Samara campus viewኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ታህሳስ ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 30, 2016)፦ በአፋር ክልል የሚገኘው ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ማታ ከምሽቱ አንድ ስዓት ተኩል አካባቢ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ እንደደረሰበት ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ የደረሰው ዘገባ አስረዳ። በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ ባይኖርም፤ በቃጠሎው የወደመው ንብረት ግምቱ ምን ያህል እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም።

የእሳት ቃጠሎው በምን ምክንያት እንደተነሳ ያልታወቀ ሲሆን፣ ጉዳዩን ለማጣራት የክልሉ ፖሊስ አቅም ስለሌለው፣ ከፌዲራል መንግሥቱ የእሳት አደጋ ምርምር ቡድን እስኪመጣለት የክልሉ ፖሊስ እየጠበቀ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

ቃጠሎው ምክንያት የዩኒቨርሲቲው ዕቃ ግምጃ ቤት ሙሉ በሙሉ በውስጡ ከነበሩት ንብረቶች ጋር መውደማቸው ታውቋል። የዕቃ ግምጃ ቤቱም ሙሉ በሙሉ ውድሟል።

ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ የተነሳውን ይኽንኑ የእሳት አደጋ ለማጥፋት አራት ሰዓታት የፈጀ ሲሆን፣ ከዕቃ ግምጃ ቤቱ ወደ ሌሎች ሕንጻዎች እሳቱ ሳይዛመት በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል።

የቃጠሎው መንስዔ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተደጋጋሚ የሚደመጡ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ከሙስና ጋር የተገናኘ ሊሆን እንደሚችል አስተያየታቸውን የሰጡ አሉ።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ