Almaz Ayana and Husain Bolt

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 3, 2016)፦ ዓለማቀፉ የአትሌቲክስ ማኅበር ፌደሬሽን ኢትዮጵያዊቷን የ10 ሺህ ሜትር ሪኮርድ ባለቤት አልማዝ አያናን የ2016 የዓለም ምርጥ አትሌት በማለት ትናንት ማምሻውን የሸለማት ሲሆን፣ ከወንዶ ትሌቶች ደግሞ ጃማይካዊው የአጭር ርቀት ሯጭ ዩሴን ቦልት ተሸላሚ ሆኗል።

አልማዝ አያና በ2016 በተካሄደው የ10 ሺህ ሜትር ውድድር በሚያስገርም ፍጥነትና በሰፊ ልዩነት 29፡17፡45 ደቂቃ በመግባት አዲስ ክብረወሰን የጨበጠች ሲሆን፣ ባለፈው ክረምት በሪዮ ዲጄኔሮ በተካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር ላይ ደግሞ በ5 ሺህ ሜትር ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች።

በዓለማቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን እስካሁን ምርጥ አትሌት ተብለው የተመረጡ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚከተሉት ናቸው፦

፩) እ.ኤ.አ. 1998 አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ
፪) እ.ኤ.አ. 2004 እና 2005 አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
፫) እ.ኤ.አ. 2007 አትሌት መሰረት ደፋር
፬) እ.ኤ.አ. 20015 አትሌት ገንዘቤ ዲባባ
፭) እ.ኤ.አ. 2016 አትሌት አልማዝ አያና

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!