Assefa Chabo
አቶ አሰፋ ጫቦ

ኢዛ (ሰኞ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. April 24, 2017)፦ በአንደበተ ርዕቱነታቸውና በብዕራቸው በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት አቶ አሰፋ ጫቦ እሁድ ሚያዝያ ፲፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. (April 23, 2017) በሰባ ሦስት ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የሕግ ባለሙያ የነበሩትና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከሚጠቀሱት ግንባር ቀደም የፖለቲካ ሰዎች ውስጥ አንዱ የሆኑት አቶ አሰፋ ጫቦ፣ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በዩናይትድ ስቴትስ፣ ዳላስ ቴክሳስ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ሕክምና ሲደረገላቸው የቆየ ቢሆንም፣ ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም።

አቶ አሰፋ ጫቦ ከአባታቸው ከአቶ ጫቦ ሣዴ ሃማ ያሬ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ማቱኬ አጀን፣ ጋሞ ውስጥ በምትገኘው ጨንቻ ከተማ ነበር የተወለዱት። አቶ አሰፋ የአራት ልጆች አባት እና የዘጠኝ ልጆች አያት ነበሩ።

የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ዝግጅት ክፍል ለአቶ አሰፋ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች፣ አድናቂዎች እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!