"ኢትዮጵያዊነት ሐሺሽ ነው፣ ሱስ ነው" የኦሮሚያው ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ

Lemma Megersa

በዚህ ሰሞን የኦሮሚያው ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በባሕርዳር ተገኝተው ያደረጉት ንግግር በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አጎናጽፏቸዋል። "ሐሺሽን ሞክሬው ባላውቅም፤ ኢትዮጵያዊነት ሐሺሽ ነው፤ ሱስ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሻለቃ ዳዊት የዋሽንግተን ሲያትል ንግግር በሞረሽ ዕይታ!

ዳዊት ወልደጊዮርጊስ
ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

(መግለጫ) ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሓሙስ ሰኔ ፩ ቀን ፪ሺህ ፱ ዓ.ም. ቅፅ፭፣ ቁጥር ፲፰

ሰዎች መልካም ሢሠሩና ሲናገሩ ማመስገን፣ መጥፎ ሢሠሩና ሲናገሩ ደግሞ መምከርና መገሰጥ ተገቢ ነው። ምንጊዜም ሁሉም ሰው ሕይዎቱን ሙሉ ስሕተት ብቻ እየሠራ አይኖርም። መልካም ነገሮችም ይሠራል። ልዩነት የሚኖረው የትኛው ሥራው ነው የሚያመዝነው? መልካሙ ወይስ መጥፎ የሚለውን መመዘኑ ላይ ነው። በዚህ ረገድ የሻለቃ ዳዊትን ሥራዎች መዝኖ፤ የማሞገሱም ሆነ የመውቀሱ ተግባር፣ እርሳቸውን የሚያውቁ፣ አብረዋቸው የሠሩ፣ የትምህርትና የሥራ ባልደረቦቻቸው ተግባር ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ ባለቤት ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው ስለባለቤታቸው ይናገራሉ

ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው
የፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ ባለቤት ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው

የፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ ባለቤት ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው በዳላስና ፎርትወዝ በተካሄደው የ፻፳፩ኛው (121ኛው) የአደዋ ድል መታሰቢያ ላይ በባለቤታቸው ላይ የደረሰውን አስገራሚና አሳዛኝ ሁኔታ ገለፁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ እንዲህ እያሰበ መሆኑ ጭምጭምታ ተሰማ (ሞረሽ )

Moresh wegenéወያኔ እንዲህ እያሰበ መሆኑ ጭምጭምታ ተሰማ፤ ዕውነት ከሆነ ጥቅምና ጉዳቱ ምን ይሆን?

ዛሬ ላለንበት ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ዐማራ የተሰኘውን ነገድ ከመኖር ወደ አለመኖር ያደረሳቸውን ምክንያት መገንዘብ፣ ለምንፈልገው መፍትሔ ጥርጊያ መንገድ ይከፍትልናል። ከትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (የትግሬ-ወያኔ) የትግል ጉዞ እንደምንረዳው፣ ችግር በገጠመው ቁጥር፣ ዓላማውንና ቆሜለታለሁ የሚለውን ሥርዓት እንደ እባብ ገላ በሌላ በመተካት ጊዜ ይገዛል። ከማኦ ዜ ዱንግ እስከ ኤንቨር ሆጃ፣ ከካርል ማርክስ እስከ ሌኒን፣ ከሂትለር እስከ ደቡብ አፍሪቃ የአፓርታይድ አገዛዝ ያሉትን ርዕዮተ-ዓለሞች ካንዱ ወደ ሌላው ከብርሃን ፍጥነት በፈጠነ ሁኔታ በመቀያየር ኅልውናውን ለማራዘም ይሞክራል። የትግሬ-ወያኔ ላለፉት 25 ዓመታት ያራመደው በዘር ጥላቻ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካና አገሪቱንና ሕዝቡን በነገድ ሸንሽኖ ያደረሰው ጥፋት፣ በተለይ ከ2007 እስከ 2009 ዓም ያሉት ዓመታት ሕዝቡ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ስለሆነበት፣ የአገዛዙን የአፈናና የእመቃ መዋቅር በመበጣጠስ በየአቅጣጫው ያስነሳው ተቃውሞ የትግሬ-ወያኔን አገዛዝ ከሥሩ እያናጋው በመምጣቱ ምክንያት «አልሸሹም ዘወር አሉ» ዓይነት እና፣ «የጥልቅ ተሐድሶው» መገለጫ እንዲሆን የታሰበ የመንግሥት የአደረጃጀት ለውጥ ለማድረግ የታሰበና ወደዚህም ግብ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ በመሰማት ላይ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከጥር 5 እስከ 6 ቀን 2009 ዓ.ም (ጃንዋሪ 13-14) በዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደው ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

የአገር አድን የቀውጢ ጊዜ ግብረ ኃይል ተቋቋመ፤ ሁነኛ የአንድነት ኃይሎች አማራጭ በአጭር ጊዜ የማውጣት ሂደት ላይ ስምምነት ተደረሰ

አቀፍ የምክክር ጉባኤ

አዘጋጅ የሆኑት ሶስት ድርጅቶች (ሸንጎ፣ የሽግግር ምክር ቤትና የወጣቶች ንቅናቄ) ቀደም ሲል ሲያደርጉት የነበረውን ግንኙነት በማደስ ላለፉት 7 ወራት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ተከታታይ የሁለትዮሽ፤ የወል ግንኙነቶችን እና ጥረቶችን በማድረግ ከቆዩ በኋላ፤ በአገራችን ጉዳይ ላይ ባለ ድርሻ ለሆኑ ለሁሉም የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች ኦፊሽያል ጥሪ በማድረግ እንደሚገኙ በደብዳቤ ካረጋገጡት 10 ድርጅቶች መካከል 9ኙ በጥር 5 እና 6 ቀን 2009 ዓ፡ም (ጃንዋሪ 13 - 14 ቀን 2017) ተገኝተው የተሳካ ጉባዔ በዋሺንግተን ዲሲ አካሂደዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“በሳይበር የሚደረግ ጥቃት ከዓላማችን አላሰናከለንም” - ከዘ-ሐበሻ የተሰጠ መግለጫ

Screen shot 2016 12 14 at 7 51 21 pm“እንኳን በሳይበር የሚደረግ ጥቃት ይቅርና የወያኔ ተገንጣይ መንግስት እስር ቤትም ከዓላማችን አላሰናከለንም” - ከዘ-ሐበሻ የተሰጠ መግለጫ

ዘ-ሐበሻ ድረገጽ ከተመሰረተች 9 ዓመት ሆኗታል። ባለፉት 9 ዓመታት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎችን መረጃ ከሚያቀብሉ የመረጃ መረቦች መካከል አንዷ በመሆን በአማራጭነት ሚድያነት አገልግላለች። በየዕለቱ ድክመቶቻችን በማረም ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር በመራመድ አሁንም ተመራጭና ተአማኒ ሚዲያ ለመሆን ተግተን እየሰራን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጃዋር መሐመድ በሚንያፖሊስ መስከረም 23 ቀን 2009 (ኦክቶበር 3, 2016) ያደረገው ንግግር

Jawar Mohammed. ጃዋር መሐመድ

ቅድመ ንባብ ማስታወሻ:-

ይሄን የጃዋርን ንግግር በጥንቃቄ ተርጉመው ያደረሱን ለአንዲት ኢትዮጵያ ህልውና የታመነ ልብ እና የጸና ዓላማ ያላቸው፤ ብሎም ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንጂ መፈጠር ያለባት ኢትዮጵያ ህዝብ መከፋፈል የለበትም ብለው በታላቅ ሀገራዊ ተጋድሎ ውስጥ ያሉ የኦሮሞ ልጆች ናቸው። መጀመሪያ እነሱን በኢትዮጵያ ህዝብ ስም አመሰግናለሁ። ቀጥሉም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይሄን የጃዋርን ንግግር እንዲያነበው እጋብዛለሁ። መልካም ንባብ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!