ዩሱፍ ያሲን (ንግግር - ስቶክሆልም 21 አፕሪል 2012)

በስዊድን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ወጣቶች ንቅናቄ ኮንፈረንስ

ልዩነቶቻን መካድ ወይም በሃይል አንድ ማድረግ ፍላጎት

ልዩነቶቻችን ውበታችን ነው የተሰኘው አባባል ብርቄዬ መፈክር ነው። OUR DIVERSITY IS OUR BEAUTY የተሰኘውን የፈረንጅኛው አባባል ትርጉም መሆኑ ነው። በዘመነ ደረግ ተብሎዋል። በኢሕዴአግ ዘመንም ተፎክሮበታል። እንከን የማወጣለት ግሩም አባባል ነው። ምክኒያቱ ጉራማሌነታችን ውበታችን መሆኑ አያከራክርምና። ልዩነቶቻችን ብርቄዬ ጌጦቻችን ናቸው። ጥያቄው እውነት ይህው ግሩምና አቻቻይ መፈክር ተግባራዊ መሆን ይቻላል ወይ ነው በዛሪዬቷ ኢትዮጵያችን። አነጋጋሪና አነታራኪው እነዚሁ ውብ የሆኑትና የሚንኩራራባቸው ልዩነቶቻን ለውዝግብ ምክኒያት እና መነሻ የመሆናቸው ጉዳይ ነው። የማንነት ፖልቲካ መሠረቱ እነዚሁ ልዩነቶቻችን መሠረት አድርጎ ወገን ለይቶ መደራጀትና አንዱ ከእነሱ የተለየውን ”ሌለኛ” የተሰኘውን ተፃርሮ መፋጠጥ ነውና። አንዳንድ ጊዜም መግጠም ነው።


በረዥሙ ታሪካችን ልዩነቶቻችን ማስተናገድ ችለናል ማለት አያስደፈርም። ዲሞክራሲ በመሠረቱ የሥልጣንን ውድድር በሰለማዊ መንገድ አስተናግዶ በመንግሥት ሥልጣን ላይ ተራ በተራ በመራጩ ሕዝብ ይሁንታ መፈራረቅ ነው። በታወቁ በሕግ በተደነገጉ የጫውታው ሕጎች መሠረት። ተወዳደሮ የሕዝብን ይሁንታ ያጣው ወገን ደግሞ ወሳኔውን ተቀብሎ ከሥልጣን ተሰናብቶ ወደ ተቃዋሚ ቦታ መዞር ነው። ጊዜውን ጠብቆ እንደገና ተወዳደሮ የመራጩን ሕዝብ ፈቃጅነት እንደገና መሻት ነው። በሥልጣን ፊርሪቆሹ በምርጫ ሳጥን አማካኝኘት ብቻና ብቻ ሲሆን ነው እንግዲህ እውነትም ልዩነቶቻችን ተቀበለንንም አስተንግደንም የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ከሥር መገንባት ጀመረናል የሚንባለው። ልዩነቶቻችን ማኔጅ ማድረግ ግን አልቻልንም፤ በረዥሙ ታሪካችን። … (ሙሉውን ንግግር በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ