የኢሬቻው እልቂት
የኢሬቻው እልቂት፣ መስከረም ፳፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. (ፎቶ፣ Reuters)

ኢዛ (ዓርብ ግንቦት ፲፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. May 26, 2017)፦ የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ በኢሬቻ በዓል ላይ ለሃምሳ አምስት ሰዎች መሞት ምክንያት የኾነውን ኹከት እና ብጥብጥ አስነስተዋል ባላቸው የመጀመሪያዎቹ ሁለት ግለሰቦች ላይ ክስ እንደመሰረተባቸው ተዘገበ።

ክስ የተመሰረተባቸው አንደኛው ተከሳሽ አቶ ቱፋ መልካ ”የአገር ሽማግሌዎች በኢሬቻ በዓሉ ላይ ንግግር ሲያደርጉ ማይክ በመቀማት ኹከት እና ብጥብጥ አስነስተዋል” በሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ተከሳሽ አቶ ከድር በዳሶ ደግሞ ”በበዓሉ ላይ ከመድረክ ጀርባ በመሆን በስልክ አመጹን ሲያስተባብር ነበር” በሚል መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

አቃቢ ሕግ ክስ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ባቀረበው ክስ ላይ፤ ተከሳሾቹ በኢሬቻ በዓል በተፈጠረው ግርግር ለሞቱት ሃምሳ አምስት ሰዎች መሞት ተጠያቂ መኾናቸውን ዘርዝሯል።

በችሎቱ የተገኙት ተከሳሾች የተመሰረተባቸው ክስ የተነበበላቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን መቃወሚያ ለመስማት ለፊታችን ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል።

በዓመቱ መጀመሪያ ላይ መስከረም ፳፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. በቢሾፍቱ (ደበረዘይት) በተከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ የሞቱ ወገኖች በመቶዎች እንደሚቆጠሩ ገለልተኛ የሆኑ ወገኖች ቢናገሩም፤ መንግሥት ግን ቁጥሩ ፶፭ ብቻ ነው ማለቱ ይታወቃል። 

አዲስ ቪዲዮ

አቶ እስራኤል ገደቡና አቶ ግርማ ካሳ
አቶ እስራኤል ገደቡና አቶ ግርማ ካሳ የፎረም 65 እንግዶች
...

መሪው ማን ነው? ኢሕአዴግ ወይስ ሕወሓት?

Excavators move earth as rescuers work at the site of the landslide at the landfill.
ኤክስካቫተሮች የተደረመሰውን በማንሳት ላይ ሳሉ (ፎቶ፣ ZACHARIAS ABUBEKER/AFP/Getty Images)
...

በቆሼው አደጋ መትረፍ የ…

Discussion on the role of the diaspora
የዲያስፖራው ተሳትፎ ምን ይሁን? በቀጥታስ ሆነ በተዘዋዋሪ መሳተፍ አለበት
...

በኢሕአዴግና በተፎካካሪ …

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!