አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ክስ ተመሰረተባቸው

አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ

ኢዛ (ረቡዕ ሚያዝያ ፱ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. April 17, 2019)፦ ከዳሽን ቢራ አክሲዮን ማሕበርና ከጥረት ኮርፖሬት ኩባንያዎች ጋር ተያይዞ በምዝበራ/ሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ክስ ተመሰረተባቸው። ተከሳሾቹ ጠበቆቻችን የክርክሩን ሒደት ከአዲስ አበባ ኾነው በፕላዝማ ይከታትሉልን ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡትን ጥያቄ ችሎቱ ውድቅ አደረገው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሴቶችም በወንዶችም የስቶክሆልም ማራቶንን ውጤት ተቆጣጠሩት

አትሌት አብርሃ | Abraha Milaw
አትሌት አብርሃ የስቶክሆልም ማራቶንን ካሸነፈ በኋላ። (ፎቶ፣ የስዊድኑ TV4)

ኢዛ (ቅዳሜ ግንቦት ፳፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. June 3, 2017)፦ በዛሬው ዕለት በስቶክሆልም፣ ስዊድን በተደረገው ፴፱ኛው የስቶክሆልም ማራቶን ኢትዮጵያውያኖቹ አትሌቶች በሴቶችም፣ በወንዶችም አንደኛና ሁለተኛ በመሆን ውጤቱን ተቆጣጠሩት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አሰግድ ተስፋዬ በድንገት አረፈ

Asseged Tesfaye
የቀድሞ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሰግድ ተስፋዬ፣ በ፵፯ ዓመቱ አረፈ። (ፎቶ፣ ማኅበራዊ ድረ ገጽ)

ኢዛ (ቅዳሜ ግንቦት ፳፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. June 3, 2017)፦ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የእግር ኳስ ተጫዋች የነበረው አሰግድ ተስፋዬ፤ በዛሬው ዕለት ከልምምድ መልስ በመታጠቢያ ቤት ውስጥ ወድቆ በአርባ ሰባት ዓመቱ በድንገት ሕይወቱ አለፈ። ሥርዓተ ቀብሩ ሰኞ ግንቦት ፳፰ ቀን ከሰዓት በኋላ በስምንት ሰዓት በቅድስት ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢሬቻ በዓል ላይ ኹከት አስነስተዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው

የኢሬቻው እልቂት
የኢሬቻው እልቂት፣ መስከረም ፳፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. (ፎቶ፣ Reuters)

ኢዛ (ዓርብ ግንቦት ፲፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. May 26, 2017)፦ የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ በኢሬቻ በዓል ላይ ለሃምሳ አምስት ሰዎች መሞት ምክንያት የኾነውን ኹከት እና ብጥብጥ አስነስተዋል ባላቸው የመጀመሪያዎቹ ሁለት ግለሰቦች ላይ ክስ እንደመሰረተባቸው ተዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወጣት ፖለቲከኛው ዮናታን ተስፋዬ ስድስት ዓመት ከመንፈቅ ተፈረደበት

ዮናታን ተስፋዬ | Yonatan Tesfaye
ወጣቱ ፖለቲከኛ ዮናታን ተስፋዬ በፌስቡክ ጽሑፍ 6 ዓመት ከ6 ወር እስር ተፈረደበት

ኢዛ (ኀሙስ ግንቦት ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. May 25, 2017)፦ ዛሬ በአዲስ አበባ ያስቻለው የከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀድሞው የሠማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዮናታን ተስፋዬ ላይ በተመሰረተው የአሸባሪነት ወንጀል ክስ የስድስት ዓመት ከስድስት ወር እስራት ቅጣት ፈረደበት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም በጄኔቭ ተቃውሞ ገጠማቸው

Anti-Tedros Adhanom
በዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ በጄኔቭ ተቃውሞ ሲቀርብ

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፲፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. May 22, 2017)፦ ለዓለም የጤና ድርጅት ለዳይሬክተርነት በእጩነት ከቀሩት ሦስቱ አንዱ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም በዛሬው ዕለት ተቃውሞ እንደገጠማቸው ኢሳት በሰበር ዜናው ዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እውቁ ፖለቲከኛና አንጋፋው ምሁር አቶ አሰፋ ጫቦ አረፉ

Assefa Chabo
አቶ አሰፋ ጫቦ

ኢዛ (ሰኞ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. April 24, 2017)፦ በአንደበተ ርዕቱነታቸውና በብዕራቸው በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት አቶ አሰፋ ጫቦ እሁድ ሚያዝያ ፲፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. (April 23, 2017) በሰባ ሦስት ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በግብጽ የሆሳዕናን በዓል እያከበሩ የነበሩ አርባ ሦስት ሰዎች በሽብርተኞች ቦምብ ተገደሉ

አንድ መቶ ሰዎች ቆሰሉ
ጥቃቱ የተፈጸመው በታንታ እና በአሌክሳንድሪያ ከተሞች ነው
ኃላፊነቱን አይሲስ ወስዷል

Church bombing in Tanta, Egypt
በግብጽ ታንታ ከተማ በሽብርተኞች ቦንብ ጥቃት የደረሰበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ

ኢዛ (እሁድ ሚያዝያ ፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. April 9, 2017)፦ ክርስቲያኖች የሆሳዕና በዓልን እያከበሩ ባሉበት በዛሬው ዕለት፣ በግብጽ ሁለት ከተሞች አርባ ሦስት ሰዎች በሽብርተኞች ሲሞቱ አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ሰዎች ቆሰሉ። የሽብር ጥቃቱን ኃላፊነት አይሲስ መውሰዱ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአንበሳ አውቶቡስ ዲፖ የ፵፮ ሚሊዮን ብር ንብረት በእሳት አደጋ ወደመ

Anbesa autobus

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Feb. 13, 2017)፦ አዲስ አበባ፣ ጀሞ አካባቢ በሚገኘው በአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ጋራዥ ላይ ዛሬ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በደረሰ እሳት አደጋ አርባ ስድስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስናይፐር የታጀበው ጥምቀት በጎንደር

Timket festival

ከጎንደር ታቦቱን ከመቅደሱ ገብተው መሸከም እስኪቀራቸው ድረስ የመንግሥት ወታደሮች ካህናቱን ቶሎ በሉ፣ ቶሎ በሉ እያሉ ያጣድፏቸው ነበር። ታቦት በራሳቼው ላይ የተሸከሙ አባቶች ሁለት እጆቻቸው ታቦቱን ቢደግፉም እንባዎቻቸው በጎንደር አስፋልት ላይ ጠብ፣ ጠብ፣ እያሉ ሲፈሱ ከበርካታ ካህናት ዓይኖች ቀረብ ብዮ አስተውያለሁ፣ መስቀል ኃይል ነው ብላ የምታምን ቤተክርስቲያን ዛሬ ስናይፐር ኃይል ነው የሚል መንግሥት በስናይፐር የጎንደር ታቦቶች እንዲታጀቡ አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!