Journalist Temesgen Desalegne

ኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ታህሳስ 5 ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 14, 2016)፦ ላለፉት ስምንት ተከታታይ ቀናት ቤተሰቦቹ በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ወህኒ ቤቶች ሁሉ ዞረው ሲፈልጉ ሰንብተዋል። አቤቱታቸውንም ለሚመለከተው ክፍል አሰምተዋል። ይሁን እንጂ ተመስገንን አየሁ የሚል አንድም የወህኒ ቤት አስተዳዳሪ አልተገኘም።

ከሁለት ዓመት በፊት በፍትህ ጋዜጣ ላይ በሚያወጣቸው ጽሁፎቹ ምክንያት የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት ወደ ወህኒ የተጣለው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ በወህኒ ቆይታው ለአመክሮ የሚሆን መልካም ሥነ ምግባር ቢኖረውም የወህኒ ቤቱ ገዢዎች ግን "ተገንገም" የሚል ተጨማሪ ሕግ አውጥተውበት እሱም ሳይስማማ በመቅረቱ ሊታሰር ከሚገባው ጊዜ በላይ እንዲቆይ ተወስኖበታል።

ተመስገን በዚህ ሁለት ዓመት በርካታ ሕመሞችን ያስተናገደ ሲሆን፣ ወህኒ ቤቱ በበርካታ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች ላይ እንደሚያደርገው ሁሉ ተገቢውን ሕክምና እንዳይከታተል ተደርጓል።

ከሰሞኑ ቤተሰቦቹ ለጥየቃ ሄደው "እዚህ የለም" የሚለውን መጥፎ ዜና በማኅበራዊ ድረ ገጾች ካሰራጩ በኋላ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች "መንግሥት ጋዜጠኛውን የት እንዳሰረው በአስቸኳይ እንዲገልጽ" ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።

ይሁንና ካልተረጋገጡ ምንጮች እንደሚሰማው "አንተ በጻፍካቸው ጽሁፎች ምክንያት ነው ይህ ህዝባዊ ተቃውሞ የተቀሰቀሰው። ብንለቅህ ተቃውሞውን ታባብሰዋለህ" በሚል ተመስገንን ላለመፍታት ምክንያት እየፈለጉበት እንደሆነ ነው።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!