ሕወሓት ብልጽግናን በይፋ ተለያየ

ሕወሓት ብልጽግናን በይፋ ተለያየ

ከሌሎች ኃይሎች ጋር እሠራለሁ አለ

ኢዛ (እሁድ ታኅሣሥ ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 5, 2020)፦ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የሚያስማሙም ነገሮች ስለሌሉ ብልጽግና ፓርቲን እንደማይቀላቀል በይፋ አስታወቀ።

ሕወሓት ይህንን ውሳኔውን ያሳለፈው ለሁለት ቀናት ያካሔደውን አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባዔ ካጠናቀቀ በኋላ ዛሬ ታኅሣሥ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ነው።

ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የዓላማና የመስመር ልዩነት ስላለው፤ ውሕደቱ ውስጥ እንደማይገባ ያስታወቀው የሕወሓት መግለጫ፤ ከዚህ በኋላ ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር የሚኖረኝ ግንኙነት ሕገመንግሥቱንና ሕግን መሠረት ያደረገ ስለመኾኑ መግለጹን በመግለጫው አመልክቷል።

ከዚህ በኋላም ከሌሎች ኃይሎች ጋር ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ለመመስረት ስለመወሰኑም አስታውቋል። መግለጫው ከዚህ ቀደም በብልጽግና ፓርቲ ዙሪያ ሕወሓት ይዞ ከቆየው አቋም አዲስ ነገር የሌለው እንደኾነ ለመገንዘብ ተችሏል።

ኢሕአዴግን የመሠረቱት አራቱ ፓርቲዎች በመኾናቸው፤ የአራቱ ድርጅቶችን የጋራ ሀብት ሕግና ሥርዓት በተከትለ መንገድ ሕወሓት ድርሻውን እንደሚያስመልስም በመግለጫው አስታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ