TPLF and ODP

ሕወሓትና ኦዴፓ

ለሕወሓትና ለአብዮታዊ ዴሞክራሲያውያን የተሰጠ መግለጫ

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 18, 2019):- የኢሕአዴግ አወቃቀር ሲመራበት የነበረው አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሕዝብን ውሳኔ ሰጪነት የሚገድብ ስለኾነ ለደረስንበት የትግል መድረክ የሚመጥን አለመኾኑን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አስታወቀ።

ኦዴፓ በዚህ መግለጫው፤ ኢሕአዴግን በማደስ፤ በዘመነ አሠራርና ሥርዓት የሚመራ ፓርቲ በመፍጠር፤ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፅንሰ ሐሳብን በመደመር ፅንሰ ሐሳብ ለመተካት ውይይት እየተደረገ መሆኑ አስታውሷል።

ባለፉት ጊዜያት የነበረውን የዝርፊያ መዋቅር፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ፀረ-ዴሞክራሲ ድርጊቶች ሲፈጸሙበት የነበረውን የዝርፊያ መዋቅር በማፍረስ፤ ዴሞክራሲያዊና ነፃነት የሰፈነባትና የበለፀገች አገር ለመገንባት በኢሕአዴግ አወቃቀር ላይ ሪፎርም ማድረግ ወሳኝ መኾኑንም ኦዴፓ እንደሚያምን በዚሁ መግለጫ ጠቅሷል።

ኦዴፓ ትክክለኛና እውነተኛ የብዝሃነት ፌዴራሊዝም ሥርዓት በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ የአገራችንን ሕዝቦች እኩልነትና ነፃነት ለማረጋገጥ የሚያወላዳ አቋም እንዳለውም በመግለጫው አትቷል።

ሙሉ መግለጫው የሚከተለውን ይመስላል፤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! ኢዛ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ