አቤል ዋበላ ከሚያዝያ 2006 ጀምሮ ለ18 ወራት "በፀረ ሽብርተኝነቱ" አዋጅ ከዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ጋር ታስሮ ከርሞ በጥቅምት 2008 በነጻ ሲሰናበት የቀድሞ መሥሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ "መልሼ አልቀበልህም" በማለቱ አቤል ክስ መመሥረቱ ይታወሳል። አየር መንገዱም "እንዲያውም ለሥራ ሥልጠና ያወጣሁበትን ወጪ ካሣ ይክፈለኝ" የሚል ሌላ ክስ መሥርቶበት፣ አቤል የመሠረተው ክስ እስኪጠናቀቅ የአየር መንገዱ ክስ በእንጥልጥል እንዲቆይ ተደርጎ ነበር።

ዛሬ፣ ታኅሣሥ 27/2008 ጠዋት በዋለው የቦሌ መ/ደ/ፍ/ቤት ምድብ ችሎት አየር መንገዱ "ከ30 ቀን በላይ ታስሮ የቀረበትን ሠራተኛ ወደ ሥራ ገበታው የመመለስ ግዴታ የለበትም" በማለት ለአየር መንገዱ ፈርዷል።

ምንጭ፤ ዞን9

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!