የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ”የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” አዲስ መጽሐፍ በሦስት የአሜሪካ ከተሞች ተመረቀ

Prof. Fikre Tolossaአብርሃም ቀጄላ

የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ”የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” አዲስ መጽሐፍ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ሦስት ከተሞች ተመረቀ። በሦስት ተከታታይ ቀናት ከዲሴምበር ፫ ቀን ጀምሮ በቨርጂኒያ፣ በዋሽንግተን ዲሲ እና በሜሪላንድ በሚገኙ የኢትዮጵያውያን ሬስቶራንቶች ነው ምርቃቱ የተካሄደው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጋምቢያው ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜይ የምርጫውን ውጤት አልቀበልም አሉ

Adama Barrow and Yahya Jammeh

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ታህሳስ ፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 10, 2016)፦ ባለፈው ሣምንት በምርጫ መሸነፋቸውን በፀጋ መቀበላቸውን አሳውቀው የነበሩትና ጋምቢያን ላለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት የመሩት የጋምቢያው ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜይ፤ በዛሬው ዕለት የምርጫውን ውጤት አልቀበልም አሉ። ድጋሚ ምርጫ መካሄድ አለበት ማለታቸው ተደመጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ውድድር መድረክ ሊመለስ ነው

Feyisa Lelisa

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ታህሳስ ፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 10, 2016)፦ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ባለፈው ክረምት በሪዮ ዲጄኔሮ ኦሎምፒክ ማራቶን ውድድር ላይ የብር ሜዳሊያ ከመቀዳጀቱም በላይ በአገሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም እጆቹን አጣምሮ በዓለም አደባባይ ላይ ካሳየ ወዲ የመጀመሪያው የሆነውን ውድድር ሊያደርግ በዝግጅት ላይ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን አስሬአለሁ የሚል ወህኒ ቤት ጠፋ

Temesgen Desalegne

ኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ኅዳር ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 9, 2016)፦ “ተመስገን ያለበትን ቦታ ለማወቅ ለ3ኛ ቀን ፍለጋ አንዳችን ወደ ዝዋይ፣ አንዳችን ወደ ሸዋ ሮቢት፣ አንዳችን ወደ ማዕከላዊ እስር ቤቶች እየሄደን ሲሆን፤ እናታችን ደግሞ ወደ ቤተክርስቲያን እየሄደች ነው።” ሲል ዛሬ ጠዋት የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ በፌስቡክ ገጹ ቤተሰቡ ያለበትን ኹናቴ እና ያደረበትን ስጋት ገለጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሰበር ዜና | የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ተስፋዬ ዲንቃ አረፉ

Former PM Tesfaye Dinkaኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ኅዳር ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 9, 2016)፦ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ብሎም ከ1981 እስከ 1983 ዓ.ም. በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ኢትዮጵያን ያገለገሉት አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ያዴሳ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. በ፸፯ ዓመታቸው አረፉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ ሔዶ ሊታከም ነው

Habtamu with his daughter

(ቢቢኤን) ባለፈው ዓርብ ኅዳር 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ከተከሰሰበት የሽብር ክስ በነጻ የተሰናበተው አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ ሔዶ እንደሚታከም ገለጸ። የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው አቶ ሀብታሙ፣ ሆሞሮይድ በተባለ በሽታ በጽኑ ሲታመም እንደሰነበተ ይታወቃል። ውጭ ወጥቶ ለመታከም በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤት አመልክቶ በተለያዩ ሰበቦች ማመልከቻው ውድቅ ሲደረግበት የቆየው አቶ ሀብታሙ፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነጻ መባሉን ተከትሎ ውጭ ሔዶ ለመታከም ማቀዱን አስታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንኮበር ከተማ በፎቶ ለታሪክ ማስታወሻነት ተቀመጠች

Photographer Michael Tsegaye

ኢትዮጵያ ዛሬ (ኀሙስ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 8, 2016)፦ የኢትዮጵያዊው ፎቶግራፈር ሚካኤል ፀጋዬ፤ አጤ ምኒልክ በዋና ከተማነት የቆረቆርዋትን ”አንኮበር”ን ለወደፊት ለታሪክ ማስታወሻ በፎቶግራፍ ለማስቀመጥ በማሰብ ከአስር ዓመት በፊት ያነሳቸውን ፎቶግራፎች በኤግዚቢሽን አቀረበ። ኢግዚቢሽኑ በአዲስ ፋይን አርት ጋለሪ ከኖቨምበር ፲፱ እስከ ጃንዋሪ ፳፩ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ፕ/ር መረራን ያሰርኩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ስለጣሱ ነው” ኮማንድ ፖስቱ

Prof. Merera Gudina

ኢትዮጵያ ዛሬ (እሁድ ኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 4, 2016)፦ ፕ/ር መረራ ጉዲና ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በቤልጅየም ብራስልስ ”ተገናኝተው በመውያየታቸውና መግለጫ በመስጠታቸው” ነው ያሰርኳቸው ሲል ኮማንድ ፖስቱ ገለጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!