አዲስ አበባ "በአዲሱ ማስተር ፕላን ወደ ጎን መለጠጧን አቁማ ወደ ላይ ከፍ ማለት ትጀምራለች" አዲሱ ኮሚሽን

Addis Ababa

ኢዛ (ረቡዕ ታህሳስ ፳፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 04, 2017)፦ በ1994 ዓ.ም ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ዘጠነኛው ማስተር ፕላን በ2006 ዓ.ም. የመጠቀሚያ ጊዜው አብቅቷል። አሥረኛው ማስተር ፕላን ከኦሮሚያ ልዩ ዞን ጋር አቀናጅቶ ለማካሄድ በርካታ ሥራዎች የተሠሩ ቢሆንም፣ ከኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ በመቅረቡ እንዲቀር ተደርጓል። በዚህ ምክንያት ባለፉት አራት ዓመታት አዲስ አበባ ይፋ ማስተር ፕላን ሳይኖራት ቆይቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ የሕብረቱን ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ሥራ በይፋ ጀመረች

United Nations Security Council

ኢትዮጵያ ዛሬ (ሰኞ ታህሳስ ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 02, 2017)፦ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ በጊዜያዊ አባልነት የተመረጠችው ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2017 አዲስ ዓመት መግቢያ ላይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ካውንስል አባልነቷን በይፋ መጀመሯ ተዘግቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰ

Samara campus viewኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ታህሳስ ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 30, 2016)፦ በአፋር ክልል የሚገኘው ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ማታ ከምሽቱ አንድ ስዓት ተኩል አካባቢ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ እንደደረሰበት ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ የደረሰው ዘገባ አስረዳ። በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ ባይኖርም፤ በቃጠሎው የወደመው ንብረት ግምቱ ምን ያህል እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ሩዙ የፕላስቲክ ሳይሆን የተመረዘ ነው” ናይጄሪያ

Plastic rice in Nigeria

ኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ታህሳስ ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 30, 2016)፦ በናይጄሪያ የፕላስቲክ ሩዝ ተሰራጭቷል ተብሎ የወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ፤ ”ሩዙ የፕላስቲክ ሳይሆን የተመረዘ ነው” ሲል የናይጄሪያ ብሔራዊ የምግብና የመድኃኒት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ማስተባበያ ሰጠ። ሩዙ ከቻይና ወደ ናይጄሪያ የገባ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ር መረራ ጉዲና በሽብር ወንጀል ሊከሰሱ ነው

Prof. Merera Gudina

ኢትዮጵያ ዛሬ (ኀሙስ ታህሳስ ፳ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 29, 2016)፦ ባለፈው ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. በአውሮፓ ሕብረት ስብሰባ ላይ ተገኝተው አዲስ አበባ ሲገቡ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ፕ/ር መረራ ጉዲና በሽብር ወንጀል ሊከሰሱ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እጅግ ታሟል

Temesghen Desalegn

ኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ታህሳስ ፲፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 27, 2016)፦ ሰሞኑን ያለበት ባለመታወቁና እስር ቤቶቹ ሁሉ ”አናውቅም” በማለታቸው ቤተሰቦቹን ጨምሮ ጉዳዩ ብዙዎችን አስጨንቆ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ በመጨረሻ ዝዋይ እስር ቤት ቢገኝም፤ በአሁኑ ሰዓት እጅግ ታምሞ ሆስፒታል መግባቱ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር የፍትሐት ሥነሥርዓት ነገ ይፈጸማል

Miruts Yifter

ኢትዮጵያ ዛሬ (ሰኞ ታህሳስ ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 26, 2016)፦ ባለፈው ኅሙስ ታህሳስ ፲፬ ቀን ፳፻፱ (Dec. 22, 2016) በሰባ ሁለት ዓመቱ ሕይወቱ ያለፈችው፣ የጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር የጸሎተ ፍትሐቱ ሥነሥርዓት ነገ ማክሰኞ ታህሳስ ፲፰ ቀን (Dec. 27) ጠዋት አምስት ሰዓት ላይ ቶሮንቶ ካናዳ በሚገኘው ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የደረሳት ዘገባ አስረዳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ፍለጋ ቀጥሏል

Journalist Temesgen Desalegne

ኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ታህሳስ 5 ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 14, 2016)፦ ላለፉት ስምንት ተከታታይ ቀናት ቤተሰቦቹ በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ወህኒ ቤቶች ሁሉ ዞረው ሲፈልጉ ሰንብተዋል። አቤቱታቸውንም ለሚመለከተው ክፍል አሰምተዋል። ይሁን እንጂ ተመስገንን አየሁ የሚል አንድም የወህኒ ቤት አስተዳዳሪ አልተገኘም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሰባት ኢትዮጵያውያን አስከሬኖች በጆንያ ተጠቅልለው በታንዛኒያ ወንዝ ውስጥ ተገኙ

7 Ethiopians killed in tanzaniaኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ታህሳስ ፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 13, 2016)፦ የሰባት ኢትዮጵያውያን አስከሬን በታንዛኒያ ወንዝ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱን የአገሪቱ መንሥግት አስታወቀ። ኢትዮጵያውያኑ ወንዝ ውስጥ ሆን ተብለው የተጨመሩ መሆኑንም ፖሊስ ተናግሯል። አስከሬኖቹ በጆኒያ ከአሸዋ ጋር ተደርገው ነው ወደ ወንዝ የተወረወሩት ሲል ፖሊስ መግለጡን የኬንያ ቴሌቭዥኖች የዘገቡ ሲሆን፣ ሟቾቹ በሙሉ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች ውስጥ 16 ያህል ጋዜጠኞች እንደሚገኙ ሲፒጄ አስታወቀ

CPJ imprisoned 2016

ኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ታህሳስ ፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 13, 2016)፦ በየዓመቱ በመላው ዓለም በሥራቸው ሳቢያ ብቻ ወደ ወህኒ ቤቶች የተወረወሩ ጋዜጠኞችን ቁጥርና ስም ዝርዝር ይፋ የሚያወጣው ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪው ድርጅት ሲፒጄ፤ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች 16 ጋዜጠኞች መታጎራቸውን ይፋ አድርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!