አዲስ አበባ በረራ ናት፤ በረራም አዲስ አበባ

አምባ የጥናት እና ምርምር ክፍል ያቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ

Map of Barara and its surrounding.
Map of Barara and its surrounding. The places shown on the map and others are identified by Marco. From Marco Vigano, “The Names Lost, the Map Grasped,”

በሀቅ ላይ የተመሰረተ ታሪክ ጽኑ የአንድነት መሰረት ነው። ፍትህንም ለማስፈን ወሳኝ ሚና አለው። ታሪክ የራሱ የሆነ የሙያ ስነምግባር አለው። የታሪክ ባለሙያ ለሙያው ፍቅርም ሲል ህይወቱን መስዋዕት ለማድረግ ዝግጁ መሆን አለበት። የሚያስከፋም ሆነ የሚያስደስት፣ የሚያስነቅፍም ሆነ የሚያስወድስ በመረጃ የተመሰረተ ሀቀኛ ታሪክን መቀበል የስልጡንነት ምልክት ነው። ታሪክን መፍራት፣ መካድ እና ማድበስበስ ኋላቀርነት ነው። ታማኝ መረጃ እስከተገኘ ድረስ ታሪክ ያለምንም ገደብ ይጻፋል። ያስከፋል ወይም ያስነቅፋል ብሎ በታሪክ ላይ ሀጢያት መስራት ጉዳቱ ከባድ ነው። የታሪክ ዕውቀት ያድጋል፣ ይሰፋል ይቀየራል። ይህ የሚሆነው ደግሞ አዳዲስ መረጃዎች በአይነትና በመጠን ሲገኙ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ የመጨረሻዎቹ ሰዓታት

አክሊሉ ሀብተወልድ

Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church Abuna Theophilos
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ የነበሩት አቡነ ቴዎፍሎስ

ሐምሌ 7 ቀን 1971 ዓ.ም. ዕለተ ቅዳሜ ከታላቁ ቤተ መንግሥት ምድር ቤት እስረኞች መካከል የክርስትና እምነት ተከታዮች የሆኑት በጠዋት ተነስተው በአባቶች መሪነት ጸሎት አድርሰዋል። የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ደውል ድምፅ ሲያስተጋባ ሰምተዋል። ፈጣሪያቸውን አውቀው በድፍረት ሳያውቁ በስህተት የፈፀሙትን በደል ይቅር እንዲላቸው ተማጽነዋል። ከጸሎት በኋላ እስረኞቹ ጧት ፀሐይ ለመሞቅና አየር ለመቀበል የተፈቀደላቸው ለ45 ደቂቃ ጊዜ አጠናቀው ወደየክፍሎቻው ተመልሰው ተቆልፎባቸዋል። የሐምሌ ፀሐይ በቀዝቃዛው በታላቁ ቤተ መንግሥት ምድር ቤት ውስጥ የታጎሩትን ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ለማጽናናት የተላከች ይመስላል፤ ሰማዩን በጋረደው ደመና መካከል ብልጭ ድርግም ትላለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የበላይ ዘለቀ ፎቶግራፍ

ዮፍታሔ

Belay Zeleke
በላይ ዘለቀ

የዘንድሮው የአርበኞች ቀን የስመ ጥሩው አርበኛ በላይ ዘለቀ ስም ጎልቶ እይታሰበ የተከበረበት መሆኑ ተጠቅሷል - ይልቁንም በአማራ ክልል።

ይህንን ተከትሎ ደግሞ ዶክተር ሽብሩ ተድላ “ከጉሬዛ ማርያም እስከ አዲስ አበባ የሕይወት ጉዞዬ እና ትዝታዬ” በሚል ርዕስ ያሳተሙትን መጽሐፍ በመጥቀስ ከዚህ በታች የሚታየው የበላይ ዘለቀ ፎቶ የርሱ እንዳልሆነ የሚገልጹ ጽሑፎች ወጥተው እያነበብን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጃንሆይ እናት

ዳዊት ከበደ ወየሳ - ከአትላንታ

Ras Darge Sahle Selassie
ራስ ዳርጌ ሣህለሥላሴ፣ የሸዋው ንጉሥ ሣህለሥላሴ ልጅ

ነገሩ ትንሽ ቆየ። እኔ ግን በሆነ አጋጣሚ በቅርቡ ነው ቃለ ምልልሱን የሰማሁት። ተስፋዬ ገብረአብ አዲስ ስላሳተመው - “የጀሚላ እናት” መጽሐፍ፤ ከጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ ጋር አጭር ቃለምልልስ አድርጎ ነበር። በትክክል እንዳዳመጥነው ከሆነ፤ “የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እናት ስም ጀሚላ ነው፤ አንድ ወገናቸው ስልጤ ጉራጌ ነው - በሌላ ወገን ኦሮሞ ናቸው።” ይለናል። (ቃለምልልሱን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ!)። በመቀጠልም፤ “የጀሚላ እናት በአቶ በዛብህ ተጠልፈው ነበር። አቶ በዛብህ ከምኒልክ ጋር በጦርነት ሞቱ። የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ወይም የጀሚላ እናት እልፍኝ ውስጥ፤ በአፄ ምኒልክ ተገደሉ።” የሚሉና ሌሎች ተዘርዝረው የማያልቁ የልብወለድ ነገሮች በመጽሃፉ ውስጥ ማካተቱን በቃለ ምልልሱ ላይ ሰማን። ወደ ኋላ በመመለስ ‘በወቅቱ ምላሽ የሰጠ ሰው ይኖር ይሆን?’ በማለት አንዳንድ ድረ ገጾችን ብመለከት፤ በዚህ የተዛባ ታሪክ ምክንያት … “ኢትዮጵያ ሆይ ታሪክ ነጋሪ አጣሽ?” የሚሉ የቁጭት አስተያየቶችን አነበብኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አድዋ ለኛ የሚሰጠን ትርጉም ምንድን ነው? እኛስ ከአድዋና ከሌሎች አገሮችስ ምን ተማርን?

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

The battle of Adwa.
የአድዋ ጦርነት የአፍሪካውያን ድል ነው!

 

መግቢያ

በአፄ ምኒልክና በተቀሩት ጀግና የጦር መሪዎቻቸው የሚመራው የኢትዮጵያ ወታደር በወራሪው ጣሊያን ላይ ድል ከተቀዳጀ ይኸው 121 ዓመት ሆነው። ከረጅም ዓመታት ጀምሮ የአድዋ በዓል በየአመቱ ይከበራል። በአሁኑ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህንን ታላቅ የድል በዓል ያከብራል። አገሩን ከሚወደውና አዲስ ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት ከሚፈልገው ጀምሮና፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከውጭ ኃይሎች ጋር በማበር ዛሬ አገራችን የምናየው ውድቀት ውስጥ እንድትወድቅ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለማበርከት ከበቃው ድረስ፣ ሁሉም በየፊናው ይህንን በዓል ያከብራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ