ኢሕአዴግናን አጋር ድርጅቶቹን ውሑድ ፓርቲ ለማድረግ ዝግጅቱ ተጥናቅቋል

አቶ መለስ ዓለም

ከሕወሓት በስተቀር የኢሕአዴግ ፓርቲዎችና አጋሮቹ ውሕደቱን ደግፈዋል

ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 14, 2019)፦ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶችንና አጋር በሚል ይታወቁ የነበሩ ፓርቲዎችን በማዋሐድ አንድ ሕብረብሔራዊ ፓርቲ ለማድረግ ሲካሔድ የቆየው ዝግጅት መጠናቀቁ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት መተዳደሪያ ረቂቅ ደንብ አፀደቀ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

የተሻሻለው የመከላከያ ሠራዊት ደንብ ቁጥር 385/2008ን ነው

ኢዛ (ሰኞ ኅዳር ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 11, 2019)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት መተዳደሪያ ረቂቅ ድንብና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ ማሳለፉ ተገለፀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የውጭ ዜግነት ያላቸው ዲያስፖራዎች በውጭ ምንዛሪ የባንክና ኢንሹራንስ አክስዮኖችን ሊገዙ የሚችሉበት ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ

National Bank Ethiopia

ዲያስፖራው በውጭ ገንዘብ የገዛውን አክስዮን ሲሸጥም ኾነ ትርፍ ሲያገኝ በብር ይኾናል የሚለው የረቂቁ መመሪያ አከራካሪ ይኾናል ተብሎ ይጠበቃል

ኢዛ(ረቡዕ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 6, 2019)፦ የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን (ዲያስፖራ) በኢትዮጵያ በየትኛውም የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ በውጭ ምንዛሪ አክስዮን ገዝተው ባለድርሻ የሚያደርጋቸውና አጠቃላይ ሒደቱን የሚመለከት ረቂቅ ሕግ መዘጋጀቱ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በቄሮ ተቃውሞ ከገጠማቸው በኋላ ከአምቦ በሔሊኮፕተር ወጡ

images/doc/images/news/2019/191022-pm-abiy-ahmed-winner-of-nobel-peace-prize.jpg

“ዳውን ዳውን ዐቢይ! ዳውን ዳውን ቲም ለማ!” የአምቦ ቄሮዎች

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 31, 2019)፦ በአምቦ ከተማ “የሰላም ኮንፈረንስ” ላይ ለመሳተፍ ወደ ከተማይቱ ያቀኑት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ፤ በውይይቱ እንዳንሳተፍ ተከልክለናል ባሉ የከተማይቱ ቄሮች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው። ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ለማ መገርሳና የኦሮሚያ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ብሔርንና እምነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችና ግጭቶች በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ነው” ኢሰመጉ

ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS COUNCIL

መንግሥት ሕጋዊና የማያወላውል እርምጃ በመውሰድ የዜጐችን ሕይወትና መብታቸውን ሊያከብረና ሊያስከብር ይገባል!

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 28, 2019)፦ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔ (ኢሰመጉ)፤ “መንግሥት የዜጎችንን ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወጣ!” በማለት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ክፍል አንድ አንቀፅ 14ን በመነሻነት ጠቅሶ፤ ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሠሥ፣ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነትና የነፃነት መብት እንዳለው አስታውሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሰሞኑ ብጥብጥ ዙሪያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከተለያዩ የሕብረተሰብ አካላት ጋር ተወያዩ

PM Dr. Abiy Ahmed

“የኛ ሐሳብ የማይስማማቸው ካሉ አማራጭ ያቅርቡ”

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 28, 2019)፦ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከመከካከያ ሚንስትሩ አቶ ለማ መገርሳና ከኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በመኾን ከአባገዳዎች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መምህር ታዬ ቦጋለ መመረዛቸውን ተናገሩ

Taye Bogale

ገዳይ መንጋዎችንና መሰሪ መሪዎቻቸውን የኢትዮጵያ አምላክ እንዴጤዛ ያረግፋቸዋል!

ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 27, 2019)፦ መምህርና የታሪክ ምሁር የኾኑት ታዬ ቦጋለ የተመረዙ መስሎ እንደሚሰማቸው በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ትናንት ጠዋት አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሕአዴግ አንድ ሲኾን ወይም ሲበተን፤ ኢትዮጵያ ትሞታለች የሚለው ሐሳብ ከድንቁርና የሚመነጭ ነው

Ethiopian parliament today

የፓርቲ እሳቤ ሳይኖር ኢትዮጵያ ነበረች

ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 22, 2019)፦ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በኢሕአዴግ ውሕደት ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ “ኢሕአዴግ አንድ ሲኾን ወይም ሲበተን፤ ኢትዮጵያ ትሞታለች የሚለው ሐሳብ ከድንቁርና የሚመነጭ ነው” በማለት ምላሽ ሠጥተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ማንም ኃይል ኢትዮጵያን ከህዳሴው ግድብ ግንባታ ሊያስቆም አይችልም” ጠ/ሚ ዐቢይ

Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed shakes hands with Egyptian President Abdel-Fattah el-Sissi, June 10, 2018

“ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ አለባት” የግብጽ መገናኛ ብዙኃን

ጠ/ሚ ዐቢይ እርምጃ ይወሠዳል በሚል ለሚሰማው ነገር፤ ውጊያ መፍትሔ አለመኾኑን ተናገሩ

ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 22, 2019)፦ በዛሬው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአባላቱ ካቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ውስጥ ግብጽ በህዳሴው ግድብ ላይ እያሳየች ያለችው አቋምን የሚያመለከት ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ግብጽ እያደረገች ያለችው እንቅስቃሴ ስጋት አይኾንም ወይ? የሚል ይዘት ነበረው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠ/ሚ ዐቢይ የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸውንና የውጭ አገር ዜጋ የኾኑ የሚዲያ ባለቤቶችን አስጠነቀቁ

PM Abiy Ahmed answering questions in parliament

“በኢትዮጵያ ሰላምና ሕልውና ላይ ከመጣ እርምጃ መውሰዳችን አይቀርም” ዶ/ር ዐቢይ

ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 22, 2019)፦ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል፤ ሚዲያዎችን የሚመለከት ነበር። የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ሞያው ከሚፈቅደው ውጭ ከሚዛናዊነት ርቀው የሚሠሩ ሚዲያዎች እየተስተዋሉ ነውና፤ ምን ታስቧል የሚል ይዘት ያለው ጥያቄ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!