የኩቤክና የአውስትራሊያ ሊቀ ጳጳስ የሆኑትና የአውሮፓና የምስራቅ አፍሪካ ም/ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ መቃርዮስ በተለይ ለሃዋርያዊ ስራ አገልግሎት በቫንኩቨር ካናዳ በተገኙ ጊዜ ከተክለሚካኤል አበበ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።

ብጹእ አቡነ መቃርዮስ በተለያዩ አለማት በቤተ ክርስቲያን የሚነሱ አለመግባባቶችን በመፍታት የሚታወቁ ሲሆን በአውሮፓ የተለያዩ አገራት በመዘዋወር ሃዋርያዊ አገልግሎት ሲፈጽሙ መሰንበታቸው የሚታወቅ ሲሆን አሁንም አገልግሎታቸውን በማስፋት በቫንኩቨር ካናዳ የምትገኘውን ጼዴነያ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ቅዳሴ ቤቱን በማክበርና ሁለት ታቦታትንም በማስገባት ቡራኬ ያደረጉ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኗንም ምስካ ይዙና መድኃኒያለም እና ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን በማለት ስያሜ መስጠታቸው ተገልጿል።

ቤተ ክርስቲያኗ አሁን በአጸደ ስጋ የሌሉት ብጹእ አቡነ ዜና ማርቆስ ባርከው በላኳቸው መላከ ጸሀይ አፈወርቅ ለገሰ አስተዳዳሪነት ላለፉት አራት አመታት ብዙ ፈተናዎችን ስትቋቋም እንደነበርም የሰበካ ጉባኤው አስታውቋል።

(ቪድዮውን ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!