በለንደን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተካሄደ

ታምሩ ገዳ (ለንደን)

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ገዳማት አድባራት እና የአብነት ት/ቤቶችን (የቆሎ ት/ቤቶችን) ከውድመት ለመታደግ የታቀደ የገንዘብ ማስባስብ ፕሮግራም በእንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ውስጥ ተካሄደ። የፕሮግራሙ ዋንኛ ተዋንያኖች ሆኑት የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ከዚህ ቀደም ያበረከቱት እና አሁንም እያበረከቱት ያልው አስተዋጽዖ ለበርካታ የኦርቶዶክስ ተዋኅዶ እምነት ትከታዮች ከፍተኛ አርኣያ መሆኑ ተገለጸ።

 

ባለፈው ህዳር 12 ቀን 2003 ዓ.ም. (ኖቭምበር 22 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.) በለንደን ከተማ እና አካባቢዋ በሚኖሩ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በስንብት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የማህበረ ቅዱሳን አባላት እና በመዴናይቱ ውስጥ ታዋቂ ከሆኑት የኢትዮጵያ ሪስቶራንቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ስንቄ ሬስቶራንት እና ቅ/ገብርኤል በተባሉ ሁለት ሬስቶራንት ድጋፍ (ስፖንሰርነት) የተዘጋጅው ይሄ የገንዘብ ማስባሰብ ፕሮግራም ላይ ለመገኘት ከምድር አሜሪካ የመጡት በኦሃዮ ኮሎምቤያ የቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክን አስተዳዳሪ ይሁኑት ቀሲስ ያሬድ ገ/መ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ገዳማት እድባራት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ጌዜያት በተከሰቱ ተፈጥሮአዊ እና ስው ሰራሽ ምክንያቶች የተነሳ ለውድመት ለዝርፊያ እና ለመበታተን አደጋዎች ተጋልጥው እንደሚገኙ አውስተው በቅዱስ መጽሃፍ በመዝሙረ ዳዊት(67: 1) ላይ "ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዜእብሄር ትዘረጋለች" ተብሎ በተጠቀሰው መስርት ኢትዮጵያዊያን ለፈጣሪ ቅርብ በመሆናቸው የተነሳ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ ችግሮች በእግዜአብሄር ቸርነት ቤቀዘቅዙም እነዚህ በገንዘብ ሌተመኑ የማይችሉ እና መተኬያ የሌላችው የሀገር ሀብቶች የአምልኮት እና የዕውቀት መሰረቶች ከፍተኛ የሆኑ ችግሮች እይተፈራረቁባቸው እንደሜገኙ አስታውቀዋል።

 

ከኢኮኖሜያዊ ችግሮች አኳያ በቀን አንዴ እንኳን መብላት የተሳናቸው መነኮሳት፣ ማምህራን እና የአብነት ተማሪዎች እየተበተኑ ይገኛሉ። ከሃምሳ አመታት በላይ ያግልግሉ ምምህራን ቢታከሙት በቀላሉ ሊድኑት በሚችሉት ደዌ ተይዘው በቤት ውስጥ ከአልጋ ላይ የዋሉበት ብዙ አጋጣሚዎች አሉ፣ የመንፈስ ልጆቻቸውም ቢሆኑ መምህራኖቻቸውን ለማሳከም አቅም ቤያጥሯቸውም የመንፈስ አባቶቻቸውን ጥለዋቸው ላለምኮብለል በመወሰን እዝያው ባሉብት እብርዋቸው መከራን የተጋፈጡባቸው በርካታ አጋጣሜዎች አሉ" ሲሉ ለተሰባሰቡት ምእመናን ገለጸዋል።

 

እነዚህ በአገር ውስጥ ሆነ በአለማቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ስም ያስጥሩ ታዋቂ የጥበብ ስዎች ማፍለቂያ የሆኑት መምህራን እና የአብነት ት/ቤቶች መታድግ የሁሉም የእምነቱ ተከታዮች ሀይማኖታዊ እና የዜግነት ግዴታዎች መሆኑን የጠቀሱት ቀሲስ ያሬድ በተጨማሪ ከዚህ ጸሀፊ ጋር ባደረጉት አጭር ቃለምልልስ በለንደን የሜኖሩ ምእመናን እነዜህ አስታዋሽ እና ትኩረት ተንፍጓቸው ይቆዩት ግዳማት እድባራት እና የአብነት ት/ቤቶች እገዛ እንዴያገኙ ጥረት ማድረጋችው በጥሩ አርያንት ሊጠቀስ ይገባል ብልዋል።

 

የማህበረ ቅዱሳን መስርታዊ እና ዘለቄታ እገዛ ያሰፈልጋቸዋል ብሎ ስፊ ጥናት በማድረግ እና ጥናቱንም በሚመለከታቸው ባለሙያዎች በማስገምገም እና ፕሮጀክቶቹንም ከአካባቢ እና ከተጠቃሜው ማህብረስብ ጋር ናባራዊ ሁኔታዋች ጋር በሚስማሙ መልኩ እንዲከናወኑ በማድረግ እነዚህ በችግር ላይ የሚገኙ የቤ/ክርስቲያኒቱ ውድ ሃብቶች ተገቢውን ትኩረት አና እርዳታ እንዲያገኙ ከበጎ እድራጌ ምእመናን ጋር በማገናኘት ላይ መሆኑን ያስረዱት ቄሲስ ያሬድ በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ የሚውለው ገንዝብ እና ማቴሪያል ግልጽነት እና ተጠያቂነት ባለው መልኩ የሚተገበር በመሆኑ በርካታ ምዕመናኖች የጥናቱን ውጤት እንደ እራሳችው ስራ እድርገው በምውስድ በገንዝብ በእውቀት በጉልብት ወዘተ እያገዙ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

 

በማያያዝም የምዕምናን እና የአስተባባሪዎቹ ማህበረ ቅዱሳን ጥምረት መፍጠር በስው ሰራሽ እና በተፈጥሮ ችግሮች እይተፈቱ የሚገኙትን ገዳማትን ነገ ቅኔ ማህሌቱን የሚመሩት ነገ ሊቀጳጳሳት ሆነው የሴኖዶስ አባላት ሆነው ቤ/ክርስቲያንን የሚመሩ አባቶች የሚወጡባቸው የአብነት ት/ቤቶችን ከመጥፋት መታደግ ይገባናል በማለት ተማጽኖአቸውን አሰምተዋል።

 

በስተመጨርሻም "እኛ በከተማዎች ውስጥ የምንኖር የተዋህዶ ልጆች እይበላን እና አይጠጣን ስለእኛ ቀን እና ለሌት ሲጸልዩ የሚኖሩት ቅዱሳን አባቶች በእንደዚህ ፈተና ውስጥ ወድቀው ማየት የለብንም መሃሉ ሰላም የሚሆነው ዳሩ በጸሎት ሲታጠር ነው አንድ ገዳም ተፈታ ማለት የእኛም በገዳሙ ውስጥ ያለን ህይወት በአጭሩ ተፈታ ወይም ከባድ መከራ ላይ ወደቅን ማለት ነው። ስለዚህ የዚህች ቤ/ክርስቲያን ችግሯን ማየት የማይፈልጉ የቤተክርስቲያን ልጆች ጊዜ እና ቦታ ሳይወስናቸው ሌተባበሩ እንደሚገባቸው እና በማህበረ ቅዱሳን በኩል ይሁን ሌሎች ማህበራት በሚያዘጋጇቸው ተመሳሳይ የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራሞች ላይ በመሳተፍ ቤ/ክርስቲያኔቱ ያለባትን ችግር (የገዳማትን እናን የአድባራትን ሁኔታ) ተገንዝቦ ለመርዳት ጥረት ማድረግ ይገባል ብዮ አስባለሁ" ብልዋል።

 

London, Nov, 22, 2010

በመርሃ ግብሩ ላይ ከነበሩ ምዕመናን በከፊል

 

በለንደን ከተማ የቅዱስ ስላሴ ቤ/ክ አገልጋይ የሆኑት ዲያቆን ሚሊዮን አጀበ በዚሁ የገንዘብ እርዳታ ፕሮግራም ላይ የማህበረ ቅዱሳን ያካሄዷቸው ወይም እያካሄዷቸው የሚኙትን የልማት እንቅስቃሴዎችን እና የተገኙ ውጤቶችን በቻርት እና በምስል የተደገፉ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል ለእርዳታ ከታጩት ፕሮጀክቶች መካከል የአባ ጌዮርጌስ ዘ ጋሰጫ ገዳም (ደቡብ ወሎ ከለላ ወረዳ የዛሬ 600 አመት ገደማ ከአንድ ወጥ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሰራ ቤ/ክ ነው) እና በከፋ ሀ/ስብከት ቦንጋ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ኪያ ኬላ አቡነ ተ/ሃይማኖት ገዳም ተጠቃሽ ናቸው ። ገለጻውን ተከትሎ ምዕመናን በግል እና በቡድን ሆነው አቅማቸው እንደፈቀደው እርዳታ እንዲያደርጉ በቀረበው ግብዣ መሰረት ግምቱ ወደ አምስት ሺ ፓውንድ እና የአንገት ሐብል እና የእጅ ብራስሌት እርዳታ ተበርክቷል። ገዳማቱ እና አድባራቱ የተደቀነባቸው ወቅታዊ ችግሮችን ልባቸውን ከነካው ምዕመናን መካከል የለንደን ከተማ ነዋሩ የሆኑ አቶ ፍሰሃ የተባሉ በበኩላቸው በማህበረ ቅዱሳን ሃሳብ አቅራቢነት ከተመረጡት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱን በራሳቸው ወጬ ከፍዓሜ ለማድረስ በምዕመናን ፊት ቃል ገብተዋል።

 

(ከግራ ወደ ቀኝ) ቀሲስ ያሬድ ገመድኅን አቡነ እንጦንስ መለከ ገነት ቀሲስ ከፍያለው አስቻለው
(ከግራ ወደ ቀኝ) ቀሲስ ያሬድ ገመድኅን አቡነ እንጦንስ መለከ ገነት ቀሲስ ከፍያለው አስቻለው
በዚህ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ የተገኙት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰሜን ምእራብ አውሮፓ ጳጳስ የሁኑት ብጹ አቡነ እንጦስ በማህበረ ቅዱሳን እና በምእመናን አማካኝነት እየተደረጉ ያሉ ገዳማትን አድባራትን እና የአብነት ት/ቤቶችን የመታደግ ርብርቦሽ በጣም የሚመስገን እና ለሌሎችም ወገኖች ጥሩ አርያ ሊሆን የሚችል ተግባር እነደሆነ ተናግረዋል። ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተመሰገነ ነው የሀዋሪያት ስራ (20:35) መዕሃፍ ቅዱሳዊ ጠቅስን ዋቤ ያደረጉት ብዑነታቸው "እግዜአብሄር ሰጬ እኛ ተቀባይ ስንሆን ዛሬ ደግሞ እናንተ ሰጬ እግዜአብሄር በተራው ተቀባይ መሆኑን በመገንዘብ ያደረጋችሁትን አስተዋጾ ፈጣሪ ይቆጥርላችሁዋል" በማለት ምስጋና አቅርበዋል ። ንግግራቸውን በመቀጠል የማህበረ ቅዱሳን አባላት ሃይማኖታዊ ተጋድሎን በተመለከተ ሲያብራሩ " ከዚህ ቀደም እያንዳንዳችን ጳጳሳት ከደሞዛችን 15% በማዋጣት የተጎዱ ገዳማትን አድባራትን እና የአብንት ት/ቤቶችን ለማገዝ እንድናዋጣ ተደረገ። በአዲስ አበባ የሚገኙ አድባራት በአመት ክብረ በአላቸው ከሚሰበሰቡት የገንዘብ መዋጮ ፈሰስ እንዲያደርጉ ቢወሰንም ከችግሩ ስፋት የተነሳ የተጠበቅውን ያህል ውጤት አልተገኘም" ያሉት አቡነ አንጦስ "እግዜአብሄር ይመስገን እና እነዚህ የመንፍስ ልጆቻችን (ማህብረ ቅዱሳን) ቅዱስ ሴኖዶስ ያልደርስባቸውን አካባቢዎችን እና ችግሮቻቸውን በግንባር በመገኘት አኩሪ ስራ እይሰሩ ይገኛሉ ። እግዜአብሄር ማህብር ቅዱሳንን በማስነሳት ይህንን የመሰለ ትልቅ እና አኩሪ ስራ እንዲሰራ በማድረጉ ክብር ምስጋና ይገባዋል። የአብነት መምህራን ከሌሉ ቤ/ክ የለችም።

 

በገዳማት ያሉ አባቶች በቀን አንዴ እንኳን ዳቤ (ዳቦ) ስለሚያስፈልጋቸው ዛሬ የምታደርጉት ስጦታ(እርዳታ) ለሃይማኖታችሁ ለታሪካችሁ እና ቤ/ክርስቲያናችሁ መሆኑን በመረዳት ያደረጋችሁት እገዛ ያስምስግናችሃል" በማለት ለሁሉም ተሳታፊዎች ያላቸውን ታላቅ እድናቆት እና እክብሮት ገልጸዋል።

 

የገዳማት አድባራት እና የአብነት ት/ቤቶች ወቅታዊ ችግሮችን ለምዕመናን በማሳወቅ እና ግንዛቤ በማስጨበጥ በኩል በለንደን የቅ/ስላሴ ቤ/ክ ከወራት በፊት አዘጋጅቶት በነበረው አመታዊ የስብከተ ወንጌል ፕሮግራም ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገው የነበሩት አቶ በላቸው ጨከነ የተባሉ ምዕመን ከዚህ ጸሀፊ ጋር ባደረጉት ቃል ምልልስ አንደገለጹት "ምዕመናኑ የቤ/ክርስቲያኔቱ ችግሮችን እንደራሳቸው ችግር በመቁጥር ያደረጉት መዋጮ የሚያስመሰግናቸው ሲሆን ወደፊትም ቢሆን ተመሳሳይ የግንዛቤ እና የእርዳታ ማሰባሰብ ፕሮግራሞች ቢካሄዱ የበለጠ ውጤት እንደሚኖር ያመላክታል" ብለዋል።

 

በገንዘብ ማሰባስቡ ፕሮግራም ላይ የተገኘች ነገር ግን ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀች አንዲት ምዕምን በበኩሏ "የማህብረ ቅዱሳን አባላት እያድረጉት ያለውን መልካም ተግባር ከሀይማኖት አባቶች ዘንድ በእንደዚህ መልኩ መገለጹ እና ቡራኬ ማግኘቱ ለአባላቱ ታላቅ መንፈሳዊ ክብር ሲሆን ለእኛም ቢሆን ማህበሩ ምን ያህል ተጠያቂነት እና ግልጽነት ባለው መልኩ ወደፊት ምን መስራት እንዳለብን መንፈሳዊ ብርታትን እንድናገኝ ይረዳናል" ብላለች።

 

ከ1985 አም ጀምሮ መንፈሳዊ አገልግሎቱን በስፋት የጀመረው ማህብረ ቅዱሳን በ2003/4 በጀት ዕም ብዛታቸው 92 የሚደርሱ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ለሚገኙ የአብነት መምህራን እና ተማሪዎች መጠነኛ ወረሃዊ ድጎማ ለማድረግ እቅድ ይዟል። በ2002/3አም በጀታቸው በአማካኝ ከ68,000 ብር እስከ 255,000 ብር የሚፈጁ አስራ ሁለት የልማት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማደረግ በአጠቃላይ በ2003 ዓ.ም በማኅበሩ ከ5ሚሊዮን ብር በላይ ዕቅድ እንደተያዘ ታውቋል።

 

ይህን የአብነት ት/ቤቶች እና ገዳማት ለመርዳት ለሚፈልጉ ምዕመናን በሚከተለው አድራሻ በኩል የበኩላቸውን እገዛ እንዲያደርጉ አዘጋጆቹ መንፈሳዊ ጥሪአቸውን አቅርበዋል።

በስልክ ቁ +251-11-1553625፣ +251-11-1553625፣ +251-91-175 15 29

ባንክ: A/C No፦ 0173060464000

CBE, Arat Kilo Branch

 

E-mail Head office : This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Europe Centre: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

America Centre This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

web page: www.eotc-mkidusan.org


 

ለግንዛቤዎት ቢረዳዎት

፠ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ከሜመጡት ቱሪስቶች መካከል ከ85% በላይ አመጣጣቸው የቤ/ክ የብትን ለማየት ነው

፠ገዳማትና የአብነት ት/ቤቶች እስከ 1908አም"የትምህርት ሚኒስተር " ሆነው አገለግለዋል

፠እጅግ ውድ የሆኑ ከ3064 በላይ ነዋየ ቅድሳት እና የብራና መጻሕፍት በስርቆት ተወስደው በውጪ አገር ቤ/መጻሕፍት ቤቶች ይገኛሉ

፠ኢትዮጵያ በአፍሪካ የራሳ የሆነ ፌደል እና አሃዝ ያላት ብቸኛ ሃገር ነች

፠ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከ400000 በላይ አገልጋዮች በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሃገር አሏት

፠በኢትዮጵያ ውስጥ ከ37 ሺህ በላይ ገዳማት አድባራት እና ቤ/ክ አሉ

፠የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከ40ሚሊዮን በላይ ክርስቲያን ምመናን በመያዝ በአፍሪካ አንደኛ በአለም ሁለተኛ ደረጃላይ ትገኛለች

 

(ምንጭ፦ አቶ በላቸው ጨከነ በቅርቡ ለግንዛቤ ማስጨበጫ ይረዳ ዘንድ ካሰባሰቧቸው መረጃዎች የተወሰደ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!