Ethio-mediaበመላው ዓለም ለምትገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን!

በቅድሚያ ልባዊ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።

ሰሞኑን በግል የኢሜይል ጥሪ ልኬላችሁ እጅግ አበራታች የገንዘብ እርዳታችሁንና ድጋፋችሁን ለላካችሁልኝ፣ በመላክ ላይ ላላችሁት ወገኖቼ ልባዊ ምስጋናዬን እንድገልጽ አፈልጋለሁ።

ቀጣዩ መልዕክት ለመላው የኢትዮሚድያ ወዳጆች በኢሜይል ማዳረስ ስለማይቻል ጥሪውን በድረገጻችንና በተለያዩ ዌብሳይቶች፣ ሬድዮና ቲቪ እንዲሁም በሶሻል ሚድያ በኩል እንዲሰራጭ አድርጌአለሁ።

ኢትዮሚድያ እ.አ.አ. በ2002 ኢትዮጵያውያን ወገኖቹን ዜናዎችንና ልዩ ልዩ መረጃዎችን በማቅረብ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ እነሆ ወደ 16ኛው ዓመት እየገባ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ የጣለውን የጎሣ ፖለቲካ እየታገለ፣ ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን እንዳይሸርሸር በተለያዩ ምሁራን የሚጻፉትን ጦማሮች ለንባብ አብቅቷል። ለፍትሕ፣ ለእኩልነትና ለዴሞክራሲ የሚደረገውን ትግል እንዲሳካ የበኩሉን ከፍተኛ አገልግሎት ሰጥቷል።

በተለይም ብዙም ነፃ ሚድያ ባልነበረበት በምርጫ 97 ወቅት፣ ኢትዮሚድያ በቅንጅት አመራር ከፍተኛ ሽልማት አግኝቶ አልፏል። የሚድያው ተዓማኒነት ከኢትዮጵውያን ወገኖች አልፎ በዩ.ኤስ. አሜሪካ ኮንግሬስ አባላት፣ በአውሮፓ ሕብረት እና በሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ እስከመሆን ደርሷል። ኒውዮርክ ታይምስም ‘ኢትዮሚድያን’ ተዓማኒ ድረገጽ ሲል ይጠቅሰዋል።

በዚህ በኢትዮሚድያ ድል ዘወትር ተኝቶ የማያውቀው የወያኔ መንግሥት ኢትዮሚድያን ለማዳከም ከተቻለም ለማዘጋት ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም። ኢትዮሚድያ በያሁ ሰርቨር (Yahoo Server) ላይ የተገነባ ቢሆንም፣ ብዙ ጊዜ ሰርቨሩን ሰብረው ለመግባት እና ኢትዮሚድያ ለማጥፋት ብዙ ሙከራዎች እንደተደረጉ የያሁ ኢንጂንየሮች የዘወትር ማስጠንቀቂያ ነበር። ይሁንና በተናጠል እና በድርጅት በኢትዮሚድያ ላይ የተወረወሩ ጥቃቶች መክቶ ይህ አንጋፋ የሕዝብ ሚድያ እስከዛሬው ድረስ ዘለቋል።

አሁን ግን ከ10 ዓመት በፊት የነበረን የዌብ ቴክኖሎጂ ተጠቅመን የገነባነውን ኢትዮሚድያ አሁን የዌብ ቴክኖሎጂ የደረሰበት ዕድገት ጋር ሊመጣጠን ስላልቻለ የግድ እንደአዲስ ድረገጹ ማሠራት አስፈልጓል። አዲሱ የዌብ ቴክኖሎጂም የድረገጹን ሴኩሪቲ እጅግ በተሻለ ሁኔታ ከተለያዩ አደጋዎች ከመከላከሉም ሌላ፣ ተጨማሪ የኦዲዮ፣ ቪድዮ፣ የውይይት መድረክና የቴሌኮንፈረንስ አገልግሎቶች ይኖሩታል።

ድረገጹን እንዳሠራ የተጠየኩት ገንዘብ ግን በግሌ የምችለው ስላልሆነ ፊቴን ሁሌም ለምኮራባችሁ ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንዳዞር አስገድዶኛል። ‘አምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሽክሙ፣ ለ50 ሰው ግን ጌጡ’ እንዳሉት አበው ይህን ሽክም በጋራ እንድንወጣው ኢትዮሚድያን ለመርዳት አቅማችሁን የሚችለውን የገንዘብ እርዳታ (donation) እንድታደርጉ በትህትና አጠይቅሀለሁ።

እርዳታውን ለመላክ ሦስት አማራጭ መንገዶች አሉ።

1ኛ) የGoFundMe ቀጣይ ሊንክ በመጫን https://www.gofundme.com/help-expand-ethiomedia-services
2ኛ) የፔይ ፓል አካውንት ካልዎት ገንዘቡን ለ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ብሎ መላክ ይቻላል።
3ኛ) ተከፋይነቱ ለኢትዮሚድያ የሚል ቼክ ወይም ማኒ ኦርደር በሚቀጥላው የፖስታ አድራሻ በመላክ ይሆናል፦

Ethiomedia
P.O. box 1757
Lynnwood, WA 98036

ኢትዮሚድያን በዘመናዊው የዌብ ቴክኖሎጂ ለመገንባት የሚያደርጉትን የገንዘብ እርዳታ በቅድሚያ አመሰግናለሁ።

አብርሃ በላይ፣ ዋና አዘጋጅ
(425) 314-5099
ኢትዮሚድያ ድረ-ገጽ
ሲያትል፣ ዋሽንግተን

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!