ናይጄሪያዊቷ ጋዜጠኛ አዴኦላ ፋዩን በአፍሪካ ወቅታዊ ዜናዎች ላይ ተመስርታ በአሸሟሪነት ትታወቃለች። ነዋሪነትዋ በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ሲሆን፣ በሣምንት አንዴ በሳህራ ቲቪ ”Keep It Real With Adeola” በተሰኘው ዝግጅቷ ነው የምታሸሙረው። ከዚህ ቀደም የቀድሞዋን ቀዳማዊ እመቤት አዜብ መስፍንን አስመልክታ ባቀረበቻቸው ዝግጅቶች በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ትታወቃላች። በዚህ ቪዲዮ የአፍሪካ መንግሥታትን ሙሰኝነት አስመልክታ ታሽሟጥጣለች።

ለማስታወስ ያህል፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለቤታቸው አቶ መለስ ዜናዊ ካረፉና በምትካቸው አቶ ኃይለማርያም ጠ/ሚንስትር ኹነው ሲተኩዋቸው ቤተመንግሥቱን አለቅም ማለታቸውን ተከትሎ አሽሟጣቸው ነበር። ከዚህም ሌላ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ለልብስ፣ ለጫማ፣ ለቦርሳ፣ ለሽቶና ለሴት እቃዎች አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዩሮ ማውጣታቸውን አስታውሳ ለአዲስ አበባ ከንቲባነት ሊወዳደደሩ መሆኑን አስመልክታም በወቅቱ ሽሙጥዋን በሳህራ ቴሌቭዥን ማቅረቧ ይታወሳል። እነዚህን ሁለት ቪዲዮዎች ከዚህ በታች አቅርበናቸዋል። መልካም ዕይታ!

ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግሥቱን አልለቅም ብለው አሻፈረኝ ማለታቸውን አስከትሎ አዴኦላ ያሸሞረችው።

ከዚህ በታች ያለው ቪዲዮ ስለወ/ሮ አዜብ መስፍን ለአዲስ አበባ ከንቲባነት የመወዳደርን ጉዳይ እና የ1.2 ሚሊዮን ዩሮውን ወጪ አስመልክታ ያሽሟጠጠችበት ነው። ቪዲዮውን ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!