“ቤን አሊን ተመልከቱ፣ ሙባረክን ወይንም ጋዳፊን ስሟቸው ሁሉም ህዝባዊ ጥያቄ ሲበረታባቸው የሰጡት መልስ ተመሳሳይ ነው። ‘እኔ ስልጣኔን ብልቅ ሀገሪቱ ቀውስ ውስጥ ትገባለች የእርስ በርስ ጦርነትም ይከሰታል።’ ነበር ያሉት ይህ የተበላበት ክርክር ሲሆን የሚያሳዝነው ግን የምእራቡ አለም መሪዎች በተወሰነ ደረጃ ሊቀበሉት የመፈለግ አዝማሚያ የሚያሳዩ መሆናቸው ነው። “ይህ ወቅት በተግባር ያረጋገጠው ነገር ሌላው ቀርቶ የተቃዋሚ ፓርቲ ሳይኖር እንኳን ህዝብ ነጻነቱን ካገኘ ወደ እርስ በርስ ጦርነት የማያመራ መሆኑን ነው። ህዝቡ ነጻነት የሚመጣው ከሀላፊነት ጋር መሆኑን ጠንቅቆ ይገነዘባል።

“በታሂር አደባባይ የፈሰሰው ሰልፈኛ የመንገዱን ሰላም እያስከበረ፣ ሙዚየሙን ከሌቦች ተከላክሎ እየጠበቀ ነበር የሀላፊነት ብቃቱን ያረጋገጠው። የተደራጀ ሀይልን እያጠፉ ‘ሊተካኝ ዝግጁ የሆነ ኃይል ስለሌ ለእኔ ስልጣን ብለቅ ሀገሪቱ ትታመሳለች’ የሚለው የአምባገነኖች ጩኸት ትርጉመ ቢስ መሆኑ ነው በተግባር የታየው። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!