Haile Geberselase

ኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ኅዳር ፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. November 11, 2016):- የዓለም አቀፉ የማራቶንና የረዥም ርቀት ማኅበር በዛሬው ዕለት ከሳምንት በፊት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ኹኖ የተመረጠውን አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴን የዕድሜ ልክ ሽልማት ወደር የማይገኝለት የማራቶን ሯጭ የሚል የክብር ስያሜ በመስጠት ለክብሩ የራት ግብዥ የማራቶን ውልድት ከተማ በሆነችው የግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ አዘጋጅቶለታል።

እ.ኤ.አ. ከ2006 እስከ 2009 በዓለም ላይ ባሉ 110 አገሮች በተደረጉት 410 ዓለም አቀፍ ውድድሮች፤ አራት ጊዜ በማከታተል በማሸነፉና በ2007 እና በ2008 እ.ኤ.አ. የዓለምን ክብረወሰን በመስበሩ ይህንን ክብር መጎናጸፉ ታውቋል።

በዓለም በረዥም ርቀት ሩጫ ወደር የማይገኝለት የሚል ስያሜን የተጎናፀፈው አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ. በ2006፣ 2007 እና 2008 በተከታታይ የዓመቱ ኮከብ አትሌት በማለት ለሦስት ዓመታት የዓለም አቀፉ የማራቶንና የረዥም ርቀት ማኅበር እንደሸለመው ይታወሳል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ