Ethiopian Dialogue Forum

የኢትዮጵያ የውይይትና መፍትሔ መድረክ

ለዜና ማሰራጫዎች ሁሉ:-

ኢትዮጵያ በለውጥ ጎዳና ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ ይህ የለውጥ ጊዜ ኢትዮጵያውያንን በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃ ሆኖ ይታያል። በዚህ የለውጥ እንቅስቃሴ ወቅት የለውጡ ኃይል ኢትዮጵያውያን ሁሉ ተደምረው ለውጡን እንዲደግፉ ጥሪ በተደረገላቸው መሰረት በከፍተኛ ሁኔታ ሲደግፉ ይታያል። የለውጡን ኃይል የመደመር ፖለቲካ ለመደገፍ የድጋፍ ሰልፎች በብዙ ቦታ እየተካሄደ ነው። ተደምረናል! ተደምረናል!! ... የሚለው ሐሳብ ገዢ ሆኗል። በርግጥ ታዲያ ይህ የመደመር መርኅ በበጎ ሐሳብነቱ ቅቡል ነው። ይህ ቅቡል ሐሳብ ከሐሳብነቱ አልፎ ወደ ተግባር የምንገባበት ዋዜማ ላይ ነን።

እስካሁን በለውጡ ኃይል የተገቡ የመደመርን መርኅ በተግባርና በሕግ ማእቀፍ የምናይበት ወቅት እየመጣ ነው። ታዲያ ይህ የመደመር መርኅ ከኢኮኖሚ አንጻር የሚኖረው የኢኮኖሚ ስትራክቸር ምን መምሰል አለበት? መደመር በኢትዮጵያውያን የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ውስጥ እንዴት መገለጽ አለበት? መደመርን መሰረት ያደረገ ሕገ-መንግሥት እንዴት ይኖረናል? በመጀመሪያ ሕገ መንግሥቱ የመደመርን መርኅ በምልዓት ይገልጻል ወይ? የተደመሩ ኢትዮጵያውያን ቃል ኪዳን ነው ወይ? ከባህልና ከቋንቋ አንጻር መደመር እንዴት ይገለጻል? ማንነት እንዴት ይደመራል? ታሪክ በመደመሩ ሂደት ምን ሚና አለው? የሚዲያዎች መደመር እንዴት ይገለጻል? እና የመሳሰሉ ጭብጦችን ይዘን በጥልቀት መወያየት ያለብን ሰዓት ላይ ነን።

የኢትዮጵያ የምክክር ኮርፖሬሽን EDF (Ethiopian Dialogue Forum)፤ በእነዚህ ጭብጦች ላይ ውይይት ለማድረግ የፊታችን መስከረም 8 ቀን 2018 በዋሽንግተን DC በኢትዮጵያ ኤምባሲ አዳራሽ ውስጥ የአንድ ቀን ሙሉ ኮንፈረንስ ያደርጋል። በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ከየሙያው ሊቆችን ጠርተናል። ለሽግግር የሚሆኑ፣ ለፖለሲ ግብዓት የሚሆኑ ሐሳቦችን ከዚህ ስብሰባ እንጠብቃለን። የአገራችንን የለውጥ ኃይል ገንቢ የለውጥና የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ሐሳቦችን ከዚህ ኮንፈረንስ እንጠብቃለን። በመሆኑም በዚህ የአንድ ቀን ኮንፈረንስ ላይ በመገኘት ውይይቱን ለኢትዮጵያውያን እንድታስተላልፉልን እንጠይቃለን። ለተጨማሪ መረጃ በመደወል ማብራሪያ ልታገኙ ትችላላችሁ።

ከአክብሮት ጋር!

የኢትዮጵያ የውይይትና መፍትሔ መድረክ ኮንፈረንስ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ

(ፊርማ አለው)

ፕሮፌሰር አቻምየለሀ ደበላ

“ተደምረን እንሻገራለን!” ዶክተር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ