በጋራ ለመሥራት ተስማሙት አስሩ ፓርቲዎች

በጋራ ለመሥራት ተስማሙት አስሩ ፓርቲዎች

አብዛኞቹ በነፃ አውጭነት ትግል ሲያደርጉ የነበሩ ፓርቲዎች ናቸው

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. December 6, 2019)፦ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) የተካተቱበት 10 የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገር አቀፍ ደረጃ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ዛሬ ተፈራረሙ።

ዛሬ ኅዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም. የተፈረሙ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በጋራ ለመሥራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት በማድረግ እንዲሠሩ ያስችላቸዋል።

በአብዛኛው በነፃ አውጭነት ትግል ሲያደርጉ የነበሩ ፓርቲዎችን በያዘው በዚህ ስብስብ ውስጥ፤ ከኦነግና ከኦብነግ ሌላ ስምምነቱን የፈረሙት ቀሪዎቹ ስምንት ፓርቲዎች፤

የአፋር ሕዝቦች ነፃነት ፓርቲ፣
የሲዳማ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣
የቤንሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣
የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣
የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣
የአገው አገር አቀፍ ሸንጎ፣
የሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲና
የካፋ አረንጓዴ ፓርቲ ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ