ቆንጅየው መሪ?

በዚህ ፎቶ አቶ መለስ ”ቆንጅየው መሪ” ለመባል ምን ያንሳቸዋል?

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ

አቶ መለስ ዜናዊ በሣጥን

PM Meles Zenawi in a cageየኢትዮጵያው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የ2002 ምርጫን 99.6 በመቶ “አሸነፍኩ” ካሉ በኋላ፤ ጥይት በማይበሣው የመስታወት ሣጥን ውስጥ ሆነው ለ”ደጋፊዎቻቸው” በመስቀል አደባባይ ንግግር ሲያደርጉ። ግንቦት 17 ቀን 2002 ዓ.ም. (ሜይ 26 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.) መስቀል አደባባይ የወጡት “ደጋፊዎቻቸው”፣ “ድምፃችን ይከበር!” ማለታቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል። በምርጫ 97 መላው የኢትዮጵያ ህዝብ “ድምፃችን ይከበር!” ቢልም እንዳልተከበረለት የአምስት ዓመት ትዝታችን ነው። … ቆይ! … ቆይ! … ለመሆኑ ጠ/ሚንስትሩ 50 ብር በነፍስወከፍ ከፍለው ያስወጧቸውን ደጋፊዎቻቸውን ፈርተው ይሆን ጥይት በማይበሣው ሣጥን ውስጥ የታጀሉት?

 

”ፍቅሬ እስከሕይወቴ” መርዓዊ ስጦታ

አርቲስት መርዓዊ ስጦታ ያንጋፋው ብሔራዊ ቲያትር ሙዚቀኛና ደራሲ የመጀመሪያ የሆነውን የልብ ቀዶ ሕክምና ካደረገ በኋላ በዶክተሮች የትንፋሽ መሣሪያ እንዳይጫወት ከተከለከለ ሰነባብቷል። ከክልከላው በኋላ ግን የሴት ልጁ ሠርግ ደረሰ። ሀገርና ወገንን በሙዚቃ ሲያዝናና እና ሲያስደስት የኖረው መርዓዊ በልጁ ሠርግ አምባሰልን በክላርኔት አለመጫወት የማይደረግ ሳይሆን የማይታሰብ መሆኑን አሰበው። አምባሰልን ገና ሲነካት ቅላጼ በምታወጣው ክላርኔቱ ሠርጉ ላይ ሲጀምረው ሙሽሮቹ በእንባ ሲቃ መጫወት ጀመሩ። ሙሽሪት ኢትዮጵያ ለአባቷ ሕይወት ስፍስፍ እያለች የሠርጉ ታዳሚዮችም አድናቆታቸውን በእንባና በጭብጨባ ገለጹ። ... እስቲ አባት ለልጁ ፍቅሩን እስከ ሕይወቴ ድረስ ያለበትን ሠርግ ቪዲዮ ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑት!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ