ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማሕበር የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

ጁላይ 21 / 2012

የአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች አመራር ባደረገው ልዮ እና አስቸኳይ ስብሰባ በሃገራችን ኢትዮጵያ ያንዣበበውን ፈርጀ ብዙ አደጋዎች ተገንዝቦ፤ የመፍትሄ መንገዶችን በስፋት መርምሯል።

 

አምባገነኑ ህወሓት መራሽ የኢህዴግ መንግስት በቆራጡ የዲሞክራሲ ታጋይ በአቶ አንዱአለም አራጌ ላይ የበየነውን የእድሜ ልክ እስራትና በእውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም ሆነ በተቀሩት የዴሞክራሲ ሰላማዊ ታጋዮች ላይ ያስተላለፍውን የእረጅም አመታት የእስር ፓለቲካ ውሳኔ እጅጉን አምርረን እንቃወማለን። የሚይዘው የሚጨብጠው የጠፋው አምባገነኑ አገዛዝ በክርስቲያኑም ሆነ በእስላሙ ሃይማኖቶች ጣልቃ እየገባ የሚፈጥራቸው ቀውሶች ሃገራችንን ከማትወጣበት አዘቅት ውስጥ እየከተታት ስለሆነ ባስቸኳይ መቆም አለበት። እየተንገዳገደ ላለው አገዛዝ ተጨማሪ የጥፋት እድልም ሆነ ጊዜ መስጠት አይገባም። የዚህ ስርአት ቁንጮ የሆኑት የአምባገነኑ የአቶ መለስ ዜናዊ ክፉኛ የጤና መታወክን ተከትሎ በሃገርም ውስጥ ሆነ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ስለመጻኢ የሃገራችን እጣፈንታ እጅግ አሳሳቢ መሆን እየተወያየ ያለው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በአምባገነን አገዛዝ እድል ስለሌለው ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የለውጥ ጥማት እውን ሳይሆን አያሌ እድሎች አምልጠዋል። ይህ አሳዛኝ ታሪክ ግን አሁን መቀየር አለበት። ለዚህም ዋናው ዋስትና ሕዝባችን እራሱን በፍጥነት አደራጅቶ ዘለቄታዊነት ያለው ዴሞክራሲያዊ የብልጽግና ስርአት መመስረት ሲችል ብቻ ነው። ... (ሙሉውን መግለጫ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!