አትሌት አልማዝ አያና የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት ተብላ ተመረጠች

Almaz Ayana and Husain Bolt

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 3, 2016)፦ ዓለማቀፉ የአትሌቲክስ ማኅበር ፌደሬሽን ኢትዮጵያዊቷን የ10 ሺህ ሜትር ሪኮርድ ባለቤት አልማዝ አያናን የ2016 የዓለም ምርጥ አትሌት በማለት ትናንት ማምሻውን የሸለማት ሲሆን፣ ከወንዶ ትሌቶች ደግሞ ጃማይካዊው የአጭር ርቀት ሯጭ ዩሴን ቦልት ተሸላሚ ሆኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ር መረራ ጉዲና አዲስ አበባ ሲገቡ ታሰሩ

የታሰሩት በአውሮፓ ሕብረት ባደረጉት ንግግር እና ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በመታየታቸው ይሆናል ተብሎ ይገመታል

Prof. Merera Gudina

ኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 30, 2016)፦ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ፕ/ር መረራ ጉዲና መታሰራቸው ተጠቆመ። ፕ/ር መረራ የታሰሩበት ምክንያት ለጊዜው በትክክል ባይታወቅም፤ በአውሮፓ ሕብረት ተገኝተው ባደረጉት ንግግርና ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በመታየታቸው ሊሆን ይችላል ተብሎ ይጠረጠራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሹም ሽሩ ሥልጣናቸውን ያጡ የኢህአዴግ ጎምቱ ባለሥልጣናት የሙሉ አምባሳደርነት ሹመት ተሰጣቸው

ከ፲፯ (17) ቀን በኋላ አዲስ ሥልጣን ተሰጣቸው

Ato Tsegaye Berhe, Ato Redwan Hussen, W/o Zenebu Tadesse, and Ato Tolossa Shagie

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፲ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 19, 2016)፦ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ባለፈው ሹም ሽር ሥልጣናቸውን ላጡ ስምንት የኢህአዴግ የቀድሞ ባለሥልጣናት የሙሉ አምባሳደርነት ሹመት ሰጡ። እነኝህ የኢህአዴግ ጎምቱ ባለሥልጣናት የሙሉ አምባሳደርነት ሹመት እንደተሰጣቸው የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ቢገልጽም፤ በየትኞቹ አገሮች ላይ ሹመት እንደተሰጣቸው አልገለጸም፤ ተሰናባቾቹ አምባሳደሮችም አልታወቁም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዮናታን ተስፋዬ ቀንና ሌሊት በሰንሰለት እንደሚታሰር ተዘገበ

Ato Yonatan Tesfaye(ኢሰመፕ) ፌስቡክ ላይ በጻፋቸው ጹሁፎች ምክንያት የሽብር ክስ ቀርቦበት ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ የሚገኘውና በእስር ቂሊንጦ ያለው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በሚገኝበት እስር ቤት ውስጥ ከአርብ ኅዳር 2/2009 ዓ.ም. ጀምሮ ቀንና ሌሊት በሰንሰለት ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የነአቶ ሀብታሙ አያሌው ጉዳይ በድጋሚ ለኅዳር ፳፯ ተቀጠረ

Habtamu, Daniel, Yeshiwas and Abrahaኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ኅዳር ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 16, 2016)፦ በአራት ታዋቂ የተቃዋሚ ፓርቲ ሰዎች፤ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ አቶ አብርሃ ደስታ እና የፓርቲ አባል ባልሆኑት አቶ አብርሃም ሰለሞን የተከሰሱበትን ጉዳይ ለማየት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ትናንት ቢሰየምም፤ የፌዴራሉ አቃቤ ሕግ በችሎቱ ባለመገኘቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በእነበቀለ ገርባ ላይ የፌዴራል አቃቤ ሕግ በዝግ ችሎት ይታይልኝ ጥያቄን ፍ/ቤቱ ውድቅ አደረገው

Ene Bekele Gerbaኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ኅዳር ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 16, 2016)፦ ዛሬ በዋለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፲፰ኛ ወንጀል ችሎት፣ የፌዴራሉ አቃቤ ሕግ ትናንት የእነ አቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ ላይ ምስክርነት የመስጠቱ ሂደት በዝግ ችሎት እንዲታይለት ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገበት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቢቢሲ በሦስት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ስርጭት ሊጀምር ነው

BBC

ኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ኅዳር ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 16, 2016)፦ የብሪቲሽ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ቢቢሲ)፣ በሚቀጥለው የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት (2017) የኢትዮጵያን ሦስት ቋንቋዎች ጨምሮ በአስራ አንድ የዓለም ቋንቋዎች አዲስ ስርጭት ሊጀምር መሆኑ ታወቀ። ኢትዮጵያውያን ቋንቋዎቹ አማርኛ፣ ኦሮምኛ እና ትግሪኛ መሆናቸው ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ የአንድ ዓመት እስራት ተፈረደበት

Journalist Getachew Workuኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ኅዳር ፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 15, 2016)፦ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ፮ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት፤ በኢትዮ ምኅዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ ላይ የአንድ ዓመት እስራት እንደበየነበት ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ ጠቆመ። ጋዜጠኛ ጌታቸው ካለፈው ጥቅምት ፳፬ ቀን ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!