የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) Ethiopian People's Congress for United Struggle (Congress)የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ኅዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም. (ኖቨምበር 14 ቀን 2012 እ.ኤ.አ.) የሸንጎው አመራር ካውንስል ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ላይ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። ሙሉው መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል።

 

የሸንጎ አመራር ካውንስል መደበኛ ሰብሰባውን አካሄደ፤ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ (ሸንጎ) ከፍተኛ አመራር ካውንስል መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታና የሸንጎውን ድርጅታዊ ሁኔታ በሰፊው ገምግሟል። ከፈላጭ ቆራጩ የአቶ መለሰ ዜናዊ ሞት በኋላም ያለውን እውነታ፤ በገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ ውስጥ እየታየ ያለውን ውስጣዊ ሁኔታና በሀገሪቱና በሕዝቧ ላይ እያስቀጠለው ያለውን ፖሊሲውን በመመርመር፤ 

 

  

• የሸንጎውን አጠቃላይ ወቅታዊ የትግል አቅጣጫ አጽድቋል።

  

• የሽንጎው የተለያዩ አካሎች በማካሄድ ላይ ያሉትን እንቅስቃሴዎች መርምሮ ትግሉ የሚጠይቀውን ሀላፊነት ለመወጣት የሚያሰችል የማጠናከሪያ መመሪያ ሰጥቷል።

 

• ቀደም ሲል በሸንጎውና በሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪል ማህበራት የተጀመረው ሰፊ የትብብር እና የጋራ ትግል እንቅስቃሴ በተጠናከረ መልክ እንዲቀጥል መመሪያ ሰጥቷል።

 

• የሸንጎውን ራእይና ሰፊ የሰራ እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳውን የአሰራር መዋቅር አሰተካክሎ አሰፈላጊ የሆነውን የሰው ሀይል መድቧል።

 

• በአቶ መለስ እግር በተተካው በአቶ ኃይለማርያም የሚመራው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት በተለመደው ፣ የፖለቲካ አግላይነት ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና የመብት ገፈፋ ጎዳና ዛሬም በመጓዝ ላይ መሆኑን በአጽንዖ ተገንዝቧል። ከዚህም አልፎ አቶ ኃይለማርያምም ሆኑ የመንግሥታቸው ዋና ዋና ባለሰልጣኖች ህዝባችንን እያሰመረረ ያለውን፣ ሲያሰለቅስ የኖረውንና ሀገራችንንም በአደጋ ላይ የጣለውን የአቶ መለሰ ዜናዊን የ 21 ዓመት አጥፌ ፖሊሲ እንዳለ ሊቀጥሉበት እንደፈለጉ ደግመው ደጋግመው ማሰታወቃቸውን በጥሞና ተገንዝቧል። ይህ አሳዛኝ የጥፋት ጎዳና ማንንም የማይጠቅም መሆኑን በመገንዘብ አቶ ኃይለማርያምም ሆኑ ድርጅታቸው ይህን ጉዟቸውን በአስቸካይ እንዲያቆሙና ሁሉን አሳታፊ የሆነ ሰፊ ሀገራዊ መግባባት የሚፈጠርበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹ አሳስቧል።

 

• የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ዋና ዋና ባለስልጣኖች ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የሀገራችንን የግዛት አንድነትና ብሄራዊ ጥቅም በዘለቄታ አደጋ ላይ የሚጥል አስተያየቶችን በተለያዩ መገናኛዎች ሲሰነዝሩ ተደምጠዋል። ይህም በተለይ የሃገራችንን ሰሜናዊ ግዛትና የኤርትራን ጉዳይ የተመለከተ ነው። በአቶ ኃይለማርያም የሚመራው ገዥ ቡድን የሀገር ጉዳይ ከሁሉም በላይ መሆኑን ቢያንስ ዛሬ ተገንዝቦ ከማንኛውም ሀገር አጥፊና ትውልድ ገዳይ ፖሊሲ እንዲቆጠብ ምክርቤቱ አሳሰቧል። የኢትዮጵያ ህዘብም የሀገሪቱን ዘላቂ ጥቅምና ደህንነት በቀጣይነት አደጋ ላይ የሚጥል፣ ጊዜውን ጠብቆ በድፍረት ሀገርን በድጋሜ ለመግደል የሚቃጣ በታኝ አደጋ ነቅቶ እንዲከታተለውና እንዲያከሽፈው ምክርቤቱ አሳሰቧል።

 

• ያለአግባብ የታሰሩት ጋዘጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች በአጠቃላይ ሁሉም የኅሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመሁኔታና በአፋጣኝ እንዲፈቱ ሸንጎ ይጠይቃል፡፡

 

• የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት እና የፀጥታ ኃይሎች እጅግ አሰችጋሪ በሆነ የፖለቲካ ሁኔታ ውሰጥ በህጋዊነት በመንቀሳቀስ ላይ በሚገኙት ታቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በተለይም ደግሞ በመኢአድ እና በመድረክ አባላት ላይ የሚወሰዱትን ቀጣይ የማስፈራራት፣ የማሰር፣ የድብደባ፣ የንብረት ነጠቃ አና በሀሰት ክስ በመወንጀል የኢሰብአዊ እስራትና ማሰቃየትን ሸነጎው መርምሯል። በተለይም ደግሞ በቅርቡ በመኢአድ አባላት ላይ በመላ ሃገሪቱ የተከፈተውን የጥቃት ዘመቻ እንዲሁም የመድረክ እና የመድረክ አባል ድርጅቶች አመራር አባላትን በግፍ በእስር ማሰቃየት መቀጠሉን አስተውሏል። ምክርቤቱ ይህን ቀጣይ የመብት ረገጣ በጥብቅ እያወገዘ ጥቃት እየደረሰባቸው ካሉት ድርጅቶችና አባሎቻቸው ጋር ሸንጎው ያለውን የትግል አንድነት ገልጿል።

 

• በገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ ውስጥ የሚገኙ ለውጥ ፈላጊዎችና ሀገር ወዳዶችም ትግላቸውን እንዲያጠናከሩና ከህዝብ ጎን እንዲቆሙ ሸንጎው ጥሪውን በድጋሜ ያቀርባል።

 

• ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብም መብቱን ለመጎናጻፍ፣ ሀገሩን ለማዳንና የተንሰራፋውን የግፍ አገዛዝ እንዲያከትም የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን ያሰተላልፋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

ኅዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም. (Nov 14, 2012

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)

www.derbiaber.com

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!