አንድ መቶ ሰዎች ቆሰሉ
ጥቃቱ የተፈጸመው በታንታ እና በአሌክሳንድሪያ ከተሞች ነው
ኃላፊነቱን አይሲስ ወስዷል

Church bombing in Tanta, Egypt
በግብጽ ታንታ ከተማ በሽብርተኞች ቦንብ ጥቃት የደረሰበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ

ኢዛ (እሁድ ሚያዝያ ፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. April 9, 2017)፦ ክርስቲያኖች የሆሳዕና በዓልን እያከበሩ ባሉበት በዛሬው ዕለት፣ በግብጽ ሁለት ከተሞች አርባ ሦስት ሰዎች በሽብርተኞች ሲሞቱ አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ሰዎች ቆሰሉ። የሽብር ጥቃቱን ኃላፊነት አይሲስ መውሰዱ ታውቋል።

የመጀመሪያው ጥቃት የተፈጸመው በታንታ ከተማ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በፈነዳ ቦንብ የሃያ ሰባት (፳፯) ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ ሰባ ስምንት (፸፰) ሰዎች መቁሰላቸው ታውቋል።

ሁለተኛ ጥቃት የተፈጸመው ከሰዓታት በኋላ በአሌክሳንድሪያ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል በመባል በሚጠራው ታሪካዊው የክርስትና ቤተክርስቲያን ሲሆን፣ ጥቃቱን የፈጸመው በራሱ ላይ ቦንብ የታጠቀ አጥፍቶ ጠፊ ነበር።

በአሌክሳንድሪያው ቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን በደረሰው የሽብር ጥቃት ሕይወታቸውን ያጡት ሰዎች ቁጥር አስራ ስድስት (፲፮) ሲሆን፣ የቆሰሉት ደግሞ አርባ አንድ (፵፩) ሰዎች መሆናቸውን የግብጽ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል።

የአሌክሳንድሪያው ፓትርያርክ ዳግማዊ ቴዎድሮስ የሆሳዕናን በዓል በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ውስጥ ሲመሩ የነበሩ ቢሆንም፤ ከጥቃቱ መትረፋቸው ታውቋል። አጥፍቶ ጠፊው ፓትርያርኩን የመግደል ዕቅድ ይኑረው አይኑረው ግን እስካሁን የተረጋገጠ ነገር የለም።

Church bombing in Tanta, Egypt
በግብጽ ታንታ ከተማ በሽብርተኞች ቦንብ ጥቃት የደረሰበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ

Security personnel bag a cross as evidence, Church bombing in Tanta, Egypt
በማስረጃነት የተያዘና በቦንብ ጥቃቱ የተጎዳ መስቀል፣ በግብጽ ታንታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ

Women try to reach loved ones after the attack in Alexandria.
ከአሌክሳንድሪያው ጥቃት በኋላ ቤተሰቦችዋን በስልክ ለማግኘት በመጣር ላይ የምትገኝ ሴት

አዲስ ቪዲዮ

Excavators move earth as rescuers work at the site of the landslide at the landfill.
ኤክስካቫተሮች የተደረመሰውን በማንሳት ላይ ሳሉ (ፎቶ፣ ZACHARIAS ABUBEKER/AFP/Getty Images)
...

በቆሼው አደጋ መትረፍ የ…

Discussion on the role of the diaspora
የዲያስፖራው ተሳትፎ ምን ይሁን? በቀጥታስ ሆነ በተዘዋዋሪ መሳተፍ አለበት
...

በኢሕአዴግና በተፎካካሪ …

Dr. Berhanu Mengistu on Forum 65
ዶ/ር ብርሃኑ መንግሥቱ ከፎረም ፷፭ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ
...

ዶ/ር ብርሃኑ መንግሥቱ ከፎረም ፷፭ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!