“ትግራዋይ መበለጥን አይፈልግም፣ ትግራዋይ ለአማራ፣ ለኦሮሞ፣ ለሶማሌ ሊጠረጥርና ሊያጎነብስ ነውር ነው” - ጌታቸው ረዳ

ጌታቸው ረዳ

“ከሁሉም ነገር በላይ ግን ትግራዋይ እየተሸነፍኩ ነው የሚል እሳቤ ለአማራ ሊጠረጥርና ሊያጎነብስ፣ ለኦሮሞ ሊጠረጥርና ሊያጎነበስ፣ እንደ ሕዝብ ለሶማሌ ሊጠረጥርና ሊያጎነብስ ነውር ነው! ይህ በትግራዋይ ታሪክ አልነበረም!!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለአቶ አባይ ፀሐዬ የተሰጠ ምላሽ፣ ከትዴት

Abay Tsehaye

ወርቅና ሐቅ እያደረ ይጠራል

ትዴት (የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር)

ሕወሓት በመላው ኢትዮጵያ እየተደረገበት ባለው ትግልና ጫና ተገዶ፣ እንደዚሁም በኢህአዴግ ራሱ ውስጥ ባሉት ፓርቲዎች መካከልም በተፈጠረው ፉክክርና ፍትጊያ የተነሣ ምስጢር አድርጎ ደብቆት የነበረውን ሐሰትና ማወናበድን አንድ ባንድ እያለ እያጋለጠው ይገኛል። ይህ ሁኔታ እዚህ ላይ የሚቆም አይደለም፣ ሕዝቡ መብቱን ለማስከበር ቆርጦ ተነስተዋልና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ካፀደቀ የሕወሓትን ገመድ በአንገቱ ላይ በገዛ እጁ እንዳሰረ ይቆጠራል

Amhara and Oromo

ከአኦትይፕ (ከአማራና ኦሮሞ ትብብር ይለምልም ፕሮጀክት)

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሕወሓት የወታደራዊ አገዛዝ አዋጅ ማለት። እንኳን የሰው ልጁ እንስሳትም ቢሆኑ አንገታቸው ላይ ገመድ ሊታሰር ሲል በፀጋ አይቀበሉም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በመላ ኢትዮጵያውያን ያልተደገፈና ከውጭ አገራትም ሆነ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ጠንካራ ተቃውሞ የተነሳበት መሆኑ በሚገባ ይታወቃል። የአዋጁ ዋና ዓላማ ሕወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ የተነሳበትን ተቃውሞ ለመጨፍለቅ፤ በኦሕዴድና ብአዴን እየተነሳ ያለውን የፍትህና የእኩልነት ጥያቄ ትግልን ለማጨናገፍ፤ ኦሕዴድና ብአዴን የሕወሓትን የበላይነት ለማስወገድ ከክልላቸው ሕዝብ ጋር ተቀራርበው ለመስራት የሚያደርጉትን ጥረት ለማደናቀፍ እና ለህወሃቶችና ለሸሪኮቻቸው አገሪቷን የመዝረፍ ዘመቻቸውን በስፋት የሚቀጥሉበትን መንገድ ለማረጋገጥ ነው። ይህ አዋጅ የአገር ወይም የሰፊው ሕዝብ ደህንነት አዋጅ ሳይሆን የጥቂቶችን የበላይነት ለማስጠበቅ የታለመ አዋጅ ነው። ምክንያቱም በቅርቡ እንኳን እንደተረጋገጠው የፌደራል የፀጥታና የመከላከያ ኃይል በማይኖርበት ጊዜ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ድጋፉንም ይሁን ተቃውሞውን አሳይቶ በሰላም ወደ ቤቱ እንደሚመለስ በበርካታ የአገሪቷ ክፍሎች በግልፅ የሚታወቅ ነው። በአብዛኛው ረብሻና ግጭት የሚቀሰቅሰው የአጋዚና የፌደራል የፀጥታ ኃይሎች በሚያዳርጉት ግድያና ትንኮሳ ምክንያት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መፍትሔው! በሕዝባዊ ማዕበል የቀውሱን ፈጣሪ ማስወገድ!!

ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ት.ዴ.ት./TAND)

ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ት.ዴ.ት./TAND)

ታሕሣሥ 2017

ቀውሱ ከባድ ነው፣ አገርን ሊያፈራርስ፣ ሕዝቦችን እርስበርስ ሊያዳም የሚችል አደገኛ ቀውስ ለመሆኑ በየቀኑ ከምንሰማቸው ዘግናኝና አሳዛኝ ድርጊቶች መገንዘብ ይቻላል። ይህ አስጨናቂ ክስተት በአንድ ወቅት ብቅ ያለና በቀላሉ የሚያባራም አይደለም። ሲከማች የቆየና ስር ያለው ነው፣ ቢሆንም በዘመነ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ጭራሽ እንዲያንሰራራ በመቻሉ አምባገነኖቹ ከሚያደርሱት አረመንያዊ ግድያ ሌላ ሕዝቡ ለእርስበርስ እልቂት እንዲዳረግ አድርገውታል። ስለዚህም የቀውሱ ነባር እና ጊዚያዊ መንሰኤዎች በውል ታውቀው፣ ተመጣጣኝ መፍትሔው ተነድፎለት፣ ተግባር ላይ ካልዋለ የፈራነው ሊደርስ ይችላልና ሳንቀደም በጋራው መፍትቴ ላይ እናተኩራለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ኢትዮጵያዊነት ሐሺሽ ነው፣ ሱስ ነው" የኦሮሚያው ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ

Lemma Megersa

በዚህ ሰሞን የኦሮሚያው ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በባሕርዳር ተገኝተው ያደረጉት ንግግር በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አጎናጽፏቸዋል። "ሐሺሽን ሞክሬው ባላውቅም፤ ኢትዮጵያዊነት ሐሺሽ ነው፤ ሱስ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሻለቃ ዳዊት የዋሽንግተን ሲያትል ንግግር በሞረሽ ዕይታ!

ዳዊት ወልደጊዮርጊስ
ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

(መግለጫ) ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሓሙስ ሰኔ ፩ ቀን ፪ሺህ ፱ ዓ.ም. ቅፅ፭፣ ቁጥር ፲፰

ሰዎች መልካም ሢሠሩና ሲናገሩ ማመስገን፣ መጥፎ ሢሠሩና ሲናገሩ ደግሞ መምከርና መገሰጥ ተገቢ ነው። ምንጊዜም ሁሉም ሰው ሕይዎቱን ሙሉ ስሕተት ብቻ እየሠራ አይኖርም። መልካም ነገሮችም ይሠራል። ልዩነት የሚኖረው የትኛው ሥራው ነው የሚያመዝነው? መልካሙ ወይስ መጥፎ የሚለውን መመዘኑ ላይ ነው። በዚህ ረገድ የሻለቃ ዳዊትን ሥራዎች መዝኖ፤ የማሞገሱም ሆነ የመውቀሱ ተግባር፣ እርሳቸውን የሚያውቁ፣ አብረዋቸው የሠሩ፣ የትምህርትና የሥራ ባልደረቦቻቸው ተግባር ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ ባለቤት ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው ስለባለቤታቸው ይናገራሉ

ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው
የፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ ባለቤት ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው

የፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ ባለቤት ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው በዳላስና ፎርትወዝ በተካሄደው የ፻፳፩ኛው (121ኛው) የአደዋ ድል መታሰቢያ ላይ በባለቤታቸው ላይ የደረሰውን አስገራሚና አሳዛኝ ሁኔታ ገለፁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!