያየት ለመስጠት የሚጋብዙ ስለሆነ ትንሽ ማለት ፈለኩ። በዚህ አጋጣሚ ሌሎች በመጵሀፉ ይዘት ላይ ዝርዝር ግምገማ ላደረጉ ሰዎች ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ለእያንዳንዱ አስተያየት መስጠት ከጊዜ አኳያ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ የማልዘልቅበትን መንገድ ልጀምረው አልፈለኩም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኮብላዩ ሚኒስትር ወጎች

ተመስገን ደሳለኝ

በዚህ ተጠየቅ ጨርፈን የምንመለከተው በኮሙኑዮኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረውና ዛሬ በስደት የሚገኘው የአቶ ኤርሚያስ ለገሰን “የመለስ ትሩፋቶች፣ ባለቤት አልባ ከተማ” የተሰኘው መጽሐፍን ነው። የመድብሉ ጻሐፊ ኤርሚያስን በግል አላውቀውም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት አቶ በረከት ስምዖን እርሱን እና ሽመልስ ከማልን ምክትሎቹ አድርጐ በሚኒስቴር ዲኤታ ማዕረግ መሾሙን በግዮን ሆቴል ለጋዜጠኞች ይፋ ባደረገበት ዝግጅት ላይ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ሽፈራው - ሞሪንጋ”ን የሚመለከት አዲስ መጽሐፍ ወጣ

“ሽፈራው - ሞሪንጋ” በአበራ ለማ "Shiferaw - Moringa" by Aberan Lemmaጋዜጠኛ፣ ገጣሚና ደራሲ አበራ ለማ “ሽፈራው - ሞሪንጋ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ አሣተመ። ሞሪንጋ ወይም ባገራችን “ሽፈራው” እያልን በስፋት የምንጠራው ዕጽ፣ እጅግ እውቅናን አግኝቶ የኖረው በእስያ ውስጥ ነው። ሕንዶች ኦሊፌራ የተሰኘው ዝርያ ባለጸጎች በመሆናችው በብዙ መልኩ ሲጠቀሙበት ኖረዋል። ዛሬ ኦሊፌራ የተሰኘው ዝርያ፣ በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ፣ በካሪቢያን ደሴቶች፣ በአፍሪካና በኦሴኒያ ውስጥ በብዛት እየለማና እየተስፋፋ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!