PM Dr Abiy Ahmed's book, Medemer

“መደመር” የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ አዲስ መጽሐፍ

“መደመር” መጽሐፍ የኢሕአዴግን የወደፊት አቅጣጫ ይጠቁማል

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 19, 2019):- ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ “መደመር” የሚል ርዕስ የተፃፈውና ቀጣዩን የአገሪቱን አቅጣጫ የሚያመላክቱ ትንተናዎችን ያካተተው ነው የተባለው መጽሐፍ ዛሬ በይፋ ተመርቆ ለገበያ ይቀርባል።

ሰሞኑን ሠፊ መነጋገሪያ ኾኖ የሰነበተው የጠቅላይ ሚንስትሩ መጽሐፍ በአንድ ሚሊዮን ኮፒ የታተም ሲሆን፣ የመሸጫ ዋጋውም 300 ብር እንደኾነ ታውቋል።

ስለመጽሐፉ ይዘት ከወጡ መረጃዎች መገንዘብ የተቻለው፤ የመደመር ፍልስፍናን መንደርደሪያ በማድረግ በፖለቲካ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ትንተና የሚሠጥ፤ የኢሕአዴግን የወደፊት አቅጣጫ የሚጠቁምም ነው። በመጽሐፉ ለውጡ በምን መንገድ እንደሚቃኝ፣ ሊለውጡ የሚችሉ አካሔዶችን ይፋ የሚያደርግ ነው።

በመጽሐፉ የምረቃ ፕሮግራም ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ተሠጥቶ የነበረው መግለጫ እንደሚያትተው ዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. አዲስ አበባን ጨምሮ በ20 የአገሪቱ ከተሞች ልዩ ልዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በሚታደሙበት ይመረቃል።

ከኢትዮጵያ ውጭም በአሜሪካ በዋሽንግተን፣ በሎስ አንጀለስና በሚኒሶታ የሚመረቅ ይኾናል ተብሏል። በአፍሪካም በኬንያ የመጽሐፉ የምረቃ ፕሮግራም የሚካሔ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የሚካሔደው የመጽሐፍ ምረቃ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሔዳል ተብሎ ይጠበቃል።

መደመር መጽሐፍ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች የታተም ሲሆን፣ ከዚህ መጽሐፍ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በተለያዩ የአገሪቷ የገጠር ክፍሎች ለሚሠሩ ትምህርት ቤቶ ማሠሪያ ይውላል ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ