የገዢውን ፓርቲና መንግስት ሽፍትነት ያጋለጠው የምርጫ ቦርድ ውሳኔ በኢትዮጵያዊን ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም!!! [አንድነት-መግለጫ]

አንድነት - መግለጫ

ጥር 21/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ የምርጫ ቦርድ የሚባል ተቋም ያለበትን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህ ደረጃ እንዲዋራድ ከጀርባ ሆኖ አመራር የሚሰጠው ገዢ ፓርቲም ሆነ መንግሰት በዚያው ልክ የሚገባቸውን የተዋረደ ደረጃ የያዙበት ዕለት ነው ብለን እናምናለን። አንድነት ፓርቲ አንድም የህግ ጥሰት ሳይፈፅም የሚያደርጋቸውን ሁሉ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና በሀገሪቱ ህግ እየፈፀመ ባለበት ሁኔታ በህግ ሽፋን የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና ሬዲዮ፣ የመንግሰት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የከፈቱት ዘመቻ የመጨረሻ የሆነውን አንድም ህጋዊ መሰረት የሌለውን ህገወጥ ውሳኔ በአንድነት ፓርቲ እና አባላት ላይ አሰተላልፈዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ተካሄዷል ብለን አናምንም!

ከአንድነት ፓርቲ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ምርጫ ቦርድ ነፃና ገለልተኛ እንዳልሆነ የሚገነዘብ ቢሆንም ባለፈው ታህሳስ 12/04/2007 ዓ.ም የተካሄደው የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ በሀገራችን የምርጫ ቦርድ አለ ወይ?! እንዲል አድርጎታል። የታህሳሱ 12/04/2007 ዓ.ም የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ነፃና ገልልተኛ አልነበረም ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የምርጫ ህጉን ተከተሎ ያልተካሄደ ሌላው ይቅርና የራሱ የምርጫ ቦርድ መመሪያን እንኳን ያልተከተለ ከመሆኑ አንፃር ተካሄዷል ብለን አናምንም። እንዲህ ዓይነቱ ድምዳሜ እንድንደርስ ያደረጉን ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም በዋናነት የሚከተሉት ነጥቦች ከግምት ውስጥ አስገብተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለሰላማዊ ዜጎች ጥያቄ ጥይት መፍትሄ አይሆንም!

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

በባህርዳር ከተማ ለዘመናት የእምነት ቦታ ሆኖ ለአምልኮ አገልግሎት ሲውል የነበረ የህዝብ ይዞታ በማያውቁትና ባልመከሩበት ሁኔታ ባለሀብት እንዲያለማው በከተማው መስተዳድር ተሰጥቷል መባሉን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ባዶ እጃቸውን ሆነው በሰላማዊ መንገድ ባሰሙት የተቃውሞ ድምጽ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን በወሰደው ዘግናኝና አሰቃቂ በጥይት የታገዘ የኃይል እርምጃ እስካሁን የአምስት ንፁኃን ዜጎች ህይወት ተቀጥፏል፡፡ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ አዛውንት እማሆይንና አካል ጉዳተኛ ጨምሮ በርካቶችን በማቁሰል የአካል ማጉደል ደርሶባቸዋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዜጎችን ሰቆቃ እና በደል ችላ ማለት ከግፈኞች ጋር እንደመተባበበር ይቆጠራል!! (ሰማያዊ ፓርቲ)

Blue party ሰማያዊ ፓርቲሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የሳውዲ መንግስት እያደረሰ ያለውን እስራት፣ ስቃይ እና ግድያ በመቃወም እና ህይወታቸው ላለፈ፣ ለተደበደቡ እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ህዝቡ ሃዘኑን እንዲገልጽ በመጪው እሁድ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ ላይ የሚሮጡ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ ጥሪ ማስተላለፉ የሚታወቅ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእግዚአብሔር ምስክሮች እንሁን (ጸደንያ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክ በቫንኩቨር)

በስመ አብ በወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!!

 

ከቫንኮቨር ፀደንያ ቅድስት ማሪያም  ቤተክርስትያን  የተሰጠ የአቋም  መግለጫ በሕጋዊውና በብፁእ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመራው የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያስተላለፈዉን የአቋም  መግለጫ ስለመደገፍ።

 

ለአምላካቸዉ  ለእግዚአብሄር አምላክነት በግልፅ ስለመሰከሩና  ስለተጋደሉ አባቶቻችን በቅዱሳን  መጻህፍት እንደተፃፈው   በብሉይ ኪዳን   ነቢያት አባቶቻችን ፣ በአዲስ ኪዳን ሐዋሪያት አባቶቻችን ፣ ባደረጉት ተጋድሎዎች ተጠብቆ የኖረዉን ስርዓት እኛም  በዚህ ዘመን የምንገኝ በክርስቶስ ደም የቆመችዉን የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችንን ዶግማና ቀኖናዋን  ሳይፋረስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ብሎም ለትውልድ የማስተላልፈ  ክርስቲያናዊ አደራ አለብን።

 

(ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!