ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ የአልሸባብና የአይኤስ አሸባሪዎች ተያዙ
ኢዛ (እሁድ መስከረም ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. September 22, 2019):- በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ የአልሸባብና የአይ.ኤስ የሽብር አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና አደጋውን ማክሽፍ መቻሉን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።
ትናንት ምሽት ላይ ከተሰጠው መግለጫ መገንዘብ እንደተቻለው፤ በኢትዮጵያ ላይ የሽብር ጥቃት ሊያደርሱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ከአሥራ ሁለት ያላነሱ አሸባሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ነው።
ከፍተኛ ሕዝብ በሚበዛባቸው፣ ሆቴሎችና በተለያዩ በዓላት ላይ ጥቃት ለማድረስ በሁለት ቡድን ተከፋፍሎ ሲንቀሳቅሱ የነበሩ መሆኑን አሳውቋል። ከፍተኛ የሽብር አደጋ ከመድረሱ በፊት በክትትል የሽብር ጥቃቱን መቆጣጠረ የተቻለ ጭምር መሆኑን የገለፀው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልገሎት መግለጫ ያስረዳል።
በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን አሸባሪዎች የሚከተሉት ናቸው።
1. ዒድ መሃድ ዓሊ
2. በሽር ዑስማን አብዲ
3. ዑስማን ዓሊ ሁሴን
4. ፋኡድ አብሽር ዩሱፍ
5. አደን ማሕሙድ መሐመድ
6. ይሳቅ ዓሊ አደን
7. መሐመድ ኢማን ዩሱፍ
8. ሬድዋን መሐመድ ሁሴን
9. መሐመድ ጉሃድ ቡዱል
10. ሰይድ ዑመር ሽበሺ
11. ሙሐመድ አብዱላሂ ዱለት
12. አብድክ መሐመድ ሁሴን
(ኢዛ)