የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ባሉበት አገር አካውንት መክፈት ያስችላል

ኢዛ (ቅዳሜ መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 5, 2019):- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትውልደ ኢትዮጵያውያን (ዲያስፖራዎች) ብቻ የሚገለገሉበትን ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ለገሃር አካባቢ ከፈተ።

ቅርንጫፉ ዓርብ መስከረም 23 ቀን 2012 ዓ.ም. በይፋ የተከፈት ሲሆን፣ ከውጭ የሚመለሱ ዲያስፖራዎችም ሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ዲያስፖራዎች የሚጠቀሙበት ይሆናል ተብሏል።

የዚህ ቅርንጫፍ የተለየ አገልግሎት በየትኛውም የዓለም ክፍል ያሉ ዲያስፖራዎች ባሉበት አገር በሚገኝ ኤምባሲ ወይም ቆንጽላ ጽሕፈት ቤት በመቅረብ አካውንት ከፍተው ገንዘብ ለማንቀሳቀስ የሚያስችላቸውን እድል የሚሠጥ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ